በረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው (የታሪክ መምሕርና ተመራማሪ) የተሰናዳው ማሕደረ ጀግንነት ወማሕደረ ንዑዳን መጽሐፍ ሊመረቅ ዛሬ ከቀኑ ከ8:00 ሠዓት ጀምሮ በራስ አምባ ሆቴል ይመረቃል።
የአገረሰብ ዕውቀት፣ የሥነ-ልሳን እና የታሪክ ተመራማሪው ጆርጅ ብራይን ሃንቲንግፎርድ ተርጉሞ እና አሰናድቶ ባቀረበየው (Glorious Victories of Amda Seyon: King of Ethiopia) የኢትዮጵያው ንጉስ ዐምደ ጽዮን የጀግንነትና የድል ሐተታ ዜና መዋዕል ስለ ንጉሱ የድል ሚስጥርና የጦር አሰላለፍ በስፋት ተነስቷል። ፀሐፌ-ታሪክ ተክለጻድቅ መኩሪያ ንጉስ ዐምደ ጽዮን የጦር ስልጠና እና አወቃቀር "የኢትዮጵያ ታሪክ: ከዐፄ ይኩኖአምላክ እስከ ዐፄ ልብነድንግል" በተሰኘው የታሪክ መፅሐፍ ቢፅፉትም፣ በዜና መዋዕሉ በተለየ አፅንዖት ተገልጿል።
ሃንቲንግፎርድ ገፅ 81-82 ድረስ፣ ንጉሱ ዐምደ ጽዮን ጃናሞራ፣ ኮረም፣ ጎጃም፣ ሐድያ፣ ተኩላው የተባሉ እጅግ የሰለጠኑ ኢትዮጵያን ጠባቂ እግረኛና ፈረሰኛ ጦር ያደራጁ ቢሆንም፣ ማንኛውንም ጥቃት፣ ኃይል እና ጦር የሚያፍረከርከው፣ በዜና መዋዕሉ፣ "በወርቅና በብር የተጌጡ ጦር፣ ጎራዴና ጋሻ ታጣቂ፣ ሲዋጉ እንደ ንስር አሞራ በጠላት ላይ የሚሽከረከሩ፣ ሲያጠቁ እንደ ሚዳቋ በፍጥነት የሚፈናጠሩ፣ ከገጠሙ ያለ ድል የማይመለሱ፣ ተናዳፊ የሆኑ 'ቀስተ ንኅብ' (Spears of the Bee) የተሰኘው የሸዋውን ጦር ዕዝ አደራጅተው ነበር። ቀስተ ንኅብ በቁጥር ከሌሎች ዕዞች ያነሰ፣ ግን በጦር ስልትና ጀብዱ ከዐምደ ጽዮን ቤተ መንግስት እስከ ቀይ ባሕር እና ግብፅ በረሃ የሚወረወር የኢትዮጵያ ክንድ ነበር ብሎታል።
የእኛ ዘመን ቀስተ ንኅብነት የተመሰከረበት፣ ዳግም ለኢትዮጵያ የተከፈለ ውዱ መስዋዕትነት፣ የወገን ፍቅር፣ በገቢር የተገለጠ ጀግንነት የተሰነደበት ክቡር ማሕደር : ቀስተ ንኅብ።
የሀሁ መጽሐፍት መደብር አድራሻ፦
አድራሻ ቁ. 1 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ
2 ስታዲየም ናሽናል ታዎር
ስ.ቁ 0911006705
0924408461