#እስከ ሞት ያስጨከነው ደብዳቤ
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቀድሞዋ ፋርስ በአሁኗ ኢራን በቀድሞዋ ፋርስ በአንድ ወገን እጅግ ጠንካራ ክርስቲያኖች፣ በሌላ ወገን ደግሞ ጣዖት የሚያመልኩ እጅግ ጨካኝ ነገስታት ነበሩባት፡፡ በርካታ ክርስቲያኖችም ክርስቶስን አንክድም፣ ለጣኦት አንሰግድም በማለት በሰማዕትነት አርፈውባታል፡፡ ከእነዚህ አንዱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዓበይት ሰማዕታት ወገን የሚቆጠረው ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ነው፡፡ በዘመኑ ከነበረው ንጉስ ሠክራድ ጋር እጅግ ይዋደዱ ነበር፡፡ ይሁንና ቅዱስ ያዕቆብ ከክርስቲያን ቤተሰቦች የተወለደ በትምህርተ ሃይማኖት ያደገ፣ በክርስትና ስርዓት ሚስት አግብቶ የሚኖር ፍጹም ክርስቲያን ነበር፡፡ ንጉሱም ከፍቅሩ ብዛት የተነሳ በቤተ መንግስት ሹመት ሰጥቶ ከእርሱ ጋር እንዲኖር አደረገው፡፡
ቅዱስ ያዕቆብም በቤተ መንግስቱ ያለው የስጋው ምቾት መንፈሳዊ ሕይወቱን እያስረሳው ከጾምና ከጸሎት አራቀው፡፡ በሒደትም ንጉሱ ያለውን ሁሉ እንደ ክርስቲያን ሳይመዝን ይሁን እሺ የሚልና ተግቶ የሚፈጽምም ሆነ፡፡ ነገሮች ከልክ ማለፍ ጀመሩ፡፡ ንጉሱ ሠክራድ “እኔ እኔ ለማመልካቸው ለእሳትና ለፀሐይ ስገድ አምልካቸውም” አለው፡፡ እርሱም በተለመደ እሺታው ሊያስደስተው ፈልጎ ሰገደ፤ ማምለክም ጀመረ፡፡ በስጋችን ምቾት፣ በወንድማዊነት ፍቅር ሰበብ፣ ሃይማኖት ከምግባር መግባ ያሳደገችንን ቅድስት ቤተክርስቲያን የተውን “በክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመላችንን ያጠፋን ስንቶች ነን? ለክብር ያበቃችንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያናነናቅንስ? ገዳማትን የረሳን፣ ትጋታችንን የተውን፣ ለባልንጀሮቻችን ፍቅር የክርስቶስን ፍቅር የተውን፣ ከቅዳሴው ይልቅ ሌላ ድምጽ እየሰማን ያለን ራሳችንን እንመርምር፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ያደረገውን ነገር በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ሰምተው እጅግ አዘኑ፡፡ እህቱ ሚስቱና እናቱ ግን ለሐዘናቸው ዳርቻ አልተገኘለትም፡፡ በእንባና በለቅሶም ደብዳቤ ጻፉለት፡፡ "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን:: በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም:: ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንህ እኛ አንተን እንደ ወንድም፣ እንደ ባልና እንደ ልጅ ልናምንህ ይከብደናል::" ይላል ደብዳቤው፡፡ እዳሉትም ከአካባቢው ለቀቁ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ሲያነበው ደነገጠ፤ በምድር ያሉት ብቸኛ የስጋ ዘመዶቹ እንርሱ ናቸውና፡፡
ከንጉሱ ጋር በነበረው ያልተገባ አካሔድ የደም ዋጋ ከፍሎ ያዳነውን ጌታ መካዱ ሲገባውም "ጌታ ሆይ! በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ: ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን! በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ!" ብሎ መሪር እንባ አለቀሰ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ በእንባና በለቅሶ አሳልፎ በጠዋት ንስሐ ገባ፡፡ በጾምና ጸሎት ጸንቶ ከንጉሱ አደባባይ ራቀ፡፡ ንጉስ ሠክራድም አስጠርቶ "ምን ሆነሃል? ስለ ምንስ በአምልኮ ከእኔ ተለየህ?" ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብም "የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲል መለሰለት፡፡
ንጉሱ ሊያባብለው ሞከረ እንደማይሆን ሲገባው በደም እስኪነከር አስደበደበው፡፡ በክርስቶስ ፍቅር እንደጸና ሲገባውም ከጣቶቹ ጀምሮ አካሉን እንዲቆራርጡት ነገር ግን ቶሎ እንዳይገድሉት ወሰነ፡፡ ሰውነቱ ሲቆራረጥ መከራው ሲጸናበት እርሱ ግን ያመሰግን ነበር፡፡ በመጨረሻም ከወገቡ በላይ ያለ አካሉና ራሱ ብቻ ነበር የቀረው፡፡ ይሕም ሆኖ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ 42 ቦታ የተቆራረጠው ሰውነቱን ረስቶ በቀረው አካሉ ያመሰግን ነበር፡፡ በመጨረሻም አንገቱን በሰይፍ መተው ገድለውታል፡፡ እስከ ሞት ያስጨከነውን ደብዳቤ የጻፉለት እናቱ፣ እህቱና ሚስቱ በሰማዕትነት በማለፉ በደስታ እየዘመሩና በስጋ ስለተለያቸው እያለቀሱ ሽቱ ቀብተው ቀብረውታል፡፡
ሰማዕታት የዚህ ዓለምን ክብር ንቀው አንገታቸውን ለሰይፍ እንደሰጡ፣ ገዳማውያን አባቶችና እናቶች የዓለምን ጣዕም ንቀው በበረሀ ወድቀዋልና በአታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እናግዝ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444