ልሳነ ግእዝ ⛪️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


📚 ከዚህ ቻናል የግእዝ ቋንቋ ይማራሉ ማጣቀሻ መጻሕፍት እንለቃለን ።

YouTube 👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow

Ads
https://telega.io/c/geeztheancient

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ስንክሳር ዘወርኀ የካቲት ፩

📋 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተባረከ የየካቲት ወር መዓልቱ ዐሥራ አንድ ሰዓት ነው፤ ከእንግዲህም ይጨምራል።

📋 በዚችም በየካቲት አንድ የከበሩ የመቶ ሃምሳ ኤጲስቆጶሳት የአንድነት ስብሰባ በቍስጥንጥንያ ከተማ በታላቁ ቴዎዶስዮስ ዘመነ መንግሥት ተደረገ።
ስብሰባቸውም የሆነው በቍስጥንጥንያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት ስለ ሆነው የክብር ባለቤት የሆነ መንፈስ ቅዱስን በከፋች ኀሳቡ ፍጡር ነው ብሎ ስለ ካደው ስለ መቅዶንዮስ ፤
ሁለተኛም አንድ ገጽ ስለሚሉ ስለ ሰባልዮሳውያን ፤
ሦስተኛ ወልድ ለብቻው ሥጋ በቀር ነባቢት ለባዊት ነፍስን አልነሣም መለኮቱ በነፍስና በልቡና ፈንታ ሆነው ስለሚሉ ስለ አቡሊናርዮሳውያን ነው። የእሊህ ከሀድያንም ስሕተት ግልጽ በሆነ ጊዜ አሰባስቦ የአንድነት ጉባኤ ያደርግላቸው ዘንድ ንጉሥ ቴዎዶስዮስን ለመኑት እርሱም ቃላቸውን ተቀብሎ ወደ ሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ኢየሩሳሌምም ኤጲስቆጶስ ወደ እስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳትም መልእክትን ላከ ምሁራን የሆኑ ኤጲስቆጶሶቻቸውንም ይዘው እንዲመጡ አዘዛቸው። እሊህም አባቶች በቍሰጥንጥንያ ከተማ ተሰበሰቡ የሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ግን አልመጣም ምሁራን የሆኑ ሰዎችን ላከ እንጂ ከእሳቸውም ጋር በእጁ የጻፉትን ደብዳቤ ላከ። የጉባኤውም ሊቀ መንበር የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስ ነው፤ መቅዶንዮስንም ጠርቶ የረከሰች ሃይማኖቱን ይናገር ዘንድ አዘዘው ያ ከሀዲም እንደ ፍጥረቶች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ የተፈጠረ ነው አለ። ጢሞቴዎስም መልሶ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕይወቱ እንደሆነ አታውቅምን የእግዚአብሔርን ሕይወት እንዴት ፍጡር ታደርገዋለህ አሁንም ከዚች ከረከሰች ሃይማኖትህ ተመለስ ወደ ዘላለማዊ እሳተ ገሃነም ከመግባትህ በፊት ንስሓ ግባ አለው። እርሱ ግን ሰምቶ አልተመለሰም እነርሱም አወገዙት ከሹመቱም ሻሩት ከቤተ ክርስቲያንም አሳደዱት
ከዚህም በኋላ ሰባልዮሳውያንን ጠርቶ እናንተስ ስለ ሃይማኖታችሁ ምን ትላላችሁ ተናገሩ አላቸው እነርሱም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ገጽ አንድ ህላዌ ነው በምንም በምን ሦስት አይሆንም አሉ። አባት ጢሞቴዎስም መልሶ እንዲህ አላቸው በዮርዳኖስ ውስጥ ወልድ ቁሞ ሳለ በፀዓዳ ርግብ አምሳል መንፈስ ቅዱስ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ አብም ከደመና ውስጥ ሁኖ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ብሎ አሰምቶ ተናገረ ያለው የወንጌል ቃል ተሻረን። እናንተ እንደምትሉት ከሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተጠመቃችሁት የክርስትናችሁ ጥምቀት ተሽሮአል አሁንም ክህደታችሁን ተዉ ብትመለሱም ይሻላችኋል። አርዮስም አስቀድሞ ወልድን ካደው ይህ መቅዶንዮስም መንፈስ ቅዱስን ካደው እናንተም የእነርሱ ተሳታፊዎች ሆናችሁ። እነርሱም ሰምተው አልተመለሱም የአንድነት ጉባኤም አውግዞ ከምእመናን አንድነት ለያቸው ከዚህም በኋላ ደግሞ ወልድ ነባቢት ለባዊት የሆነች ነፍስን አልነሣም ሥጋን ብቻ እንጂ የሚለውን የአቡሊናርዮስን ትምህርት አወገዙ። እሊህ መቶ ኃምሳ የሆኑ ኤጲስ ቆጶሳት አባቶቻችንም በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ጌታ አዳኝ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋራ በነቢያት አድሮ የተናገረ የሚለውን ጨመሩ።
ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተስረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሣት የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ ተስፋ እናደርጋለን። ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ አባቶቻችን የተናገሩት ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እስከሚል ነው። እሊህ መቶ ኃምሳው አባቶች የተሰበሰቡት ስለ መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ስለርሱ የእርሱን ነገር አብራሩ ። ለእርሱም እሊህ መቶ ኃምሳው አባቶች የተሰበሰቡት ስለ መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ስለርሱ የእርሱን ነገር አብራሩ ። ለእርሱም ምስጋና ይሁን የአባቶቻችንም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

አርኬ
ሰላም ለክሙ ማኀበረ ኢየሱስ ኬንያ። ጉቡአን ዘቍስጥንጥንያ። ምሰለ ሰባልዮስ አብድ ለመቅዶንዮስ ሐራውያ። ታጽድፍዎ ውሳጤ ግብ ዘዕሙቅ ቀላያ። ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ኢይኪድ ባሕርያ ።

ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜት ሰማዕት
በዚችም ዕለት በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ መንግሥት ፍጻሜ በሰማዕትነት የሞተ ከሀዲ አርዮስንም ያወገዘ የሰማዕታትም ፍጻሜ የሆነ የሊቀ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ። ጻድቁ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖታትን ቤቶች ሁሉ አፈረሰ ይችንም ቤተ ክርስቲያን ከእስክንድርያ ከተማ በምዕራብ በኩል በቅዱስ ጴጥሮስ ስም አነፃት በዛሬዋም ዕለት ከበረች በውስጧም ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ። ያቺም ቤተ ክርስቲያን እስላሞች በግብጽ እስከ ነገሡበት ዘመን ኖረች ከዚያም በኋላ ቢሆን የታወቀች ሁና ትኖር ነበር ከዚህም በኋላ ፈረሰችና ምድረ በዳ ሆነች ። የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ግን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጅ የተያዘችና የተጠበቀች ናት ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

አርኬ
ሰላም ለቅዳሴ ቤትከ እንተ ሐነፅዋ ሕዝባ። ለእስክንድርያ መንገለ ምዕራባ። ጴጥሮስ ዘኮንከ ለስምዐ ሃይማኖት መክብባ። ቃል እምሰማይ ከመ ለብእሲት ነበባ። ለማኅደርከ ዘትነብር ቅሩባ።

የካቲት ፩ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
፪.ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ (ንጉሠ ቍስጥንጥንያ)

ወርኀዊ በዓላት
፩.ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ ፪.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ ፬.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፭.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

✍️ የቅዱሳንን ዝክር ከማንበብ ባለፈ በስማቸው መጸለይ (ዘፀ. ፫፪፥፲፫): በምጽዋትም ማሰብ (ማቴ. ፲፥፬፩) ይገባል። ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ተጠንቀቁ : ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ ። (ሐዋ. ፳፥፳፰)


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram




Репост из: ብራና መጻሕፍት
ጾመ ድጓ.pdf
20.0Мб
የብራና ጾመ ድጓ


📚📖
https://t.me/BiranaEthio


🤳




ሰላምታ - ፪

አይቴ ውእቱ = የት ነው?

ዳዊትተክለማርያም ሀሎ = ተክለማርያም አለ?

ሰሎሞንናሁ ወጽአ እምነ ማኅደሩ =
አሁን ከቤቱ / ከማደሪያው/ ወጣ፤

ዳዊትአይቴ ዘሖረ ይመስለከ = የት የሄደ ይመስልኻል፤

ሰሎሞንኀበ ቅድስት ማርያም ውእቱ ዘሖረ = ወደ ቅድስት ማርያም ነው የሔደው።

ዳዊትዮም ቀዳሲ ውእቱ =
ዛሬ ቀዳሽ ነው።

ሰሎሞንአኮ = አይደለም፤

ዳዊትኩለሄ ቤተ ክርስቲያን ውእቱ ዘእንበለ ቤተክርስቲያን ሊሉይ ነገር ኢየአምር።
= ሁልጊዜ ቤተክርስቲያን ነው ያለቤተክርስቲያን ሌላ ነገር አያውቅም።

ሰሎሞንውእቱሰ ኀረየ መክፈልተ ሰናየ
= እሱስ መልካም እድልን መረጠ።

ዳዊትማእዜ ይትመየጥ
= መቼ ይመለሳል?

ሰሎሞንዐሠርቱ ሰዓት ይመጽእ በድኅር ነዓ አው ንስቲት ጽንዐ እስከ አሥር ሰዓት
= አሥር ሰዓት ይመጣል በኋላና ወይም ትንሽ ቆይ እስከ አሥር ሰአት።

ዳዊትኦሆ እምዝንቱ እነብር
= እሺ ከዚህ እቀመጣለሁ።

ሰሎሞንእወ በጊዜ ውእቱ ዘይበውእ ውስተ ቤቱ።
= አዎ በጊዜ ነው ወደ ቤቱ የሚገባው።

ዳዊት፦ ምንት ነሲኦ ውእቱ ዘሖረ፤ = ምን ይዞ ነው የሔደው?

ሰሎሞንመጽሐፍ ቅዱስ ወሐመር
= መጽሐፍ ቅዱስና ሐመር።

ዳዊትአንሰ አሌ ሊተ አልብየ ተስፋ።
= እኔስ ወዮልኝ ተስፋም የለኝ።

ሰሎሞንዮጊከ ዘወድቀ ይትነሳ፤ = አይዞህ የወደቀ ይነሳል።

ዳዊትወኀልቀ ዘመንየ በከንቱ፤ = ዘመኔ በከንቱ አለቀ።

ሰሎሞንኢታማስን ተስፋከ ባሕቱ ጽንአ በሃይማኖት ወግበር ሰናየ።
= ተስፋህን አታጥፋ ነገር ግን በሃይማኖትህ ጽና፤ መልካምን አድርግ።

ዳዊትይኩነኒ በከመ ትቤለኒ፤ = እንደምትለኝ ይደረግልኝ ይሁንልኝ

ሰሎሞን
አሜን፤ = ይሁን ይደረግ።



ከመምህር ደሴ ቀለብ - ትንሣኤ ግእዝ መጽሐፍ የተወሰደ።


ሰላምታ ፩


አባ = ሰላም ለከ ወልድየ
ሰላም ላንተ ይሁን ልጄ
ሰሎሞን = እግዚአብሔር ይሴባሕ፤ ወሰላም ለከ አቡየ= እግዚአብሔር ይመስገን ላንተም ሰላም አባቴ

አባ = አብያፂከ፣ ሰብአ ቤትከ ዳኅና ውእቶሙ= ጓደኞችህ፣ ቤተሰቦችህ ደህና ናቸው?

ሰሎሞን =እወ አቡየ ሎቱ ስብሐት = አወ አባቴ ለእርሱ ምስጋና
አባ = ብከኑ መጽሐፈ ጸሎት = የጸሎት መጽሐፍ አለህ?

ሰሎሞን = እወ = አወ
አባ = ልሳነ ግእዝ እፎ ውእቱ፧ የግእዝ ቋንቋ እንዴት ነው?
ሰሎሞን = ቀሊል ውእቱ፡
=ቀላል ነው

አባ = ናሁ ትትናገር ጥቀ፧
አሁን በጣም ትናገራለህ?
ሰሎሞን = ንስቲት ንስቲት፤ ትንሽ፣ትንሽ፤
አባ = ባሕቱ ምንት ይገብር ለከ፧ ነገር ግን ምን ያደርግልሃል?

ዳዊት = ይትሔደስ መንፈስየ አመ ሰማእኩ በእዝንየ ልሳነ ግእዝ። ግእዝ ቋንቋ በሰማሁ ጊዜ መንፈሴ ይታደሳል።
አባ = እንከሰ ኩሉ ሰብእ እመይትናገር ሠናይ ውእቱ። እንግዲያስ ሁሉ ሰው ቢናገረው ጥሩ ነው።
ሰሎሞን = ተስፋየ ውእቱ፤
ተስፋየ ነው
አባ = ናሁ እለመኑ ይትናገሩ ልሳነ ግእዝ። አሁን እነማን የግእዝ ቋንቋን ይናገራሉ?
ሰሎሞን = ብዙኀን ውእቶሙ አኮ አነ ባሕቲትየ። ብዙዎች ናቸው እኔ ብቻ አይደለሁም
አባ = ምንት ትቤ አንተ እንዘ ይትናገሩ ልሳነ ግእዝ። ግእዝ ሲናገሩ አንተ ምን ትላለህ?

ሰሎሞን = ፍስሐ ፈድፈደ ሊተ። ደስታ በዛልኝ።
አባ = ማእዜ ውእቱ ዘወጠኑ ለምሂርመቼ ነው ለመማር የጀመሩ?
ሰሎሞን = በዝንቱ ዓመት፤
በዚህ ዓመት
አባ = እግዚአብሔር ያርእየነ ለፍሬሁ። እግዚአብሔር ፍሬውን ያሳየን
ሰሎሞን = አሜን ለይኩን።
አሜን ይሁንልን

https://t.me/geeztheancient


ስንክሳር አመ ፲ወ፩ ለጥር

አርኬ

ሰላምለጥምቀትከ በኍልቈ ክራማት ሠላሳ ። እምዘወለደተከ ድንግል ዘኢተአምር አበሳ ። አመ ቆምከ ዮም እግዚኦ ለዮርዳኖስ ማዕከለ ከርሣ። ለወድሶትከ ማዕበላቲሃ ተከውሳ። ወባረኩከ አናብርት ወዓሣ።

ሰላም ለጥምቀትከ በዘቦቱ ይነጽሑ ። ኃጣውአ ሰብእ ዘዘዚአሁ ። አመ ላዕሌከ እግዚኦ አእዳወ ዮሐንስ ተሰፍሑ ። ሶበ ርእዩከ ቀላያት ደንገፁ ወፈርሁ ። ማያትኒ በርእስከ ፈልሑ።

በዝንቱ በዓል ዘያሜንን ወይነ ። ወዘያረስዕ ኀዘነ ። ንዑ ንትፈሣሕ እንዘ ናረትዕ ልሳነ። ዘኢያስተርኢ ኅቡእ እስመ አስተርአየ ለነ። እሳት በላዒ አምላክነ።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቅዱስ እንጦንዮስ ሰማዕት

በዚችም ቀን ከፋርስ አገር ሰዎች ወገን የሆነ የከበረ እንጣልዮስ በሰማዕትነት ሞተ ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ በሮም አገር የሠራዊት አለቃ መኰንን ሆኖ ዐሥራ ዐምስት ዓመት ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን 🙏 አሜን።

አርኬ
ሰላም ለእንጣልዮስ ዘረሰየ ማኅሠሦ። ለእግዚአብሔር ጽድቆ ወሰማያዊተ ንግሦ። ጊዜያተ ሠላሰ እስከ መጠወ ነፍሶ። ድኅረ አውቀዩ ልሳኖ ወዘሐቁ ማዕሶ። ለፍጻሜ ስምዑ በሰይፍ መተርዎ ርእሶ።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አባ ወቅሪስ ገዳማዊ

በዚችም ዕለት የከበረ ተጋዳይ ለሆነ አባት አባ ወቅሪስ የእረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቅዱስ አባት በባስልዮስ ዘንድ አደገ እርሱም ቅስና ሾመው ይህም ቅዱስ በደም ግባቱ በላሕዩ ደስ የሚል ፊቱም የሚአምር ነበር። በቀደመው ግብሩ ወጣት ሁኖ ሳለ የሹሙን ሚስት ተመኛትና እጅግም ወደዳት እርሷም ወደደችው ወደ ሌላ ቦታ ሒደው ፍላጎታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ተማከሩ ለዚህም ነገር ሲዘጋጁ በሕልሙ ራእይን አየ። እርሱ ታሥሮ በፍርድ አደባባይ ቁሞ ነበር ሌሎችም ብዙዎች እሥረኞች ከእርሱ ጋር አሉ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸውን ይመረምሯቸው ነበር እርሱም በልቡ የታሰርኩት በምን ይሆን ባሏን ልነጥቀው ስለፈለግሁ ስለዚያች ሴት ነውን እርሱ ከስሶኝ ወደዚህ ታላቅ ግዳጅ ላይ አደረሰኝን አለ። በዚህም ነገር እየተሸበረ ሳለ በቀድሞ ወዳጁ አምሳል አንድ ሰው መጣና የታሰርከው በምንድን ነው? አለው ስለ ኃጢያቱ ስለ አፈረ ሊሰውረው ወደደ ግድ ባለውም ጊዜ እንዲህ ነገረው ወዳጄ ሆይ እገሌ ስለሚስቱ የከሰሰኝ ይመስለኛል ስለዚህም ፈርቼ እሸበራለሁ በወዳጁ አምሳል ወደርሱ የመጣው መልአክም ወዳጄ ሆይ ይህን ስራ እንዳትሰራ ወደርሱም እንዳትመለስ በቅዱስ ወንጌል ማልልኝ እኔም ዋስ እሆንሀለሁ አለው በወንጌልም ማለለት በዚያንም ጊዜ ከእንቅልፉ ነቃ ያየው ራእይም እውነት እንደሆነ አወቀ ። ስለዚህም አገሩን ትቶ ወደ እስክንድርያ ሔደ በዚያም ስሟ ኄራኒ የሚባል እግዚአብሔርን የምትፈራ አንዲት ሴት አገኘ በተነጋገሩም ጊዜ የልቡን ሁሉ ነገራት እርሷም እነዚህን ያማሩ ልብሶችህን ተው ተርታ ልብስንም ለብሰህ እግዚአብሔርን አገልግለው አለችው። ከዚያም ወደ በርሀ ሔደ ከብዙ ተጋድሎ የተነሳ ሆዱ እንደ ድንጋይ እስከ ደረቀ ድረስ ቅጠላቅጠል እየበላ ኖረ ጌታችንም ወደርሱ መጥቶ ፈወሰው። አጋንንትም ስለሚፈታተኑትና ስለሚያሰቃዩት እርሱ በጾምና አጋንንትም ስለሚፈታተኑትና ስለሚያሰቃዩት እርሱ በጾምና በጸሎት በመጋደል በክረምት ዝናብ እየወረደበት ራቁቱን ቁሞ ያድራል በበጋም በቀን የፀሐይ ትኩሳት በሌሊትም ቁር ሰማያዊ ሀብት እስከተሰጠው ድረስ መላዕክትም ወደርሱ መጥተው ሰማያዊ ኅብስትን ሰማያዊ መጠጥን ይመግቡት ነበር ። የተሰወሩ ራእዮችን ያውቅ ዘንድ ተገባው ሶስት ድርሰቶችንም ደረሰ አንዱ በበረሀ ስለሚኖሩ ሁለተኛው በአንድነት ስለሚኖር መነኮሳት ሦስትኛው ስለካህናት ነው ። በአንዲት አለትም ስሙ ቡላ የሚባል ገዳማዊ ወደርሱ መጥቶ እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ አባ ብላም እንዲህ አለው ወንድሜ ወቅሪስ ሆይ በቻህን አትሁን ጥቂት ወንድሞችን ካንተ ጋር አኑር እንጂ ያረጋጉህ ዘንድ ከሰይጣንም ጦርነት እንድትድን እንዲሁም አደረገ ።
ከዕለታትም በአንዱ ሃይማኖትን በለወጡ በአርዮስ በንስጥሮስና በማኒ አምሳል ሆነው ሦስት ሰይጣናት ወደርሱ መጥተው በሃይማኖታቸው ተከራከሩት እርሱም በቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትና ሃይማኖታቸው በቀናች አባቶች ትምህርት ረታቸውና አሳፈራቸው ። ብዙዎችም የሆኑ ድንቆች ተአምራቶችን የሚሰራ ሆነ በአንዲትም እለት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሔደ ጊዜ ተዘግታ አገኛት መነኮሳቱም መክፈቻ ፈልገው አላገኙም በላይዋም በአማተበ ጊዜ በሩ ተከፈተለት ። አባትህ ሞተ ብለው በነገሩት ጊዜ ዋሽታችኋል አባቴስ የማይሞት ሰማያዊ ነው አለ ተብሎ ስለርሱ የሚነገርለት ወቅሪስ ይህ ነው ዜንውም በገድሉ መጻሐፍና የአባቶች ዜና በተጻፈበት መጻሐፍ አለ ። ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ሔደ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

አርኬ
ሰላም ለወቅሪስ እንተ ርእየ በንዋም። እንዘ ውእቱ እሙረ ከዊኖ በዓውደ ምኵናን ቅውም። ሶበ ተኀይጠ ለብእሲት በስነ ላሕያ አዳም። ከመ ያድኅን ነፍሶ በአውትሮ ጸሎት ወጾም። ነዋኀ ተናከራ ለዛቲ ዓለም።

ሰላም እብል በቃለ ሐሤት ወፍሥሓ። እንዘ እጼውዕ ስመከ ሠርከ ወነግሀ። ዮሐንስ ሰባኪ ጥምቀተ ለንስሓ። ኅፅበኒ ወአንጽሐኒ እስመ አባልየ ረስሐ። በማየ ዮርዳኖስ ዘኵሎ አንጽሐ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አምላከ ቅዱሳን በጥምቀቱ ይቀድሰን። ከበረከተ ጥምቀቱም ያድለን።

ጥር ፲፩ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.በዓለ ኤዺፋንያ
፪.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፫.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
፬.አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
፭.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት
፮.ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት


ኤጲፋንያ በዘቦቱ አርአየ እግዚእ ስብሐተ መለኮቱ በውስተ ጥምቀት በቅድመ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ።


እንኳን አደረሳችሁ




እንቋዕ ለበዓለ ከተራ በሰላም አብጽሐክሙ/ን ❤🙏😍


🥁🪘🪈


መዝሙር ዘሰንበት

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ፤ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አሕዛብ፤ ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ፤ አርአዮሙ ስብሐቲሁ አምኑ ቦቱ አርዳኢሁ፤ ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ፤ ወይቤሎሙ ቅድሑ ማየ ወምልዕዎን ለመሳብክት እስከ አፉሆን፤ ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ፤ ጥዒሞ አንከረ ሊቀ ምርፋቅ በረከተ ዘአምላክ ገብረ፤ ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ፤ ቤዛነ ተስፋነ ወልደ አምላክ፤ ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ።


+++ ማኅሌት ዘበዓለ ጥምቀት ምስለ ዘቃና ዘገሊላ +++                                                                    
📖  ከአባቶቻችን ጋር የምስጋና ቃል ጋር አንድ ሆነን ለምስጋና እንተጋ ዘንድ፤ ለማኅሌቱም እንግዳ እንዳንሆን እነኋት እንደ ረዳት ትሆነን ዘንድ ከመጽሐፈ ዚቅ የተቀዳውን በሚከተለው ቀርቧል፡፡ መድረኩን ከማኅሌቱ ጋር ለማዋሐድም መድረክ አካባቢ ለሚያገለግሉ ነገር ግን መጽፉን ለመመልከት ላላደረሳቸውም ለማስታወስ ያህል . . .

#ዋዜማ
ሃሌ ሉያ ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን ወተስፋ ቅቡጻን፤
ክርስቶስ አስተርአየ ውስተ ዓለም፤
እምድንግል ተወልደ ክሡተ ኮነ፤
እንዘ ይትዔዘዝ ለአዝማዲሁ፤
ከዊኖ ሰብአ በዮርዳኖስ ተጠምቀ ፡፡
+++
++
#በሐምስተ ++
በዮርዳኖስ ተጠምቀ ፈጺሞ ሕገ፤
ወአስተርአየ ገሃደ በዮርዳኖስ ተጠምቀ፡፡

++ እግዚአብሔር ነግሠ ++

አስተርእዮ ኮነ ዘክርስቶስ ስነ መለኮት፤
ከመ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ፡፡
+++
#ይትባረክ +++
ርእዩከ ማያት እግዚኦ
ርእዩከ ማያት ወፈርሁ፤
ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምፀ ማያቲሆሙ፡፡

++
#ሠለስት++
አርአየነ ፈቃዶ በከመ ሥምረቱ ለአምላክነ፤
ወረደ ወተወልደ እምብእሲት፤
ወአንሶሰወ ዲበ ምድር ወአስተርአየ ከመ ሰብእ በበህቅ ልህቀ፤
በሠላሳ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ፡፡
++
#ሰላም ++
ሃሌ ሉያ (4) በሰላም አስተርአየ ወልደ አምላክ ፍጹም፤
ወተወልደ በሀገረ ዳዊት በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይቤዝወነ ፤
ወልደ አምላክ ፍጹም አስተርአየ፡፡
++
#ክብር ይእቲ ++
ኵሎሙ ማኅበረ መላእክቲሁ ይሴብሑ ወይዜምሩ፤
ለዘበሥጋ ሰብእ አስተርአየ ፤
ንዑ ንስግድ ሎቱ ሃሌ ሉያ፡፡

++
#ዝማሬ ++
ኅብስተ ሰማያዌ ወጽዋዓኒ ዘማየ ሕይወት፤
ጠዓሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ፡፡

++# ዕጣነ ሞገር ++
ሃሌ ሉያ (2) ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ
ወማየ መንጽሔ ዚአነ፡፡
++
#ሰላም ++
ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት፤
በፍሥሐ ወበሰላም፡፡

#ምልጣን
በፍሥሐ ወበሰላም፤
ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት፡፡
++++

+++
#ማኅሌት +++
ሰላም ለአእዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ፤
ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘኢተልዎ ርእይ
. . . . .
ዚቅ
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ ክርስቶስ ውእቱ ዘወጽአ እማይ፤
እመንፈስ ቅዱስ ሠለስቲሆሙ እለ አሐዱ እሙንቱ ሠለስቲሆሙ፤
እለ ይከውኑ ሰማዕት ሠለስቲሆሙ፤
ለሊሁ ወረደ መንፈስ ቅዱስ ከመ ይቀድስ ማያተ፤
ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤
ጸጋ ወጽድቅሰ በኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ፡፡

++
#ነግሥ ++
ሰላም ለማየ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ዘአተቦ፤
መንፈስ ቅዱስ ከመ አጥበቦ፤
ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ፤
ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ፤
ማይ ኀበ የሐውር ጸበቦ፡፡
ዚቅ
ርእዩከ ማያት እግዚኦ
ርእዩከ ማያት ወፈርሁ፤
ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምፀ ማያቲሆሙ፡፡

+++
#ትምህርተ ኅቡዓት +++
እምሰማያት እም ኀበ አብ አይኅዓ፤
በሕማማተ ሥጋሁ ቤዘወነ ፤
ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት፤
ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ፤
ወማየ መንጽሔ ዚአነ፡፡

አልቦ ዚቅ ፡- (እንደ ሚታወቀው ይህ ትምህርተ ኅቡዓት ጌታ ከትንሣኤው በኋላ ከዕርገቱ በፊት በነበሩት ፵ ቀናት ውስጥ ለሐዋርያት ያስተማረው ትምህርት ነው፡፡ ጌታ ባስተማረው ትምህርት ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት አይገባም በሚል ዕሳቤ ትምህርተ ኅቡዓት በሚቆምበት ወቅት ዚቅ እንዳይኖረው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ደንግገዋል። )

++
#ምልጣን ++
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ፤
ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ፤
እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤
አማን መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ፡፡
++ እስመ ለዓለም ++
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ ፤
ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፤
ወወጺኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ፤
መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ፡፡

++
#ዕዝል ++
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ቃለ እግዚአብሔር፤
ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ ወተገሠ በሥጋ መንፈስ ዘኢይትገሠሥ፤
ወዘኢይትለከፍ ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት
ወገብረ መንጦላዕተ ፡ ሥጋ ሰብእ መዋቲ
ወረደ ዲበ ምድር ወአንሶሰወ ውተ ዓለም
በበሕቅ ልሕቀ በሠላሳ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ፡፡

++
#ምልጣን ዘዕዝል ++
ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት
ወገብረ መንጦላዕተ ፡ ሥጋ ሰብእ መዋቲ ፡፡
++
#አቡን ++
ሃሌ ሉያ (5) እስመ ስምዓ ይቀውም ሎቱ አብ ናዛዜ፤
በርእየተ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር
ዘኪያሁ ሠመርኩ ይቤ፤ ወለይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ መድኅን እምቅድስት ድንግል
ኪያሃ ሠምረ አብ በሥጋ ምጽአቶ፡፡
++
#ሰላም ++
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ ወበእንተ ጥምቀቱ፤
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ኃዲጎ ተስዓ ወተስዓተ ነገደ፤
ቆመ ማእከለ ባሕር ገብአ ወወጽአ በሰላም፡፡

+++++++++++++++++++++++++++++++
#ዘቃና ጥር 12
ሥላሴክሙ ሥላሴ ይረስየኒ መካነ፤
ድኅረ ተዋሐድኩሰ ዘሥላሴሁ ብርሃነ፤
ዮርዳኖሰክሙ ዝየ እስመ ኵለንታየ ኮነ፤
ኢየኃሥሥ እምዮርዳኖስ ሰማዕተክሙ ምእመነ ፤
ወኢይትሜነዮ ለታቦር እስመ ታቦር አነ፡፡
ዚቅ
ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ፤
እማርያም ዘተወልደ አፍቂሮ ኪያነ መጽ ኀቤነ ዘነቢያት ሰበኩ ለነ፤
በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይፈጽም ኵሎ ሕገ ወአስተርአየ ገሃደ፡፡

++ #መልክዐ ሚካኤል ++
ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ፤
ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ፤
ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ፤
ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ፤
አልቦ እምሰብእ ዘየኀድግ ሱታፎ፡፡
ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ዘበተዋህዶ ይሴለስ
እምኀበ አብ ትጉሃን ይትቄደስ
እሳተ ሕይወት ዘኢይተገሠሥ ወኢይጤየቅ ለዓይን ረቂቅ መንፈስ
ንሰግድ ለትሥልስቱ አሐተ ስግደተ ወሎቱ ናቄርብ ስብሐታተ፡፡


©Aleph ቴሌግራም ቻናል ላይ የተወሰደ።


እንቋዕ አብጽሐክሙ/ን ውሉደ ኢትዮጵያ።


የጊዜ አመልካቾች

ትካት፣ ዐለም - ድሮ፣ ጥንት፣ ቀድሞ - Old times
ዘልፍ ወትር፣ ዘልፈ ወትረ - ወትሮ፣ ዘወትር ያለማቋረጥ
ለዝሉፍ፣ ለዝላፋ - ለወትሮ፣ ለዘወትር፣ ለዘላለም
ቅድም፣ ትማልም - መጀመሪያ - In the Beginning
ትማልም - ትላንት - Yesterday
ቅድመ ትማልም - ከትናንት በስቲያ/ወዲያ - Before yesterday
ዮም፣ ይእዜ - ዛሬ፣ አሁን፣ ዘንድሮ - Today, Now, This year
ናሁ - አሁን - Now
ጌሠም፣ ሳኒታ - ነገ፣ ነገታ፣ ማግስት - Tomorrrow
ድኅረ ጌሠም - ከነገ በስቲያ - After tomorrow
ቅድመ ዝ ዐመት - ከዚህ ዓመት በፊት - Before this year/last year
ዘዮም ዐመት - የዛሬ ዓመት - Year after now/next year
ሣምንት - ሣምንት - week
ዘልፈ፣ ወትረ - ዘወትር - Every day
ለለ/በበ ዕለቱ - ዕየለቱ - Every day
ዋሕድ ዋሕድ ጊዜ - አልፎ አልፎ - Some times
ወርኅ - ወር - Month
ዘዮም ወርኅ - የዛሬ ወር - A month before or after now
ዐመት - ዓመት - Year
ዕለት፣ መዐልት - ቀን - Day
ጽባሕ - ጧት - Morning
ቀትር - ቀትር - After noon
ክ.ዘመን - ክ.ዘመን - Century
ሺሕ - ሺሕ - Millenuiem
መንፈቀ ሌሊት - የሌሊት ግማሽ - Mid night
ቀዳማይ መንፈቅ - የመጀመሪያ ወሰን - First Semester
ካልኣይ ወሰን - የኹለተኛው ወሰን - Second semester


#ልሳነ #ግእዝ #Ge'ez #Language

ገቢር ተገብሮ = አድራጊ ተደራጊ / Direct and indirect Object/

✍️ ገቢር/ አድራጊ /፣ ተገብሮ /ተደራጊ/ ማለት የማይሸጋገሩትንና የሚሸጋገሩትን ግሶች የምንለይበት ሰዋስዋዊ ሙያ ነው፡፡

የሚሻገሩ ግሶች /Transitive Verbs /፦ ማለት ከባለቤቱ ወይም ከድርጊት ፈጻሚው ድርጊቱን በማሳለፍ በድርጊት መፈጸሚያው ላይ ማረፉን የሚያመለክቱ ግሶች ናቸው።
ለምሳሌ፦ አበበ አንበሳ ገደለ፤ ብንል "ገደለ" የሚለው ግስ አበበ የተባለው የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት በአንበሳው ላይ ድርጊት መፈጸሙን የሚጠቁም ስለሆነ ነው። ነገር ግን አንበሳ ተገደለ ብንል ድርጊቱ እዚያው አንበሳው ላይ ብቻ መቅረቱን እንጂ ከማን ወደ ማን መኼዱን የሚያመለክት አይኾንም።

የማይሻገሩ ግሶች /Interansitive Verbs በተገብሮ/ passive ይነገራሉ። ነባር አንቀጽና የማለት አንቀጾች የማይሻገሩ አንቀጾች ናቸው።

ገቢር/ተሻጋሪ----ተገብሮ/የማይሻገሩ

አቅረበ - አቀረበ ------ ሞተ - ሞተ
ጸፋአ - መታ ------- ነበረ - ተቀመጠ
ሰበረ - ሰበረ -------- ሖረ - ኼደ
አኀዘ - ያዘ -------- ቆመ - ቆመ
አንበረ -አስቀመጠ
አጥረየ - ገዛ

✍️ ተሻጋሪ ግስ ያለበት ቃል ተሳቢን ያስከትላል።

ምሳሌ
የማይሳቡ - Indirect ☑️ የሚሳቡ - Direct ☑️
እምከ - እናትኽ እመከ - እናትኽን
እምኪ - እናትሺ እመኪ - እናትሽን
ወልድከ - ልጅኽ ወልደከ - ልጅኽን


✍️ ተሻጋሪ ግሶች
ምሳሌ፣ ቀተለ/ገደለ/፣ ቀደሰ / አመሰገነ/፣ በልሀ /በላ/ እናም ሲተረጎም “ን” የሚለውን ትርጉም ያመጣል፡፡
ረከብነ ሕይወተ = ሕይወት አገኘን ሲሆን በግእዝ ግን
ተረክበ ሕይወተ = ሕይወት ተገኘ ቢል ግን አይለውጥም /ስሕተት የለበትም/ ምክንያቱም ተረክበ ተቀተለ እና የመሳሰሉት ተገብሮ/ የማይሻገሩ ናቸውና፡፡

ምሳሌ
ባለቤት /ተገብሮ/ (subject)

ዝ ቤት ሐዲስ ውእቱ -- ይህ ቤት አዲስ ነው፤
ተወልደ ለነ -- ተወለደልን
ተሰቅለ ለነ -- ተሰቀለልን
ሖረ ኀበ ገዳም -- ወደ ገዳም ኼደ።

ተሰብረት ሐመርየ ውስተ ባሕር - መርከቤ በባሕር ውስጥ ተሰበረች።

ቀረብከ አንተ ኀበ እሳት - ወደ እሳት ቀረብክ።
መጽአ ብየ ከይሲ - እባብ መጣብኝ
እነዚህ ከላይ ያየናቸው የማይስቡ/የማይሻገሩ ናቸው።

✍️ ተሳቢ / ገቢር/ (direct object)

ምሳሌ
ወልድየ ሐነፀ ቤተ = ልጄ ቤትን ሠራ፤
ወለደት ወልደ ማርያም -- ማርያም ልጅን ወለደች፤
አንተ ሰበርከ ሐመረ - አንተ መርከብን ሰበርክ።
አቅረበ ለነ ማየ - ውኃን አቀረበልን።
መኑ ሰቀለ ወልደኪ፧ -- ልጅሽን ማን ሰቀለው?
አነ ቀተልኩ ከይሴ - እባብን ገደልኩ፤
ከላይ ያየናቸው የሚስቡ/ የሚሻገሩ ናቸው።

📖 ለማጠቃለል የሚከተሉት ሕግና ሥርዓት አሉት።

1. ከላይ እንዳየነው የመጨረሻው ሳድስ ፊደል ወደ ግእዝ ይለወጣል፡፡
ቤት = ቤተ ይሆናል፡፡

2. ካእብ ወደ ሳብእ ይለወጣል፡፡ ኩሉ= ኩሎ ይሆናል፡፡
ወሖረ ኩሉ ኀበ ቤቱ - ሁሉ ወደ ቤቱ ሄደ።
እግዚአብሔር ያፈቅር ኩ - እግዚአብሔር ሁሉ ይወዳል።

3. ሳልስ ወደ ኀምስ ይለወጣል፡፡ ብእ--- ብእ
ዊ=ዌ ይሆናል፡፡

☑️ ተገብሮ =ብእሲ ሖረ ኀበ ሐቅል
☑️ገቢር =ርኢኩ ብእሴ ውስተ ቤተ

☑️ ተገብሮ = አቤሜሌክ ኢትዮጵያዊ ውእቱ።

☑️ ገቢር = ወባረከ እግዚአብሔር ውእተ ኢትዮጵያዌ - እግዚአብሔር ኢትዮጵያዊውን ባረከ።

4. የተጸውኦ ስሞች
ምሳሌ ሲጨምር፡፡
ሙሴ = ሙሴሃ ይሆናል።



ተለውነ ✍️
https://t.me/geeztheancient


ትእዛዝ፡፵ወ፰ ።
በእንተ፡ዘኢይጸውም፡ጾመ፡አርብዓ፡ወረቡዕ፡ወዐርብ። ኤጲስ፡ቆጶስ፡አው፡ቀሲስ፡አው፡ዲያቆን፡አው፡አናጕንስጢስ፡አው፡መዘምር፡ለእመ፡ኢጾመ ፡ አርብዓ ፡ ቅዱሰ፡ወረቡዕ፡ ወዐርበ፡ይሰዐር፡ለእመ፡ኢከልኦ፡ሕማም፡ዘሥጋ። ወለእመ፡ኮነ፡ሕ ዝባዊ፡ይሰደድ።

ትእዛዝ፡፵ወ፱ ። ለእመ ፡ ጾመ ፡ ኤጲስ፡ ቆጶስ፡ አው፡ቀሲስ፡ አው፡ዲያቆን፡ አው፡፩እምሥዩማን፡ምስለ ፡አይሁድ፡ወይገብር፡ ፋሲካ፡ምስሌሆሙ፡አው፡ይትወከፍ፡በኀቤሆሙ፡አምኃ፡በዓሎሙ፡ ናእተ፡አው፡ዘይመስሎ፡ይሰዐር፤ ወለእመ ኮነ፡ሕዝባዊ፡ይሰደድ። ሕዝባዊ፡ለእመ፡ወሰደ፡ኀበ፡ምኵራበ ፡ አሕዛብ ፡ ወምኵራበ ፡ አይሁድ፡ቅብአ፡ወማኅቶተ፡ይሰደድ።


ትእዛዘ ሐዋርያት
ገጽ ፳፪


ዝ መጽሐፈ ግእዝ ጥቀ ሠናይ ውእቱ




Репост из: ብራና መጻሕፍት
Ethiopian_Geez_1300_ca_Krestos_Gospels_Illuminated_WDL_13018.pdf
74.4Мб
ከነጮቹ ዌቭሳይት የተገኘ ነው።
እዚህ ይቀመጥ።

https://t.me/BiranaEthio

Показано 20 последних публикаций.