በአዲስ አበባ ብሥራተ ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካርል አደባባይ ቅርንጫፍ ላይ በዛሬው ዕለት በተፈጠረ አለመግባባት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።
በአለመግባባቱ ሳቢያ የሦስት ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ከተከታተሉ ሰዎች መረዳት ችሏል።
ህይወታቸው ያለፈው በባንኩ በጥበቃ ሰራተኝነት ሲያገለግሉ የነበሩ አካላት ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በባንኩ የሰው ህይወት ስለማለፉ ማረጋገጥ ቢችልም ዝርዝር ክስተቱን ከባንኩ ለማረጋገጥ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም ሲልም ዘግቧል ።
ይህንን በሚመለከት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን የጠየቅ ሲሆን "ጉዳዩ በምርመራ ላይ ነው" የሚል አጭር ምላሽ ተስጥቶታል።