ለሕወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሆነ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ
አንዳንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ረገብ እያለ የቀጠለው የሕወሓት አመራሮች ሽኩቻ መነሻው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የተሳተፈው የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ምን መፈጸምና አለመፈጸም እንዳለበት በተገቢው ሁኔታ ሳይደራደር ትዕዛዝ ተቀብሎ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን፣ የሕወሓት አንደኛው ክንፍ ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።
ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ዘ ኒው ሂዩማኒታሪያን ከተሰኘ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት አሁን በትግራይ ፖለቲካ ልሂቃን መካከል ለሚታየው መቆራቆስ ዋነኛ ምክንያት ነው፤›› በማለት ስምምነቱን ‹‹የክፍፍሉ መነሻ›› ብለውታል።
አቶ ጌታቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይዘውት የተጓዙት ተደራዳሪ ቡድን በጦርነት ለደቀቀችው ትግራይ፣ ‹‹ጦርነቱን ብቻ እንዲያስቆምና ከዚያ ያለፈም ያነሰም ነገር እንዳይፈጽም ነበር ተልዕኮ የተሰጠው፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ የክልሉን መንግሥት የሚያፈርስ ትዕዛዝ ጭምር ይዘው መጥተዋል...
@ethio_mereja_news