ለድርጅት ደንበኞችና ተቋማት በክላውድ ላይ የተመሰረቱ 7 የዲጂታል ሶሉሽኖች ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር #EnterpriseSolutions #Ethiotelecom
ኩባንያችን የተቋማት አቅም የሚገነቡ፣ አሰራሮችን የሚያዘምኑ እንዲሁም ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው የላቀ አገልግሎት በማቅረብ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ የሚያስችላቸው ሰባት የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖችን ተግባራዊ ማድረጉን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል፡፡
ይፋ ያደረግናቸው ሶሉሽኖችን የዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ፣ ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ፣ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን፣ የትምህርት አመራር ስርዓት ሶሉሽን እንዲሁም የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት ሶሉሽን፣ ቴሌ የጥሪ ማዕከ...