ስርአት!
(የሞገሤ ልጅ)
አንተ የእኔ ምትክ፣
የእራሴ መታያ የአብራኬ ክፋይ፣
እንኳንም ወለድኩህ፣
የፈጠረህ ፈቅዶ ዐይኔን በዐይኔ እንዳይ።
አንተ ግን ቸኩለህ፣
መልሰህ መሄድህ ወደመጣህበት፣
ምን ሰይጣን መክሮህ ነው፣
ያረከኝ በሃዘን እንድኮረማመት።
የውልህ ልንገርህ፣
ተወልዶ ማረፉ በሰላሳኛ ቀን፣
ላንተም ኪሳራ ነው፣
ለኔም የእድሜ ልክ ስብራት ሰቀቀን።
ያንተን ጉዳት ላርዳህ፣
ለገነት ከሆነ ሞትህ በዚህ እድሜ፣
እኔም አልገባሁም፣
ካንተ በላይ ኖሬ 55 ቀን ጾሜ።
By @tafachgitm
@getem
@getem
@getem
(የሞገሤ ልጅ)
አንተ የእኔ ምትክ፣
የእራሴ መታያ የአብራኬ ክፋይ፣
እንኳንም ወለድኩህ፣
የፈጠረህ ፈቅዶ ዐይኔን በዐይኔ እንዳይ።
አንተ ግን ቸኩለህ፣
መልሰህ መሄድህ ወደመጣህበት፣
ምን ሰይጣን መክሮህ ነው፣
ያረከኝ በሃዘን እንድኮረማመት።
የውልህ ልንገርህ፣
ተወልዶ ማረፉ በሰላሳኛ ቀን፣
ላንተም ኪሳራ ነው፣
ለኔም የእድሜ ልክ ስብራት ሰቀቀን።
ያንተን ጉዳት ላርዳህ፣
ለገነት ከሆነ ሞትህ በዚህ እድሜ፣
እኔም አልገባሁም፣
ካንተ በላይ ኖሬ 55 ቀን ጾሜ።
By @tafachgitm
@getem
@getem
@getem