ዳሽን ባንክ እና ኤም-ፔሳ ሳፋሪኮም ዓለም አቀፍ ሃዋላን የሚያዘምን አገልግሎት በጋራ አስጀመሩ
ተቋማቱ ለዓለም አቀፋ የሀዋላ አገልግሎት ካሽ ጎን እንደሚጠቀሙም ዛሬ ስምምነት ባደረጉበት ወቅት ተናግረዋል።
ስምምነቱ፤ ኢትዮጵያዊያን ከውጭ በቀጥታ በካሽ ጎ ሞባይል አፕልኬሽን አማካይነት ወደ ኤምፔሳ ገንዘብ የሚላክበትና መቀበል የሚቻልበትን ዕድል የሚፈጥር እንደሆነም ተነግሮለታል፡፡
ዛሬ ይፋ የተደረገው ስምምነት፤ የሐዋላ ገንዘብ ልውውጥን አስተማማኝና ቀልጣፋ የሚያደርግ ነው ሲሉ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና ቺፍ ሬቴይል እና ኤም ኤስ ኤም ኢ ኦፊሰር አቶ ይህንዓለም አቅናው አስረድተዋል።
የኤም-ፔሳ ሳፋሪኮም በመወከል በመድረኩ ንግግር ያደረጉት፤ ኤልሳ ሙዞሊኒ ስምምነቱ የፋይናንስ አካታችነትን የሚያበረታታና አዳዲስ የዲጂታል የፋይናንስ መፍትሄዎችን ለማቅረብ ተጨማሪ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።
ይህን አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞች ከዛሬ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት ከውጭ ሀገራት ገንዘብ ሲልኩ በዕለቱ ካለው ምንዛሪ የ10 በመቶ ተጨማሪ ጉርሻ እንደሚያገኙ በመድረኩ ሲነገር ሰምተናል፡፡