የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ቁልፍ የተግባር አመላካችና የአገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
--------------------------------------------------
(የካቲት 26/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደ መነሻ ያሰባሰባቸውን 91 ቁልፍ የተግባር አመላካችና የአገልግሎት እርካታ ትንተና እና ሰነድ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ነው።
ትንተናውን መሠረት አድርጎ የሚዘጋጀው ሠነድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸምና የአገልግሎት አሠጣጥ እርካታ ላይ ያለውን ጥንካሬና ክፍተት በመለየት ለቀጣይ አፈጻጸም ግብዓት የሚገኝበት መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ስርዓተ ትምህርትና ፕሮግራሞች ዴስክ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ነጋዎ ገልጸዋል።
ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተሰበሰቡ መረጃዎች ላይ መሠረት አድርጎ በመከናወን ላይ ያለው የትንተና እና ሰነድ ዝግጅት ተቋማቱ የቁልፍ ተግባር አፈጻጸምና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉበትን ደረጃ ከማመላከት ባለፈ በቀጣይ ያለባቸውን ሀላፊነት ከተጠያቂነት ጋር እንዴት መወጣት እንዳለባቸው የሚያመላክት መሆኑን የስራ ሀላፊው ገልጸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የምርምር ስነ-ምግባር ዴስክ ሀላፊ ዶ/ር አቡሌ ታከለ በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ገለጻ የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሠረት አድርጎ የሚከናወነው ትንተና እና ሰነድ ዝግጅት ቁልፍ የተግባር አመላካቾችን ለማጥራትና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ደረጃን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን አመላክተዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የተፈራረመውን የቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያ ስምምነት አፈጻጸም የሚደግፉ በርካታ የሪፎርም ስራዎች እያከናወነ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።