ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል በመጠቀም ዩክሬን ላይ ጥቃት ፈፀመች
ሩሲያ በዩክሬን መካከለኛው ምስራቅ በምትገኘው ዲኒፕሮ ከተማ ላይ ያነጣጠረ አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል በመጠቀም ጥቃት ስለመክፈቷ ዩክሬን አስታውቃለች።
ይህ ጥቃት ከተረጋገጠ ሞስኮ በጦርነቱ ውስጥ እንዲህ አይነት ሚሳኤል ስትጠቀም የመጀመሪያዋ ይሆናል ተብሏል።
የዩክሬን አየር ኃይል ትክክለኛውን የሚሳኤል ዓይነት ባይገልፅም፤ በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ በሰጠው መግለጫ ሚሳኤሉ የተወነጨፈው ከካስፒያን ባሕር ጋር ከሚዋሰነው ከሩሲያ አስትራካን ክልል ነው ብሏል።
በዲኒፕሮ ከተማ ከሌሎች ስምንት ሚሳኤሎች ጋር አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል የተተኮሰ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የዩክሬን ጦር ከእነዚህ ውስጥ ሥድስቱን መምታቱንም አስታውቋል።
በጥቃቱ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውንና በኢንዱስትሪ ተቋማት እና የአካል ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል ሲል የዘገበው ኤፒ ነው።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L