ኤቶዮጵ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


Enjoy....
🔴Music 🎶
🔴News
🔴Untold history
🔴Poem
🔝HOME OF FUN AND KNOWLEDGE🔝
For any comment @Ethopianism1
https://t.me/joinchat/AAAAAEtLCnvgbwuhJunrLA

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ATC NEWS
ያገኘ ይተባበረኝ , ያላገኘ share ያድርግልኝ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ይህ ከዚህ በታች የሚታየውን ዶክመንት ( ቴምፓ ) ያገኘ አካል
ካለ በዚሁ ገፅ inbox አድርጉልን , ያላገኘ ደግሞ share
አድርጉልኝ በማለት እህታችን ትዕግስት ወርቁ ጠይቃለች ። #share በማድረግ እንተባበራት


@amharictutorialclass
@amharictutorialclassbot


"መንገድ ተዳዳሪ ነኝ።
'መተዳደር' ከባድ ቃል ነው። 'መተዳደር' የሚለው ቃል በሐምሌ
ብርድ ወፍራም ጋቢ ተከናንቦ አጃ መጠጣት ይመስላል። ግን
እንዴት ነው መንገድ ላይ እየኖሩ መተዳደር? . . .
ላውንቸር ተሸክሜ በኩራት የተራመድኩበት ጎዳና ላይ፤ ሀገር
እንደሌለው ሰው አፈር 'እፍ' ብዬ ተኛሁ . . . .
ያልሞትኩት ፈሪ ስለሆንኩ ይመስለኛል። ፈሪ አልነበርኩም፤ ግን
ይመስለኛል።
ያቺ ሀገሬን፣ ያቺ በሚስቴና በእንጀራ ልጄ የተካኋትን ሀገሬን
እሞትላታለሁ ስል እውነቴን ነበር።
የቆምኩት እስዋ ላይ አይደለ?
የምተነፍሰው እሷ ላይ ቆሜ አይደለ?
አቅም የላትም ግን እንደ ዶሮ ጭራ አብልታ ታሳድረኛለች። ግራና
ቀኝ በጠላት ተከባ፣ እንደ ልጅ መከራዋን እንዳላይ አድርጋ ከልላ፣
ጠራም ደፈረሰም ጠላዋን አጠጥታኛለች።
ወታደር ስለሆንኩ፤ እኔንም ደርቦ ልዩ ጥቅም እንዳገኘሁ ሁሉ
'የወታደር መንግስት' እያለ ሲሳደብ የኖረ ሲቪል ለእኔ ግድ
ይሰጠዋል?
ሲሰድበኝ ኖሮ እንደገና ሲጨንቀው 'ትታችሁ መጥታችሁ ሀገራችንን
አስወሰዳችሁ' እያለ ከሚያወራ ቀባጣሪ ምን ይጠበቃል? . . .
አገሬን ነክተውብኝ ጮኼ የተነሳሁ ነኝ። ምርምር አላደርግኩም።
ተማርን እንደሚሉት አገሬን በቃላት ነዝንዤ በፉክክርና በምቀኝነት
ለጠላት አልሰጠሁም። ጠላቷ እንዲደፍራት የእናቴን ቀሚስ ወደ
ላይ አልሰበሰብኩም። ደፋሪው የልጆቿን ታሪክ ሰምቶ ሲርበተበት፣
ሊደፍራትም ሲፎክር 'አይዞህ' ብዬ የሱሪውን አዝራር
አልፈታሁለትም።
እኔ የፊት በር ስዘጋ የጀርባ በር ከፍተው፣ ጠላታቸውን አገራቸው
እልፍኝ አስገብተው፣ እናታቸው ተከናንባ የተኛችበትን ብሉኮ
ገፈው፣ 'ይቻትልህ' እንዳሉት አጅሬዎች አይደለሁም . . .
ከርሞ ከርሞ መቆየት ደጉ፤ ጠላ እየጠጣሁ እዛ አለማያ ኮሌጅ
የሚያማምሩ ለጋ ወጣቶች ሳይ በልቤ 'ለመሆኑ ለእነሱ እግሬ
እንደተሰነከለ፣ ዐይኔ እንደጠፋ፣ ሳንባዬ በብርድ እንደታመመ
ይገባቸዋል? እላለሁ . . .
ወሰናቸውን ስጠብቅላቸው አካሌን ባጎድልም፤ ከምንም
የማይቆጥሩኝ መዓት ናቸው። ድሮ በቆራጡ ዘመን ሀገር ለማዳን
ስንረባረብ፣ ዛሬ ምን የመሰለ የሚያምር ጫማ ለመግዛት ሲሻሙና
ሲያብዱ አያለሁ። እዛም ጥጥና ጎማ የሚሸት ጫማቸው ስር
ያልታዘነለት ተሸናፊ ነኝና አፈር እየተነፈስኩ፣ አስፋልት እየላስኩ
እርመጠመጣለሁ።
ከጫማቸው የረከስኩ ነኝ . . .
የጀልዴሳን አወዳይ ጫት በጎልማሳነቴ ከዚያድ ባሬ መንጋጋ
አላቅቄ እነሱ አፍ አስገብቼ፣ ይኸው መርቅነው በፈዘዙ አይኖቻቸው
እያዩ ጣል ጣል ያደርጉኛል . . .
እገረማለሁ?
.
.
ኧረ አልገረምም!
ክርስቶስን የከዳው አብሮት ቂጣ የቆረሰ እኮ ነው።
ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም ቢሉ ዕውነት አለው።
***
# የስንብት_ቀለማት


🇪🇹🇪🇹ክብር ለእናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሌም በጀግኖችሽ ከፍ ትያለሽ🇪🇹🇪🇹

🇪🇹እንኳን ለታላቁ የአድዋ ድል አደረሳቹ🇪🇹🇪🇹


አድዋ
...................................................
አልፎ ሲያወሩት ሁሉ ነገረ ይቀላል ታሪክ ሁኖ ያልፋል ፡፡ውሸት አይደለም ትላንት አባቶቻችን ከነጭ በላይ ነበሩ ፡፡ዘመኑ የፈቀደለትን ዘመናዊ መሳሪያ ያነገቱ ከነጫጭባ ወራሪ በላይ ነበሩ ፡፡ከጥበብ በላይ ከእውቀት በላይ ከአክሱም ፡ከላሊበላ ፡ከፋሲል ግንብ ፡በላይ ነበሩ ፡፡ስለእራሳቸው ክብር የነበራቸው በማንነታቸው የሚኮሩ "ኢትዮጵያዊ"ብለው በድፍረት በአንደበታቸው እራሳቸውን የሚጠሩ ፡ላመኑበት የሚሞቱ ፅኑ እና ቆራጥ አባቶች ነበሩ፡፡ባህላቸውን፡ወገናቸውን፡ወግና ልማዳቸውን የሚያከብሩ ኢትዮጵያዊ ነበሩ፡፡
" ክብር ለአድዋ ጀግኖች"
"ክብር ለቀደሙ አበው አባቶች"
..... ታሪክን እየዘከርን ታሪክ እንስራ........


ዓድዋ


ካሣ አንድ ለእናቱ አትበሉኝ አልወድም ከገብርዬው በላይ ከየት ይመጣል ወንድም😍

የራስ ሚካኤል እጅ የነራስ መንገሻ
ለጠላት አያጣም ጥጋብ ማስታገሻ❤️

አላሚ ሰው ሲገኝ እንደ ራስ አረጋይ
በመሬት ያስኬዳል በራሪ እንደ ድንጋይ 💪

@ethopianism🇪🇹


ሀመር 😍


አብርሃም ሊንከን
┈┈•✦•┈┈
አብርሃም ሊንከን እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 12 ቀን 1809 ነው የተወለደው። ከ1861 እስከ 1865 ድረስ አሜሪካን የመራ 16ኛው ፕሬዝዳንትም ነበር። ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ በ1865 ዓ.ም. ኤፕሪል 15 ቀን ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትቶ ተገደለ።

አብርሃም ሊንከን ወደ ስኬት ከመድረሱ በፊት በርካታ ያልተሳኩ የሕይወት ውጣ ውረዶችን አልፏል፦

➺ በ1832 ሥራውን አጣ፤

➺ በ1832 ለሕግ አውጪነት ተወዳድሮ ተሸነፈ፤

➺ በ1833 ንግዱ ከሰረበት፤

➺ በ1834 ለሕግ አውጪነት
ተመረጠ፤

➺ በ1835 አፍቃሪው (አን ሩትሊጅ) ሞተችበት፤

➺ በ1836 የአእምሮ መረበሽ ገጠመው

➺ በ1838 ለአፈ-ጉባኤነት ተወዳድሮ ተሸነፈ፤

➺ በ1843 ለአሜሪካ ኮንግረስ አባልነት ለመወዳደር መመረጥ አቃተው፤

➺ በ1848 እንደገናም መመረጥ አልቻለም፤

➺ በ1849 ለመሬት አስተዳደር
ባለሙያነት አመልክቶ ሳይሳካለት ቀረ፤

➺ በ1854 ለሴኔት አባልነት ተወዳድሮ ተሸነፈ፤

➺ በ1856 ለምክትል ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር መመረጥ አልቻለም፤

➺ በ1858 በድጋሚ ለሴኔት አባልነት ተወዳድሮ ተሸነፈ፤

በ መ ጨ ረ ሻ ም
➺ በ1860 በፕሬዝዳንትነት ለመመረጥ በቃ!!!

☆ ይኽ የአብርሃም ሊንከን ወደ ስኬት የተደረገ ረዥም የውጣ ውረድ ጉዞ ነው!!
@ethopianism






ጉርሻ

በ 😍አዳም ረታ 

‘ጉርሻ የሚያቀራርብ ነው። በጉርሻ አይኖቻችን የፈጠሩት ርቀት ይጠፋል። በኋላ እንዳየሁት መጎራረስ ወደ ወሲብ የሚጠጋ ኢትዮጵያዊ ድርጊት ነው።

በማዕድ ዙርያ እንዲቀመጥ የተገደደው ተከፋፍሎ ግለሰብ የሆነው ቡድንና ማሕበረሰብ በሚዘረጋው የበላተኛ እጅ ድልድይነት ይቀራረባል። ‘አብረን በልተን’ ሲባል ውስጡ ከባድ የጉርሻ ይዘት አለ። ጉርሻ አገናኝ አቀራራቢ ድርጊት ነው።

ሌላም ዝርዝር ረድፍ አለው።

በርበሬና ሚጥሚጣ በመብላት ሂደት ውስጥ ዜጋ ያልበዋል። በዚህም በእያንዳንዱ እንጀራ ሰበከት ላይ የአብሮ በላተኛችን የወዝ አሻራ ይታተማል። ይሄ አስገራሚ የሆነ ግላዊ ማህተም ያለው (እያንዳንዱ ሰው የራሱ ከማንም ግለሰብ የሚለየው የጣት አሻራ ስላለው) የተቀናበረ ድራማ በሚጠጋ ‘ማጉረስ’ ተብሎ በተሰየመ ድርጊት ማሕበራዊ ቅንጅት ይከናወናል። በጉርሻ ሂደት የግልና የማሕበራዊ አላማዎች ሳይጋጩ ይቀርባሉ።

ይሄ ሁሉ አማካይ ወደ ሆነው ብልት ወደ አፍ ያመጣል።

ጉርሻ በአፍ መግባት አለበት። የጉርሻ አጉራሽና ጎራሽ የሚረካከቡት ታላቁ ቀዳዳ አፍ ነው። ለሕይወት የሚያስፈልገው ምግብ የሚገባበት፣ ቋንቋ የሚሰራበትና ሰዎች በራሳቸውና በሌላው መሃል ያለውን ልዩነት የሚያጠቡት ወይንም የሚያሰፉት በአፍ ነው። (ሃሃሃሃ) አፍን ሴቶችና ወንዶች የሚጋሩት ቀዳዳ ነው። ይሄ ግንዛቤአችንን ጠንካራ ሁለንተናዊነት ይሰጠዋል። ጎራሽ አፉን ሲከፍት አጉራሽ ሕይወት እንደሚሰጠው አምኖ ነው።

እኔና አንተ፣ አንተና አንቺ….. ወዘተ በስምረት ውስጥ የሚጠፉበትና ‘እኛ’ የሚሆኑበት ነው። የቦታ ርቀት የሚወድምበት ነው።

አብረው ተቀምጠው ሲበሉ የማይጎራረሱ ሃበሾች ቁጥራቸው ከበዛ ኢትዮጵያ የምትባል እንደሌለች ወይ በመለወጥ ላይ እንዳለች ምልክት ነው።’

እቴሜቴ ሎሚ ሽታ


@ethopianism


ፀረ ሰነፍ

ዶ/ር ዐብይ ለካድሬዎች በፍጹም የሚስማማ አይደለም ። ካድሬዎችን በግልጽ "ይሄ ኮፍያና ቲሸርት እያሠራቹ የምታላዝኑትን ነገር ተዉ . . ."
ሲል ይሸነቁጣቸዋል

(ሰውየው ገፅ 319 ሚያዝያ 2011)
@ethopianism


°°°መሰላል°°°

መሰላል ለመውጣት
አለው ትልቅ ብልሀት ።
ያላዩን ጨብጦ ፤
የታቹን ረግጦ ፤
ወደላይ መመልከት
እጆችን ዘርግቶ በሀይል መንጠራራት።
ጨብጦ መጎተት የላዩን ፤
ላይ ታች እንዲሆን ።

አንድ በአንድ እየረገጡ
መሰላል የወጡ ፤
ብልሆች የማይጣደፉ
ሞልተዋል በያፋፉ ።
ዘርግተው የጨበጡት መርገጥ
የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ ።
ሲወርዱ ግን ያስፈራል የረገጡትን ያስጨብጣል ።

#መስፍን_ወልደማርያም ፣ እንጉርጉሮ ፤

@ethopianism


ትንሽ ዘና ትሉ ዘንድ....
.
.

ልጅቷ የቤታቸው በር ይንኳኳና ስትከፍተው ቦይፍሬንዷ ነው፤

ግን አባትዋ በቅርብ ርቀት ሰለነበሩ በስነ-ስርአት ሰላም አላለችውም

ወዲያውኑም ልጁ እንዳይቀባጥር በኮድ

እሷ፦ሀይ ሰላም ነው "አባቴ እቤት ነው" የሚለውን የበውቀቱ ስዩም መፅሀፍህን ልትወስድ መጥተህ ነው?
.
ልጁ፦ወዲያውኑ ነቄ ይልና እር እኔስ
የበአሉ ግርማን
"ታዲያ የት ልጠብቅሽ" የሚለውን መፅሀፍ ልወስድ ነበር።
.
እሷ፦ውይ እሱን መጽሀፍ እንኳን ቶሎ አላገኘውም ባይሆን ያአዳም ርታን "ከማንጎው ዛፍ ጥላ ስር" የሚለውን ልስጥህ
.
ልጁ፦ጥሩ በዛው"እንደ ደርስኩ እደውላለሁ" የሚለውን መጽሀፍም እንዳትርሽው.
.
እሷ፦እር ምንም ችግር የለም
የይስማክ ወርቁን "ቶሎ መጣለሁ ጠብቀኝ" የሚለውንም ይዥልህ መጣለሁ:............
ልጅቷ በሩን እንደዘጋች አባቷ አስቆማትና

አባት፦ በጣም የሚገርም ነው ይህንን ሁሉ መጽሀፍ ያነባል?
.
እሷ፦ አወ አባየ እንዲት ያለ ስማርት ልጅ መሰለህ!
.
አባት፦በጣም ደስ ይላል እንደዛ ከሆነማ እኔም አንድ መጽሀፍ ልስጥሽና ትወስጅለት አለሽ:
.
እሷ፦ እሽ አባየ የቱን መጽሀፍ ?
.
.
አባት፦ እዛ መደርደሪያ ላይ ሀዲስ አለማየሁ የፃፈው "በናተ ቤት በኮድ አውርታችሁ ልባችሁ ውልቅ ብሏል" የሚለውን!
😁😄






Ethiopian Music : Solomon Nigussie ሰለሞን ንጉሴ (እንቢ ካለ) - New Ethiopian Music 2013(Official Video)


ከጋሽ መስፍን በጨረፍታ
*
አንድ ቡና ቤት ውስጥ ግድግዳው ላይ የተሣለ ነው፡፡ ሰውዬው በአንበሳው ላይ ይነጣጥራል። በሰውዬውና በአንበሳው መካከል ጅረት አለ። አዳኙን እግሩ ቀጥ እንዳለ ስታዩት ሣሩ ላይ ተኝቷል ብላችሁ ታስባላችሁ፡፡ ነገር ግን መሆን አለበት ብላችሁ ስለምትገምቱ ነው እንጂ ሥዕሉ ላይ የሚታየው በሣሩ ላይ ሲንሳፈፍ ነው፡፡
እሺ ብሎ አይዞርላችሁም እንጂ ግድግዳውን ዞር ብታደርጉት ደግሞ ቆሞ እሚተኩስ ይመስላችኋል። አንበሳው በተዝናና ሁኔታ ሰውዬውን ትኩር ብሎ ያየዋል። አስተያየቱን ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ ብቻ፣ ‹‹እውነት አሁን ልትተኩስ ነው እስቲ ወንድ!›› የሚል ይመስላል፡፡
የሥዕሉ ምጣኔ ነገር አይወራም፡፡ የፊት እግሮቹ እኩል አይደሉም፡፡ አንዱ ወፍራም አንዱ ቀጭን ነው፡፡ የጅራቱን ማጠር ስታዩ፣ ሥዕሉ ሲሣል ግድግድጋው ጠባብ ነበር እንዴ ማለታችሁ አይቀርም፡፡ የወገቡም ቅጥነት፣ ‹‹ሽንጧ ስምንት ቁጥር›› የሚለውን ዘፈን ያስታውሳችኋል፡፡ የቅርበት-ርቀቱ ሚዛን እንዳልተጠበቀ በግልጽ ይታያል። ለምሳሌ ጠመንጃው ከሰውዬው በልጦ ጅረቱን አቋርጦ አንበሳው አፍንጫ ሊደርስ ትንሽ ቀርቶታል። ከወዲያ ማዶ ያለው ጋራ ደግሞ አንበሳው ጀርባ ላይ ያረፈ ይመስላል፡፡ ከሁሉም ይልቅ የሚገርመው አውሬው ጥቂት እንኳ እንደ መዝለል ወይም እንደ መሸሽ ሳይል በኩራት ዝም ብሎ አዳኙን ማስተዋሉ ነው፡፡ ይኸን ሥዕል ሳይ የአንዳንድ አርበኞች ሥዕል ትዝ አለኝ፡፡
ወረቀቱ ስለማይበቃ ነው እንዳይሉን እንጂ የአርበኛው ጠመንጃ የጣልያኑን ዓይን እየወጋ፣ ‹‹ደጃች እገሌ ጠላት ላይ ሲያነጣጥሩ›› የሚል ከሥሩ እየተለጠፈበት፣ እንደ እንቁጣጣሽ አበባ እየዞረ ሲሸጥ፣ የእነ አብየ ገብረ መንፈንስ ቅዱስ፣ የቅዱሳን፣ የሰማዕታት፣ ያ ያ ሁሉ ታየኝ፡፡›› ታዲያ አሁን እዚህ ለምናነሣቸው መሰረቱ እነሱ ይመስሉኛል፡፡ ጥንት ከምዕተ ዓመታት በፊት የተሣሉትን ግን ለጥናት ሊጠቅሙ ስለሚችሉ ለታሪክና ቅርስ ተመራማሪዎች ቢተው ጥሩ ነው፡፡
ሌላው ያየሁት የፋሲል ግንብ ነው፡፡ ይኸ ሥዕል በብዛት በየቦታው ይታያል፡፡ አሣሣሉ አንድ ይምሰል እንጂ አጠቃላይ መልኩ የተለያየ ነው። አጥር ያለው፣ አጥር የሌለው፣ ዛፍ ያለው ዛፍ የሌለው፣ በጽጌረዳና በሀረግ ያጌጠ፣ በለምለም ሣር ያሸበረቀ፡፡ የአንዳንዱ ጥላ አጣጣል ፍጹም ቅጥ ያጣ ከመሆኑ የተነሣ ፀሐይዋ ሁለት የሆነች ሊመስላችሁ ይችላል፡፡ አንዳንዱ ከበረንዳው በታች ዘንባባ፣ ባሕር ዛፍ፣ ጥድ፣ በያይነቱ በሰልፍ ይተከልበታል፡፡ ምን ያህል እውነት እንደሆነ አላውቅም እንጂ ፓፓያ የተሣለበትም አለ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡
የግንቡ የአካባቢ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን፣ ቀለሙም ብዙ ዓይነት ነው፡፡ ቢጫ፣ ሰማያዊ፣ ሮዝ፡፡ የአራት መቶ ዓመት ህንፃ በፒያሳ ቀለም መታደሱ እንኳን አይከፋም፡፡ እኔን በጣም ያስገረመኝ ግን፣ ከግንቡ ፊት ለፊት፣ ከቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት አንዲት ሹርባ የተሠራች የሀገር ልብስ የለበሰች ውብ ወይዘሮ፤ ጃንጥላዋን ከፍ አርጋ ይዛ ገበያ አዳራሽ እምትሄድ ይመስል በቄንጥ ስትራመድ የሚያሳየው ሥዕል ነው፡፡ እስቲ ሴትየዋ እዚያ ምን ታደርጋለች? ላልጠፋ ግድግዳ … ለብቻዋ መሳልስ ይቻል የለም!
በተለይ የፋሲል ግንብን፣ የአክሱም ሐውልትን፣ ጢስ ዐባይን፣ ላሊበላን የሚሥሉ ሰዎች፣ ባዶ ቦታ ለምን ባዶውን ይቅር እያሉ ነው መሰለኝ፤ ደስ ያላቸውን ነገር ይጨምራሉ፡፡ ባዶ ቦታ ማስፈለግ አለማስፈለጉን ሳያስተውሉ፡፡ ለምሳሌ፣ ወፎችፐ ከሩቅ እየበረሩ ሲመጡ እንዲያውም ሰማይ ካለ ወፎች በግድ ይኖራሉ፡፡ ወንዝ ወይም ኩሬ ከተነሳ ዳክዬዎች ሲዋኙ መታየት አለባቸው፡፡ ዛፍ ደግሞ ጦጣ ከሌለችበት ዛፍ ሊሆን አይችልም። ሣሩም ሁልጊዜ አረንጓዴ ነው፡፡ ምናልባት ለዚህ የሚገፋፋቸው የኢትዮጵያ ልምላሜ ይሆን? በአጠቃላይ የቡና ቤት ሠዓሊያዎች ትልቅ ድክመት ዝምድና ወይም ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ጎን ለጎን ማስቀመጣቸው ነው፡፡ ማን ያውቃል፣. ከፍ ብሎ የተጠቀሰችዋ ሴትዮ ሲገርመን፣ ላሊበላ ቤተክርስቲያን ላይ ጂንስና ቢትልስ ለብሶ ኳስ የሚያነጥር ልጅ እንድ ቀን እናይ ይሆናል፡፡
(ከደራሲ መስፍን ሀብተማርያም
“የቡና ቤት ሥዕሎች እና ሌሎችም ወጎች”
መፅሃፍ ላይ የተቀነጨበ)

* * *


😂😂አንዱ ገበሬ የዘራቸዉን
አትክልትና ፍራፍሬ ሲደርሱ
ሁሌ
እዛዉ ማሳዉ ዉስጥ ቁጭ
ብሎ ይበላል
፡ በዚህ ድርጊቱ የተገረመዉ
ጎረቤቱ ለምን እንዲ
እንደሚያረግ
ልጠይቀዉ ይልና ይጠይቀዋል

ጎረቤት :-ቁጭ ብለህ ከምትበላቸዉ ለምን
አትሸጣቸዉም?

ገበሬዉ :- ከዛስ?

ጎረቤት :- ከዛ በምታገኘዉ ብር እርሻህን ታስፋፋበታለህ

ገበሬዉ :- ከዛስ?

ጎረቤት :-ከዛ የተሻለ ገንዘብ
ታገኝበታለህ ፡
ገበሬዉ :- ከዛስ?

ጎረቤት :- ከዛ ወደ ኢንዱስትሪ
ትሸጋግራለህ
፡ ገበሬዉ :- ከዛስ?

ጎረቤት :- ከዛማ ቁጭ ብለህ
ትበላለህ

ገበሬዉ :- አሁንስ ምን እያረኩ ነዉ ታዲያ ? 😂



Показано 20 последних публикаций.

196

подписчиков
Статистика канала