እንኳን ለጾመ ኢየሱስ በሰላም አደረሳችሁ !!!
ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በድርሳነ ጾም ላይ ሲመክር እንዲህ ይላል፡-ነገር ግን ዐስበ ጾም ሲባል ከመባልዕት በመከልከል ብቻ እንደሚገኝ አድርጋችሁ አታስቡ፡፡ እውነተኛ ጾም ማለት ከእኩያትም መራቅ ነውና፡፡ የበደልን እስራት ፍታ፤ ወዳጅህ ባስጨነቀህ ጊዜ ዕዳውን ተውለት፤ ጠብንና ክርክርን ለማድረግ አትጹም እንዲል፡፡ የጥሉላት ምግቦችን አትበላም፤ ወንድምህን ግን ትበላዋለህ፡፡ ወይንን ከመጠጣት ርቀኻል፤ ሌሎች ሰዎችን ከመውቀስ ግን አልተቈጠብህም፡፡ እስከ ሠርክ ጊዜ ከምግበ ሥጋ ተከልክለህ ትውላለህ፤ ነገር ግን ጊዜህን በፍርድ ቤት ትጨርሰዋለህ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር የሚቀበለውንና እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ጾም እንጹም፡፡ እውነተኛ ጾም ማለት ከእኩያት መራቅ፣ አንደበትን መቈጣጠር፣ ከቍጣ መከልከል፣ ሐሜትን ከመውደድና የሐሰት ቃልን ከመናገር እንዲሁም በሐሰት ከመመስከር መለየት ነውና፡፡ እውነተኛ ጾም ማለት እነዚህን ከማድረግ መራቅ ነው፡፡(ቅዱስ ጎርጎርዮስ፣ በእንተ ጾም ) ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጾም በጸሎት፣ በአቂበ ሕዋሳት መፈጸም እንዳለበት፣ ሕዋሳትን በመሰብሰብ ራስን በጾም መቀደስ ከእግዚአብሔር በረከት እንደሚያመጣ ያስረዳል፡፡
መልካም የጾም የጸሎት ጊዜ ይሁንልን !!!
@Ewntegna