ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




በረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው (የታሪክ መምሕርና ተመራማሪ) የተሰናዳው ማሕደረ ጀግንነት ወማሕደረ ንዑዳን መጽሐፍ ሊመረቅ ዛሬ ከቀኑ ከ8:00 ሠዓት ጀምሮ በራስ አምባ ሆቴል ይመረቃል።

የአገረሰብ ዕውቀት፣ የሥነ-ልሳን እና የታሪክ ተመራማሪው ጆርጅ ብራይን ሃንቲንግፎርድ ተርጉሞ እና አሰናድቶ ባቀረበየው (Glorious Victories of Amda Seyon: King of Ethiopia) የኢትዮጵያው ንጉስ ዐምደ ጽዮን የጀግንነትና የድል ሐተታ ዜና መዋዕል ስለ ንጉሱ የድል ሚስጥርና የጦር አሰላለፍ በስፋት ተነስቷል። ፀሐፌ-ታሪክ ተክለጻድቅ መኩሪያ ንጉስ ዐምደ ጽዮን የጦር ስልጠና እና አወቃቀር "የኢትዮጵያ ታሪክ: ከዐፄ ይኩኖአምላክ እስከ ዐፄ ልብነድንግል" በተሰኘው የታሪክ መፅሐፍ ቢፅፉትም፣ በዜና መዋዕሉ በተለየ አፅንዖት ተገልጿል።

ሃንቲንግፎርድ ገፅ 81-82 ድረስ፣ ንጉሱ ዐምደ ጽዮን ጃናሞራ፣ ኮረም፣ ጎጃም፣ ሐድያ፣ ተኩላው የተባሉ እጅግ የሰለጠኑ ኢትዮጵያን ጠባቂ እግረኛና ፈረሰኛ ጦር ያደራጁ ቢሆንም፣ ማንኛውንም ጥቃት፣ ኃይል እና ጦር የሚያፍረከርከው፣ በዜና መዋዕሉ፣ "በወርቅና በብር የተጌጡ ጦር፣ ጎራዴና ጋሻ ታጣቂ፣ ሲዋጉ እንደ ንስር አሞራ በጠላት ላይ የሚሽከረከሩ፣ ሲያጠቁ እንደ ሚዳቋ በፍጥነት የሚፈናጠሩ፣ ከገጠሙ ያለ ድል የማይመለሱ፣ ተናዳፊ የሆኑ 'ቀስተ ንኅብ' (Spears of the Bee) የተሰኘው የሸዋውን ጦር ዕዝ አደራጅተው ነበር። ቀስተ ንኅብ በቁጥር ከሌሎች ዕዞች ያነሰ፣ ግን በጦር ስልትና ጀብዱ ከዐምደ ጽዮን ቤተ መንግስት እስከ ቀይ ባሕር እና ግብፅ በረሃ የሚወረወር የኢትዮጵያ ክንድ ነበር ብሎታል።

የእኛ ዘመን ቀስተ ንኅብነት የተመሰከረበት፣ ዳግም ለኢትዮጵያ የተከፈለ ውዱ መስዋዕትነት፣ የወገን ፍቅር፣ በገቢር የተገለጠ ጀግንነት የተሰነደበት ክቡር ማሕደር : ቀስተ ንኅብ።


የሀሁ መጽሐፍት መደብር አድራሻ፦

አድራሻ ቁ. 1 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ
2 ስታዲየም ናሽናል ታዎር
ስ.ቁ 0911006705
0924408461




ልዑል ዶ/ር አስፋወሰን አሥራተ ካሣ እንዳተቱት አባቶቻችን የሠራሯት፣ ያበጃጇት፣ የኖሩባትና ታሪካቸውን የጻፉባት የታላቋ ሀገር የኢትዮጵያ ጥንታዊ ማንነትና ምንነት በዚህ ጥልቅ የታሪክ ፍሰት ማሳያ መጽሐፍ ግልጽ ሆኖ ቀርቦልናል። የታሪክ ተመራማሪና ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው በተባ ብዕሩ ተሰውሮብን የነበረውን ኢትዮጵያ ለዘመናት ያለፈችበትን ያልተገለጠ እውነት መጋረጃውን ገፎ፣ አቧራዋራውን አራግፎ “የታላቋ ኢትዮጵያ ዝክረ ታሪክ” በሚል ታላቅ ርእስ እንደ ስሙ ታላቅ የሆነ መጽሐፍ እነሆ ለንባብ አብቅቶልናል።
መጽሐፉ በዘመናት ሂደት፣ በሕዝቦች ዑደት የኢትዮጵያ በሮች ሲጠቡና ሲሰፉ፣ ሲላሉና ሲጠብቁ መዛግብቶቿን እየከፋፈተ ያሳያል፤ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ድርሳናት እያመሳከረ፤ በየዘመናቱ የሆነውን የዓለመ ሰብእን ክዋኔ እየመረመረ እነሆ ማንነታችሁ ራሳችሁን ተመልከቱ ይለናል። የሀገራችንን የታላቅነቷን ምሥጢሮችም አንድ በአንድ እየዘረዘረ ወደ ቀደመው ታላቅነታችን ይጠራናል። ሃገራችን በሐሰት የትርክት ታሪክ እየተናጠች በምትገኝበትና ትክክለኛው ታሪካዊ እውነታ እየደበዘዘ ባለበት በዚህ ወቅት ነባራዊውን ሃቅ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ መዛግብትን በመመርመር በማስረጃ አስደግፎ የኢትዮጵያን ጥንታዊና የመካከለኛው ዘመን ታሪክ እንዲህ ገሃድ አውጥቶ የሚያስረዳና ለተመራማሪዎችም ትልቅ ዋቢ በመሆን የሚያገለግል ይህን የመሰለ ድርጁ የምርምር መጽሐፍ ማግኘት ትልቅ ገጸ በረከት ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ነው።
ዋና አከፋፋይ፦ ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ቁ.1 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ.
ቁ.2 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ስ.ቁ.2519 11 00 67 05




የጎንደር መንበረ መንግስት መድሃኒዓለም የአራቱ መጽሐፍት ቤት መምህር እና አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የተረጎሙት 1044 ገጽ ያለው የሐይማኖተ አበው የትርጓሜ መጽሐፋቸው ድጋሜ ታትሞ ለገበያ ቀርቧል። የመጽሐፉ ገቢ ለጎንደር ጉባኤ ቤት ነው ተብሏል።

👉መጽሐፉ ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጽሐፍት መደብር ።
አድራሻ ቁ.ጥ 1 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ
2 ስታዲየም ናሽናል ታዎር
☎️☎️☎️🤳 0911006705
0924408461




የቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ "ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ" የተሰኘ የታሪክ መጽሓፍ በሀሁ መጽሐፍ መደብር እየተሸጠ ነው። የሀሁ መጻሕፍት መደብር አድራሻ፦
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2. ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ታዎር
ስ.ቁ. 09 11 00 6705




"ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ" የተሰኘ የታሪክ መጸሓፍ ተመረቀ
****

የቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ "ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ" የተሰኘ የታሪክ መጽሓፍ ተመረቀ።

መጽሐፉ በአማርኛ ቋንቋ ስለቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የህይወትና የኢትዮጵያ የታሪክ ውጣ ውረዶችን የሚያትት ሲሆን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለምረቃ በቅቷል።

በመፅሐፍ ምረቃው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ተገኝቷል።

የቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ፋውንዴሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ንጉሴ አምቦ በመርሃ ግብሩ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፀንታ እንድትቆም ልጆቿና ንጉሰ ነገስቷዋ የተጓዙበትን ረጅም መንገድና የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚዘክር ታላቅ መጽሐፍ ነው።

የመጽሐፉ ሽያጭ ለቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ፋውንዴሽን ገቢ የሚውል ነው ተብሏል። የመጽሐፉ ሽያጭ በፋውንዴሽኑ አማካኝነት በመላ ሀገሪቱ በሁሉም መጽሐፍት መሸጫ መግዛት እንደሚቻል ገልጸዋል።

በቀጣይም ቅጽ ሁለት እንደሚታተም ተናግረዋል።

©ኢ ፕ ድ

መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2. ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ታዎር
ስ.ቁ. 2519 11 00 6705



Показано 11 последних публикаций.

18 104

подписчиков
Статистика канала