GhionMagazine ግዮን መጽሔት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


https://t.me/+kQKnGzeZl1IyZmZk
በኢትዮ ሐበሻ ሕትመትና ማስታወቂያ ኃ/የ/ግ/ማ ሥር ታተመው ለንባብ የሚበቁት ግዮን መጽሔት እና ኢትዮ ሐበሻ ጋዜጣ የቴሌግራም ቻናል ነዉ።
ዕለታዊ ትኩስ ዜናዎች
ፖለቲካዊ፣ ዘገባዎች
ሃይማኖታዊና ባህላዊ
ማኅበራዊና፣ ኢኮኖሚያዊ
ኪናዊ ይዘት ያላቸው ጽሑፎች በስፋት ይስተናገዱበታል፡፡https://t.me/+kQKnGzeZl1IyZmZk
በተጨማሪም፡-

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


" ይሄንን ፍትሃዊ ምርጫ ነው ብዬ አልቀበልም "
አቶ ዱቤ ጅሎ


በዛሬ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኘሬዝደንት ምርጫ የተሸነፉት አቶ ዱቤ ጅሎ የምርጫውን ሂደት እና ውጤት አጣጥለውታል።

ከምርጫው በኋላ ለሃትሪክ ስፓርት አዘጋጅ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ
የተከበሩ ዱቤ ጁሎ በተለይ ለሀትሪክ ምርጫውን ፍትሃዊ አይደለም ፥ ደባ ተሰርቷል ብለዋል።

በቃለ መጠይቃቸው የሚከተሉትን ብለዋል ፦

👉በሀገር ላይ ከፍተኛ ደባ እየተሠራ ነው፤እኔ ይሄንን ፍትሃዊ ምርጫ ነው ብዬ አልቀበልም

👉ምርጫው ፍትሃዊ አይደለም

👉 ምርጫው ያለቀለት ነው ወደ ጉባኤው አትሂድ ተብዬ ነበር፤ በጉባኤውም የገጠመኝ ይኸው ነው

👉ሌላው ቢቀር የወከለኝ ክልል እንዴት አንድ ድምፅ ይነፍገኛል፤ይሄ ራሱ የምርጫውን ፍትሃዊ አለመሆን ያሳያል


ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነ

አትሌት ስለሺ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆኖ የተመረጠው ፌዴሬሽኑ ባደረገው 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ ነው።

በዚህም አትሌት ስለሽ ለቀጣይ 4 ዓመታት ፌደሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ይሆናል።

በምርጫው፣ ከስድስት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የቀረቡ ዕጩዎች ተሳትፈዋል ተብሏል።

አትሌት ገ/እግዜአብሄ ገ/ማሪያም፣ አቶ ዱቤ ጅሎ ፣ ወ/ሮ ሪሳል ኦፒዮ፣ ኮማንደር ግርማ ዳባ እና አቶ ያየ ሀዲስ በምርጫው ተወዳዳሪ ነበሩ።

አትሌት ስለሺ ስህን በምርጫው የተመረጠው ከኦሮሚያ ክልል ተወከሎ በመወዳደር ነው።

አትሌቱ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ማገልገሉ ይታወቃል።

ያለፉትን 4 ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝደንትነት ለመራቸው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ሽልማት ተበርክቶላታል።

ከሸገር 102.1


የአሜሪካው ' ስታርባክስ / Starbucks ' ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ናቸዉ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ እና የUSAID ዳይሬክተር ሆክላንደር ለበርን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አሜሪካ በኤምባሲዋ በኩል የስታርባክስን አመራር " እንኳን ወደ ኢትዮጵያ፤ ወደ ቡና መገኛዋ ሀገር በደህና መጡ " ብላለች።

የስታር ባክስ አመራር ሚሼል በርን በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላለው አስደናቂ እድገት፣ በምርታማነት ላይ ስላሉ ኢንቨስትመንቶች ይመክራሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ በተመለከተ ይወያያሉ።

ስታር ባክስ (starbucks) በቡና አቅርቦቱ በመላው ዓለም የሚታወቅ ከፍተኛ ሃብት ያለው ኩባንያ ነው።

@tikvahethiopia


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት 22 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተደረገበትንና ከ 1,300 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ለበረራ ሙያ ባልደረቦች የተገነባ ባለ 8 ወለል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ  ለምረቃ አበቃ።

ይህ በ48,000 ስኩዌር ካሬሜትር ላይ ያረፈ እጅግ ዘመናዊ ህንፃ በአንድ አመት ከአንድ ወር ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን በውስጡም ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነ፣ በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ የተገጠመለት፣ እንዲሁም ድንገተኛ የእሳት አደጋን መቋቋም እንዲያስችል ተደርጎ በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ የተገነባ ነው።

ይህ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ህንጻ  ቻይና ጂያንግሱ በሚባል ህንጻ ተቋራጭ ድርጅት እና K2N አርክቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ አማካሪ ድርጅት የተገነባ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የቻይና ጂያንግሱ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር ባሻገር የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት በ2ኛ ዙር የቤት ግንባታ ፕሮግራም ለ5000 ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በአርጀንቲና የተቀረፀው ቀኑን ወደ ጨለማ የቀየረው አዋራ ያዘለው ንፋስ


አሜሪካ የራሷን የጦር ጀት ቀይ ባህር ላይ መታ ጣለች
የአሜሪካ ባህር ሀይል  የራሱን F/A -18 ተዋጊ ጀት መቶ መጣሉን የአገሪቱ  መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን ) አሳውቋል፡፡
በየመን የሁቲ ይዞታዎች ናቸው በተባሉ ስፍራዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው F/A 18 ተመቶ መውደቁ ይፋ የሆነው፡፡ የተዋጊ ጀቶቹ ሰራተኞች ህይወት እንዳላለፈ እና አንደኛው ቀላል ጉዳት ብቻ እንደደረሰበት ተወስቷል፡፡ አብራሪዎቹ ከጀቶቹ መውጣታቸው የተነገረ ሲሆን በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ሁቲ መግለጫም እየተጠበቀ ነው፡፡ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አደጋው መድረሱን በይፋ ማመኑን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።




የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በአዲስ አበባ


ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማክሮንን " ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ " ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

" በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖር እምነታቸውን ገልጸዋል።

የማክሮንን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ ዋና ዋና የአዲስ አበባ መንገዶች ላይ የተተከሉ የማስታወቂያ ስክሪኖች " ፕሬዜዳንት ማክሮን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መጡ " የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፈባቸው ነው።

ማክሮን ፤ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት ሲመጡ በ6 ዓመታት ይህ ሁለተኛቸው ነው።


ምስላዊ መረጃ፦ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጪው ጥር አጋማሽ ገደማ የስልጣን መንበራቸውን ሲረከቡ በሀገሪቱ ጊዜያዊ ጥበቃ የተሰጣቸውን ጨምሮ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ናቸው የተባሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በገፍ ለማስወጣት እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

አሜሪካ ካለፈው ዓመት ጥር እስከ መስከረም ባሉት ወራት ብቻ፤ 271,000 ገደማ ስደተኞችን ወደ 192 ሀገራት በግዳጅ መልሳለች። ከእነዚህ መካከል 27ቱ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ መሆናቸውን የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ አስፈጻሚ መስሪያ ቤት ዓመታዊ ሪፖርት ያሳያል።

በተቋሙ መረጃ መሰረት፤ በ2024 ወደ ኢትዮጵያ የተጠረዙ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ሶስት ዓመታት ከተመዘገቡት ከፍተኛው ነው። በ2019 አሜሪካ 32 ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የመለሰች ሲሆን አሃዙ በቀጣዩ ዓመት ወደ 43 ከፍ ብሎ ነበር።

ከኢትዮጵያ ጎረቤቶች በ2024 ብዛት ያላቸው ዜጎቿን ከአሜሪካ የተቀበለችው ሶማሊያ ነች። ሶማሊያ በተጠቀሰው ዓመት ከአሜሪካ በግዳጅ የተመለሱ 64 ሰዎች ተቀብላለች።

ከኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን በተጨማሪ 48 ኬንያውያን፣ 34 ኤርትራውያን እና 5 ሱዳናውያን በዓመቱ ወደ ሀገራቸው በግዳጅ እንደተመለሱ የተቋሙ ዓመታዊ ሪፖርት ይጠቁማል።

በ2024 አሜሪካ በግዳጅ ወደ ተለያዩ ሀገሮች የላከቻቸው ሰዎች ቁጥር ባለፉት አስር ዓመታት ከነበረው ሁሉ ከፍተኛው ነው። በአሜሪካ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ወይም በጊዜያዊ ጥበቃ የሚኖሩ 11 ሚሊዮን ገደማ ስደተኞች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚገመት የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ይጠቁማሉ።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


የጥንቃቄ መልዕክት

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ህብረተሰቡ ያልተመዘገቡና የጥራት ደረጃ የማያሟሉ ፀረ ወባ መድኃኒቶችን እንዳይጠቀም አሳሰበ፦




አርሰናል 5 -1 ክሪስታል ተጠናቋል

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐግብር 5ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ጋብሬል ጄሱስ 2x ፣ ካይ ሀቨርትዝ ፣ ዴክላን ራይስ እና ማርቲኔሊ አስቆጥረዋል።

የክሪስታል ፓላስን ብቸኛ ግብ እስማኤል ሳር ከመረብ አሳርፏል።

አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ያደረጋቸውን ያለፉት አስር ጨዋታዎች አልተሸነፈም ሰባቱን ሲያሸንፍ በሶስቱ አቻ ተለያይቷል።


ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር ጸደቀላት

ዓለም ባንክ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል። ከብድሩ 90 በመቶው የንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጧል። ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።

ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚለቀቀው፣ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው። የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደኾነም ባንኩ ባሠራጨው አጭር መግለጫ አውስቷል።

ንግድ ባንክ መዋቅራዊ ማሻሻያውን ከመተግበሩ በፊት፣ የቅርንጫፎችና የሠራተኛ ቅነሳን ጨምሮ ማሻሻያው ሊያስከትላቸው በሚችላቸው ማኅበራዊ ተጽዕኖዎች ዙሪያ በቅድሚያ ጥናት ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።


“የትግራይ ሰራዊት በዲዲአር ስም እንዲበተን እየተደረገ ነው” - በደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት

በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና በመልሶ ማዋሃድ ሥራ ስም፣ የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄ ሳይመለስ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዲበተኑ እየተደረገ ነው ሲል ክስ አሰምቷል።

የህወሓት አንዱ ክፋይ በመቐለ ከተማ፣ “የእምቢታ ዘመቻ” ብሎ የጠራው ስብሰባ ሲያጠናቅቅ፣ “ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈፅም የተሰጠው ሥራ ሙሉ በሙሉ ወድቋል” በማለትም ገልጿል።

በሌላ በኩል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለሦስት ቀናት ያካሔደውን ስብሰባ አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ “ክልሉን ወደ ግርግር እና የአመፅ ተግባር ለማስገባት የሚንቀሳቀሱ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አይታገስም” ብሏል።

የሁለቱ ቡድኖች ፖለቲካዊ ሽኩቻ  አሁንም ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ እንደዘለቀ ነው፡፡


በሶሪያ የተገኘው የጅመላ መቃብር በዓለም ላይ ትልቁ የጅምላ መቃብር ሳይኾን አይቀርም ተባለ

ሶሪያዊያን በከፍተኛ ደረጃ ተሰቃይተው ከተገደሉ በኋላ በጅምላ የተቀበሩበት የቁተይፋ መቃብር ነው።
በዚህ መቃብር 150,000 ሶሪያዊያን በጅምላ ተቀብረዋል። እንደዚህ ዐይነት የጅምላ መቃብር ናዚ አይሁዶችን በጅምላ ከቀበረ በኋላ ታይቶ አይታወቅም።
150,000 የጠፉ ሶሪያዊያን እዚህ ጅምላ መቃብር ውስጥ በስብሰው ተገኝተዋል።
@ዘኢኮኖሚስት


በሞዛምቢክ ቺዶ በተሰኘው አውሎ ንፋስ የሟቾች ቁጥር 73 ደረሰ

በሞዛምቢክ ውስጥ በቺዶ አውሎ ንፋስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 73 መድረሱን የአደጋ አስተዳደር ባለስልጣናትማ አስታውቀዋል።
የሀገሪቱ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ሊቀ መንበር ሉዊዛ ሜኬ በሰጡት መግለጫ “አውሎ ነፋሱ በደቡብ አፍሪካ ሀገራት ላይ ያደረሰውን ጉዳት መጠን የሚገመግምው ሂደት ቢቀጥልም ተጨማሪ ስራዎች እየተለዩ ይገኛል። በአውሎ ነፋሱ ምክንያት የሞቱትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ማወቅ አንችልም በየእለቱ የተጎጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ግን መናገር እንችላለን ብለዋል።

ሁኔታው በጣም አስፈሪ እና አስጨናቂ ነው። ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር ለማወቅ ብዙ ድጋፍ እንፈልጋለን ፣ ካልሆነ ግን አስከሬን ለማግኘት በጣም ከባድ እየሆነብን ነው ፣ ምክንያቱም አንዳንዶቹ ህንጻዎች በላያቸው ላይ ከወደቁ በኋላ በጥልቅ የተቀበሩ ናቸው ብለዋል ።አውሎ ነፋሱ እየተረጋጋ በሄደ ቁጥር የጉዳቱን መጠን ስንገመግም የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ የሚችልበት እድል አለ ሲሉ ሜኬ አክለዋል።

2.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአውሎ ነፋሱ ተጎድተዋል ተብሏል። የሞዛምቢክ የህፃናት አፍን ድርጅት የዩኒሴፍ ተወካይ ሉዊዝ ኢግልተን እንዳሉት 90 ሺ የሚያህሉ ህጻናት በአውሎ ነፋሱ “የከፋ ጉዳት” ደርሶባቸዋል። “በተጎጂው ማህበረሰብ ውስጥ ከሞላ ጎደል የተጎዱ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ ነው። እነዚህ ልጆች ስንቅ እና መጠለያ ለማግኘት እየታገሉ ያሉ ናቸው። ልጆች የአውሎ ነፋሱን ጫና እየተሸከሙ ይገኛል።

አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ልብን የሚሰብር ነው ሲሉ ኢግልተን ተናግረዋል። እሮብ እለት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ለአውሎ ነፋሱ የአደጋ ጊዜ ምላሽ 4 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቷል። በአጎራባች ሀገር ማላዊ የሀገሪቱ የአደጋ እና አስተዳደር ጉዳዮች ዲፓርትመንት  እንደገለፀው የሟቾች ቁጥር 13 የደረሰ ሲሆን በደቡብ ማላዊ ክልል ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች 45,000 ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል። ባለፈው ሳምንት ቺዶ አውሎ ንፋስ ሞዛምቢክ ውስጥ ኃይለኛ ንፋስ ፣ ነጎድጓድ እና ከባድ ዝናብ አስከትሏክ። 24 ሰዓታት ውስጥ ከ250 ሚሊ ሜትር በላይ ዝናብ የጣለ ሲሆን ከዚያም አውሎ ነፋሱ ወደ ማላዊ ተሻግሯል።






ሩሲያ የዩክሬንን ዋና ከተማ በሚሳኤል እየደበደበች መሆኑ ተሰማ

ሩሲያ የዩክሬን ዋና ከተማ ኬቭን በሚሳኤል እየደበደበች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቃቱም በውል የማይታወቁ ሰዎች የተገደሉ እና የቆሰሉ እንዳሉ የዩክሬን ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በትላንትናው ዕለት ዓመታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ "ሩሲያን ማሸነፍ እንደማይቻል ዩክሬንም ሆነች አጋሮቿ ደጋግማ ማሰብ አለባቸው" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በዚህም በዛሬው ዕለት ሩሲያ ኬቭን በሚሳዔል ጥቃት እየደበደበች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ "ከ630 በላይ መኖሪያ ሕንጻዎችን ጨምሮ፤ ከ50 በላይ የጤና ተቋማት እና ትምህር ቤቶች አገልግሎታቸውን አቋርጠዋል ሲሉ" የኬቭ ባለስልጣን ክስ አቅርበዋል፡፡

የኪቭ ከተማ ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ ሰርሂ ፖፕኮ በሰጡት መግለጫ፤ የሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በርካታ መሰረተ ልማቶች በሩሲያ ጥቃት መውደማቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ጥቃት ሩሲያ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ሳትጠቀም እንዳልቀረች ባለስልጣኑ ተናግረዋል፡፡

የዩክሬን አየር ሃይል የአየር መከላከያው ወደ ዋና ከተማው የተወነጨፉትን አምስት የኢስካንደር-ኤም ሚሳኤሎችን መትቶ ማክሸፉን አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በሮስቶቭ ክልል የዩክሬን የሚሳኤል ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በኪቭ ላይ የቡድን ጥቃት መፈጸሙን አምኗል፡፡

ጥቃቱ በተሳካ ሁኔታ የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት (SBU) ኮማንድ ፖስት፣ የሉች ዲዛይን ቢሮ እና የሚሳኤል የጦር መሳሪያ የሚሳኤል ማማማቻዎችን ኢላማ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ አውዳሚ ጦርነት ከገቡ ሦስት ዓመት ሊሞላቸው የወራት እድሜ የቀራቸው ሲሆን፤ ከሁለቱም በኩል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሩሲያዊን እና ዩክሬናዊያን ከመኖሪያ ቀያቸው እንደተፈናቀሉም ዓለም አቀፍ የሰብዕዊ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ያወጧቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡



Показано 20 последних публикаций.