ግጥም ለኢየሱስ ️️️📖✍


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Другое


እንኳን ወደ ግጥም ቤታችሁ በደህና መጣችሁ ይህ የገጣሚ #አማኑኤል ነጋሽ እና የለሎች ገጣሚያን ግጥም የሚቀርብበት ነው
አዘጋጅ✍️AMANUEL NEGASH(Abu)
ግጥሜን ለኢየሱስ
5K🏃🏃‍♂️
ለአስተያየት👇
@AbuGitimBot
@abu_ND8
🛑YOUTUBE🛑
https://www.youtube.com/@gitim_alem
Telegram
@gitim_alem

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций




❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓
.     📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ 📖

🙋‍♂እግዚአብሔር ወደ ሸክላ ሰሪው የላከው ነብይ ማን ነው❓

📌ትክክለኛ መልስ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ ።
⚡️Wave ለመግባት 👉 @samazion_cj


እምነት😭

ዕብራውያን 11
32፤ እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና።
33፤ እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥
34፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ።
35፤ ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤
36፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤
37፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤
38፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።ዕብራውያን
39-40፤ እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።🤔😭

ዐይናችን ይከፈት በኢየሱስ ስም😞

መልካም ምሽት🤔


ገደብ አልባ ፍቅር

አንተ አይሁድ ሆነህ እኔ ሰማሪያ
በሰው የተጠላሁ የሆንኩ ማስተማሪያ
ገደብን ሁሉ አልፈህ ስትገባ መንደሬ
ሕይወቴን ለውጠህ ልትሆን መምህሬ
ሕግጋትን ሽረህ መጣህ ወደ ቤቴ
ደፍርሶ የነበረው ጠራልኝ ሕይወቴ.
ለአንዲቷ ነፍስ ስለኔ ተጨንቀህ
ማለፍ ግድ ቢልህ ድንበር አቋርጠህ
በዛ በቀትር ከቀኑ ስድስት ሰዓት
ውሃ የሚቀዳ ማንም በሌለበት
ከጉድጕዱ አጠገብ ብቻህን ቁጭ ያልከው
ታሪኬን ለውጠህ አባት ልትሆነኝ ነው.
መች ጠምቶህ ሆነና ውሃ ስጪኝ ያልከው
ከኔ ተቀብለህ ልትጠጣ ያሰብከው
ወደ ተዘጋው ልብ የሚስጥሬ ጕዳ
ልትገባ ነው እንጂ ፈልገህ ቀዳዳ.
ልክ እንደ ልማዴ ሰዓቴን ጠብቄ
ውሃ ልቀዳ ብመጣ እርቄ
የሕይወቴን ጌታ በዛ አገኘውት
ልቤን ከፍቼ ከቤቴ አስገባውት.
አይሁድ ነህ ብዬ ችላ ያልኩት ሰው
ያውቀኛል ብዬ ከቶ ማልጠብቀው
ጉዴን ሁሉ ነግሮ ወንጌል አሰበከኝ
ውሃ አጠጪኝ ብሎ የሕይወት ምንጭ ሆነኝ.

     ✍ ሃና መኮንን

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8


ለምን ነጋ?


በደስታ አገር ውሰጥ መሀል ክፍለ ከተማ፣
ብርሃኑን አድምቆ የ ፍቅራችን ሻማ፣

ደስ እያላቸው ሰማይና ምድር፣
እንደ አሳ ሰጥሜ በምኞቴ ባህር፣

ባማረው አዳራሽ ሰፍሬ በእንቅልፌ፣
ከናፍቆቴ ጉያ ሃሳቤን ታቅፌ፣

ልኑር ስል ይህ ፍጥረት አቤት ግን ቅናቱ!
ምሽት ይሻለኛል ለምን ነጋ ሌቱ?


ሁሉም ከተሟላ ቀን ከሆነ ሁሌ
መች ታስቦ ያውቃል ፈጣሪ እንዳለ?

በተደላው አለም  እንድያው ስንደላቀቅ፣
ቅጠሉን  ጠግቤ ከፍሬው  ግን ብርቅ፣
ጥርሴ ይሳቅ እንጂ ውስጤ የለውም  ጤና፥
ምሽት ይሻለኛል እረፍት አለውና።

ለምን ነጋ ሌቱ ልኑር ስል ህይወቴን?
እርካታን ጠግቤ ሳልሸኘው ጥማቴን።
አይኔ በቃኝ ሳይል እንባ ማፍሰሱን ፣
ጉልበቴ ሳይደክም ሳያቆም መንበርከኩን።

ምረባውን ማይረባውን ሁሉን ባንዴ ይዞ፣
ልቤን ልያደናብር  ሊያስቀረው አፍዝዞ፣
ቀኑ ለምን መጣ አልፈልገውም እኔ፣
ምሽት ይሻለኛል አይይ ብርሃንን አይኔ።


✍አላዘር T.

| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |


መስዕዋት አንዴ ብቻ


ዕብራውያን 10 ፡26፤ የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥

የአድስ ኪዳን የመሥዋዕት ስርዐት ከብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ስርዐት ጋር ቡብዙ ይለያያል ።
የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት የምደረገው አንድ ሰው ሀጢአኛ እንደ ሆነ ስሰማው የኮርማንና የዋኖስን እንድሁም ለሎችን ለመስዋዕትነት የሚሆኑትን እንስሳት ሀጢአትን በሰራበት ሰዓት ሁሉ ያቀርባል ። ይህ የመሥዋዕት ዑደት እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ድረስ የቀጠለ የመሥዋዕት ሥርዓት ነበር።
በዚህ ሥርአት መሥዋዕትነት ይደገማል ሀጢአት ሲደገም አሁንም አሁንም መሥዋዕቱን ይደጋግሙታል።
ነገር ግን አዲስ ኪዳን ማለትም ኢየሱስ በደሙ አዲሱን ሥርዐት ከጻፈ ወዲህ ነገሮች እንደ በፍቱ አይደለም፤ አንድ ሰው መሥዋዕት አንደ ብቻ ነው የቀረበለት ይህም አንደ ኢየሱስ በመስቀል በከፈለው ዋጋ። ታዲያ አንድ አማኝ መስዋዕት አንዴ ከተደረገለት ከክርስቶስ መሥዋዕትነት ውጭ ለላ መሥዋዕት መጠበቅ የለበትም።
እንደ ብሉይ ክዳን ሀጢአት ከሰራሁ የሚያስተሰርይለት ዳግም መሥዋዕት የለም።
ከዚህ መሥዋዕት በላይ አልፎ በሀጢአተ የመኖርን ሰው ቃሉ ''የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ የጸጋውን መንፈስ ያክፋፋ '' ይለዋል ለዚህም እግዚአብሔር ትልቅ ቅጣት እንዳዘጋጀለት ነው ቃሉ ምናገረን።
እግዚአብሔር ልጁን ለእኛ ሀጢአት ብሎ ጨክኖበት እየመረረውም ለሀጢአት አሳልፎ ሰጥቶአልና በልጁ ጉዳይ ድርድር አይቀመጥ ልጁን የተላለፈ ለእግዚአብሔር ቀዩን መስመር አልፏል አይራራለትም። ልጁን አቅልለን ሲናየው እግዚአብሔርን አያስችለውም ወድያውኑ ይነሣል፤ ምክንያቱም ለዛ ሰው ያለ ሀጢአት ወርዶ ተሰቅሎ ሞቶለታልና ።
እግዚአብሔር በልጁ ጉዳይ ቀልድ አያውቅምና ቀይ መስመሩን አንለፍበት!!

ይቀጥላል ....

✍️አማኑኤል ነጋሽ(አቡ)

| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |


ብዙዎቻችን ከቅባቱ ጋር ያልተገናኘነዉ ከሌሎች ጋር ፉክክር ዉስጥ ገብተናል፡፡ ይህ በእዉነት ልናስበዉ የሚገባን ጉዳይ ነዉ፡፡እግዚር ሳይሆን ቅባቱን ያዘገየዉ የእኛዉ ያለመታዘዝና ትዕብታችንን ነዉ፡፡
እግዚር ትዕብተኞችን ይቃወማል ለትሁታን ፀጋዉን ይሰጣል፡፡ አራት ነጥብ፡፡ከዚህ ዉጭ ሌላ ቅባት መቀበያ መንገድ የለም፡፡
ትህትና ቅባትንይስባል በተቃራን ትዕብት ቅባትን ይገፋል፡፡
ቅባተኞች አልፎ ይሄዳሉ ቅንዓተኞች ይዋዳሉ
ቅባተኞች ይሸለማሉ ቅናተኞች ይሸበራሉ
ቅባተኞች ይሸኛሉ ቅናተኞች ይቀበራሉ
ቅባተኞች ይሾማሉ ቅናተኞች ይሻራሉ

3/መለመን ወይም መጠየቅነዉ፡ በዚህ ኤልያስ ለኤልሳኤ እስከ አሁን ከእኔጋር ቆይተል ከአንተ ሳልወሰድ ከእኔ ምትፈለገዉ ምንድር ነዉ? በአንተ ላይ ያለዉ መንፈስ በእኔ ላይ በእጥፍ ይሁን ብሎ ጠየቀዉ፡፡ኤልሳዕ ኤልያስን የምጠይቀዉ ሌላ ብዙ ነበረዉ፡፡ነገር ግን የኤልሳዕ መሻት እና ያንን የበረዉ ሁሉነገሩን ትቶ ኤልያስን የተከተለዉ ለቅባት ብቻ ነዉ፡፡ይህን ጥያቄ ኤልያስን ለመጠየቅ ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ ምርጫዉን ያደረገዉ ቅባት ስለነበረዉ፡፡
እኛስ ቢንሆን ይህ ዓይነት ጥያቀዉ ብቀርብልን ምላሻችን ቤት ዘመናዊ መኪና አቤት ሀብት የኤልያስ የነበረዉ ሁሉ ብለን ነበር ምንመለሰዉ፡፡ይህን በምን አወክ ካላችሁኝ መልሴ ሌላ ጥናት ስያስፈልግ የፀሎት ርዕሳችን ያጨናነቁ ጉዳዮች ከእነዚህ ዉጭ ሌላዉ የለም፡፡ፀሎታች ዝማርያችን ስብከታችን ሁሉ በምድራዊፍላጎታችን ላይ ነዉ፡፡
መመልከት ነዉ፡ ይህ የመጨረሻ መርህ ነዉ፡፡ኤልያስ ኤልሳዕን እኔ ከአንተ

በወንድም ዳግም ዳንኤል
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |


ቅባት ምንድር ነዉ
2ኛ ነገ 1-22
ቅባት ማለት መለኮታዊ የሆነ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ህይወት ተገልጦ የሚሰራበት የተለየ መንገድ ነዉ፡ዶ/ር ቻላቸዉ ፡፡ይህ ደግሞ መለኮታዊ ብቃት ከተፈጥሮአዊ ዉጭ የሚገለጥበት እዉነት ነዉ፡፡ቅባት ኃይል ስዎች መካከል ልዩ የመፍጠር ሀይል አለዉ፡፡በክርቲያኖች አንድ መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ በአንድ አጥብያ እያመለኩ አንድ ትምህርት አብሮዉ ተምሮ ግን ይህን ያህል በህይወታቸዉና በአገልግሎታቸዉ ልዩነት እንዴትሊፈጠር ቻለ? ይህ ምሥጥሩ ከቅባት ጋር ያላቸዉ ግኑኝነት እና በግል ህይወታቸዉ ለመንፈሳዊ ነገሮች የምሰጡት ትኩረት ይወሰናል፡፡ ደከማና ብርቱ ስለመሆን አይደለም ጎበዝ እና ሰነፍ ስለመሆን አይደለም ትኩረት፡፡ይህን እዉነት በደቀመዛሙርት መከካል የዚህ ዓይነት ሁነታ ተከስቶአል፡፡ የ12 ደቀ ደቀመዛሙርት አገልግሎትታቸዉ ስንመለከት ሁሉ እኩል ተፅእኖ አልፈጠሩም፡፡አንዳንዶች እንኳን ምንም ዓይነት ሥራ እንዳልሠሩ ስራቸዉና ስማቸዉ እንኳን ከመጽሐፍ ቅዱስ ለማግኘት እስከ ምንቸገር ድርስ ያሉሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በእያንዳንዱ መፅሐፍ ቅዱስ ገፅ ላይ ይገኛል፡፡ለቅባት የሚንሰጠዉ ትኩረት በእኛዉ የሚገለጠዉን የቅባትንልክ ይወስነናል፡፡
የቅባት ኃይል ሲገለጥ የጨለማዉ መንግሥት ሥራዉ ይፈርሳል፡፡ የቅባቱ ኃይል ሲገለጥ ቀንበር ከትዉልድ ጫንቃ ይሰበራል፡፡ ስለዚህ ቀንበር የሚሰበር በዚህ ምድር የቅባት ብቻ ነዉ፡፡ቅባት መለኮታዊ ኃይል ከተለምዶዊና ከተፈጥሮ ዉጭ እንግዳ የሆነ ክስተት የሚከወንበት የሰማይ ኃይል የሚገለጥበት አሠራር ነዉ፡፡
ቅባት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የመሸጋገር መለኮታዊ ባህርዉ አለዉ፡፡ እግዚር ቅባትን የምሰጠዉ የትዉልድን ክፍተት እና እንቆቅልሽን ለመፈታት ነዉ፡፡ የብሉክዳን ሲንመለከት እግዚር የመጀመሪያዉ ከመወለዱ በፍት በታላቅ ቅባት የተገለጠዉ ሳምሶን ሲሆን በእርሱ ላይ የተገለጠዉ ቅባት እሥሬኤልን ከፍለስጠማዊያን እጅ ነፃ አዉጭ እንድሆን ነዉ፡፡ ሳዖል ላይ የተቀባዉ የእሥራኤል ጠላቶችን በተለይ የአማለቃዊንን ዝክር ከምድር ገፅ ለማጥፋት ነዉ፡፡ዳዊት የተቀባዉ ከፍልስጤማውያኖች እጅ የእሥራኤል ህዝብ ነፃ ለመዉጣት ነዉ፡፡ ቅባትን እግዚር በግለሰቦች ላይ የሚያመጣዉ ዋና ዓላማ ህዝብ ነፃ ለመዉጣት ነዉ፡፡ቅባትን እግዚር በግለሰቦች ላይ የሚያመጣዉ ዋና ዓላማ ህዝቡ ነዉ፡፡ቅባት የግለሰቦች ንብረት ሳይሆን እግዚር ለህዝብ ችግርና ሰቆቃ መለኮታዊ ምላሽን ለመስጠት ግለሰቦችን ተጠቅሞ መለኮታዊ ፈቃድ የምፈጽምበት ነዉ፡፡የቅባቱ ባለበትነቱም ንብረትነቱ እግዚር ራስ ነዉ፡፡ ቅባት የግለሰቦች የቅንጦት ንብረት ሳይሆን የመለኮቱን ፈቃድ በእነርሱ አማከይነት ለመፈፀም እግዚር የሰጠዉ ዉድ የመለኮት ኃይል ነዉ፡፡
ቅባትን እግዚር ሲስጥ አስቀድሞ ዓላማዉን ያስታዉቃል፡፡ የተሰጠዉ ቅባት ለዓላማ በተገቢ መንገድ መግለጥ እና ለተሰጠበት ዓላማ ብቻ መጠቀም ግደታዉ የተቀባዩ ግለሰብ ነዉ፡፡
እግዚአብሔር ሆይ ቀባኝ የዘመናች የሁላችን ፀሎት ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ይህ ፀሎት አስፈላጊ እንዴሆነ ብታወቅም የእግዚር መልስ ግን ለምን ቅባቱን ፈለክ ልጄ ? ያ ማለት የሚንቀባበት ምክንያት ልታወቅ ይገባል፡፡ያለ ዓላማ የሚሰጥ ቅባት በፍፁም የለም፡፡እግዚር ይህን ዉድ የመለኮትን አሠራር የሚገለፅበትን ዕንቁን እንድሁ ስለተለመነ አይሰጥም፡፡ቅባት በእኛ ልመና ብቻ ሳይሆን በሰጨዉ በእግዚር ፈቃድ የሚሰጥ ነዉ፡፡ ቅባት በእኛ በኃይል እና በሙላት እንድገለጥ ከእኛ የምጠበቅ ስብዕናን መገንባት ያስፈልጋል፡፡ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ያ ሁሉ የከተማን ብረት ነቃቅሎ ይዞ የሚሄድ አንበሳን እንዴ ጥጥ የሚፈትል ሳምሶን ያን ከባድ ቅባት አጣዉ፡፡ለምን ቅባቱን የሚያስቀጥል ስብዕና ባለመገንባቱና አካሄዱን ጥንቃቄዉ ባለመምራቱ አጣዉ ፡፡መቀባት ብቻዉን በቃ አይደለም፡፡ቅባቱ የምፈለገዉ ህይወት መርህ መከተል እጅግ ወሳኝ ነዉ፡፡በተመሳሳይ ሳዖልም በተቀባዉ ቅባት ረዥም ርቀት ከቅባቱ ጋር አልተራመደም፡፡እግዚር ቅባቱን ያለዓላማ ለምጠቀሙት ጊዜ አይሰጥም፡፡ ቅባቱ ወዲያዉኑ ወደ ዳዊት ሽፍት አደረገዉ፡፡ሳሙኤልንም እግዚር እንድህ አለ እኔ ለናቅሁት ለሳዖል አታስብ፡፡እርሱ ቅባቱን ያላከበረዉን እግዚር አያከብርም፡፡
እግዚር በየዘመናቱ አድስ ቅባት አይፈጥርም፡፡ ነገር ግን ያን የመጀመሪያ ቅባት ከግለሰብ ወደ ግለሰብ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ያሸጋግራል፡፡ይህ ልዩ የእግዚር አሠራር ነዉ፡፡አድስ የሚፈጠር ቅባት ሳይሆን ቅባቱ የምገለጥበት አድስ አሰራሮች ይዘረጋል፡፡ ለምሳሌ እግዚር በሙሴ ላይ ከተገለጠዉ ቅባት ለሰባ እሥራኤል ሸማግለዎች ላይ አሸጋገረዉ፡፡ በኤልያስ ላይ የሠራዉን ቅባት በእጥፍ ኤልሳዕ ላይ አስተላሌፈዉ፡፡ይህ ብቻ አይደለም የአድስ ክዳን የመጀመሪያዉ ነብይ መጥመቁ ዮሐንስ የተቀባዉ በኤልያስ ቅባት ነዉ፡፡
ቅባት ይህን ያህል ዉድና ዕንቁ ከሆነ እንዴት ማግኘት ይቻላል? ይህን ጥያቄ ሁሉ ቅባትን ኃይልና መለኮታዊ አሠራር የረዱ ሰዎች የምጠይቁ ጤይናማ ጥያቄ ነዉ፡፡የእኔም የሁልጊዜ ረሃቤና ጥማተ ነዉ፡፡ ይህን እዉነት አጥብቀዉ እራሰን ጠይቀያለሁ፡፡እግዚርን ጤይቀያለዉ፡፡ በቅባት ኃይል እያገለገሉ ያሉአገልጋዮችን አጥብቀ ጤይቃለሁ ምክንያቱም ቅባት ለቅባት ያለኝ መረዳት እና የቅባቱን አስፈላጊነት በዉል ከተረዳሁ ዉዲይ አብዘቼ ይህን እስላስያለዉ፡፡መልሱን ግን እግዚር ከቃሉ እዉነት አስተማረኝ፡፡ቅባት የሚገኝበት ልዪ የሰዉ ፍልስፍና የለለበት እግዚር በራሱ መንገድ የምሰጥበት መንገዶች የተለያዪ ናቸዉ፡፡ እግዚር በኤልያስ ላይ የነበረዉ ቅባት በኤልሳዕ ላይ በእጥፍ እንድሰራ እግዚርየሠራበትን ከቃሉ እዉነት የተረዳሁበትን ሃሳብ በጥቅቱ ልካፍላችሁ፡
ይህም ቅባቱን የመቀበያ መርህ፡ ማለት እግዚር ኤልያስን ከኤልዛበል ዛቻ ፈርቶ በዋሻዉ ዉስጥ ከተደበቀበት ጠርቶ ኤልያስን ገና ብዙ ያልፈፀሜዉ ቀርተልዕኮ እንዴለዉ ከተነገረዉ ዉስጥ አንዱ በፈንታህ ነብይ የሚሆነዉ ኤልሳዕን እንዴምቀባዉ ተነግሮለታል፡፡ይህ እዉን እንድሆን ኤልያስና ኤልሳዕ መገናኘት የግድ ነዉ፡፡ ስለዚህ ኤልሳዕ የተከተለዉ መርህ እነሆ፡
መከተልእና
መታዘዝ
ትህትና
መለመን መጠየቅ
ማየት
መከተል፡ ይህ ሁሉ ትቶ መከተል፡፡ኤልሳኤ የነበረዉ ንብረት ሥራ ማህበራዊ እሴቶችን ሁሉ ትቶ ኤልያስን ተከተለዉ፡፡ በዛሬዉ ዘመንዋ ዋጋ ብሰላዉ የኤልያስ ንብረቱ እና ሀብቱ በጣም ብዙ እንዴምሆን መገመት ይቻላል፡፡ ኤልሳዕ ይህን ሁሉ
ትቶ ቅባት ፍለጋ ተነሳዉ፡፡ በዛረዉ ዘመን ቢሆን ምን ይባል ነበረዉ፡፡አርፎ ሥራዉ አይገፋም እንዴ በስተእርጅና ወጥቶ ይንከራተታል፡፡
2/ትህትና፡ በእርግምጥም አንድ አባወራዉ የአንድን ነብይ አገልጋይ ለመሆን ወጣዉ፡፡ ኤልሳዕ ኤልያስ በሰረገለዉ እስከተነጠቀዉ ሰዓት ድረስ የኤልያስ አገልጋይ ነበረዉ፡፡ቃሉ የኤልያስ ረዳት ነበረዉ ይላል፡፡በተጨማርም በኤልያስ እጅ ላይ ዉሃ የሚያፈስ ነበረዉ፡፡ ይህን ሳስብ ለቅባት መፀለይ ቀላል እንዴሆነና ቅባትን ማግኘት ምያህል ከባድ እንዴ ሆነ እደነቃለሁ፡፡ ለዚህም ነዉቅባቱ የራቀብን ፡፡አቤት ትህትና !እንዴ ኤልሳዕ ያንን ሁሉ ሀብት ንብረት ጥሎ መጥቶ የኤልያስን እጅ ያሳጥባል፡፡ትህትና ዝቅ ብሎ ሌላዉ በማገለገል ዉስጥ ቅባት ይሸጋገራል፡፡ ዛሬ


ኢየሱስ ልባችን ሞልቶ ይደር 🤲
አሜን😌


Репост из: ግጥም ለኢየሱስ ️️️📖✍
ኢየሱስ ተወልዶ ባይሰብር ቀንበር
በድቅድቅ ጨለማ ተውጠን ነበር
በዳዊት ከተማ ባይገለጥ ኖሮ
ጠፍተን ቀርተን ነበር ገና ያኔ ድሮ።

ነገር ግን ተወልዶ የምስራች መጣ
በሞት ጥላ ላሉት የፅድቅ ፀሐይ ወጣ
አማኑኤል በስጋ ሆነልን መበርቻ
እኛም ይዘን መጣን የወርቁን መባቻ
ወርቅም ወርቅ አይደል እጅግ የረቀቀ
ለእኛስ ክብር አለን ልቆ የደመቀ
ደስ አያሰኘው ብር ነሃስ ወርቁ
ኑና በእልልታ የሱስን አድንቁ።

ግጥም ለኢየሱስ

   💙እወዳቸዋለ💙

---------------------------------------------------------
SHARE
            @gitim_alem
            @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8


HANBA TEKLE

"መሥዋዕት ለእግዚአብሔር"
ጥር 4 እሁድ ከሰዓት በሚሊንየም አዳራሽ

"የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤" ነህምያ 2:20
ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ጥር 4 በሚሊንየም አዳራሽ "መሥዋዕት ለእግዚአብሔር" በተሰኘ መሪ ቃል ምስጋናና አምልኮ የሚገባውን አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማምለክ ቀጠሮ ይዘናል!
እስከዚያው ሁላችሁም በፀሎት እንድታስቡን እንጠይቃለን!

{ @GITIM_ALEM }
{ @GITIM_ALEM }


የእግዚአብሄር መልኮታዊ አሠራር መረዳት

እግዚአብሔር ነገሮችን የሚሠራው በተላትናዉ መንገድ ብቻ ሳይሆን በራሱ በፈለገዉ መንገድ የመለኮቱን ፈቃድ ይሠራል፡፡ይህ ደግሞ የእርሱ ነፃዉምርጫዉ ነዉ፡፡ እኛ የሰዉ ልጆች ከመለኩቱ ፈቃድ ጋር አብኛዉ ጊዜ የመለኮቱ ፈቃድ በልምዳችን ለመፈፀም እንነሳለን፡፡ ፡፡እግዚአብሔር በየዘመናት ፈቃድ የሚፈፅመዉ በራሱ መንገድ ነዉ፡፡ ሰዎች ግን ይህንን እዉነት ሳይረዱ የእግዚርን መለኮታዊ ፈቃድን ይጋፋሉ፡፡
እግዚር በቀደመዉ ትዉል ጋር በሠራበት መንገድ ብቻ አይሠራም፡፡የእግዚርን አሰራር በተለመደዉ መንገድ መጠበቅ ከመለኮትን ፈቃድና ሥርዓትን መቃወም ብቻ ሳይሆን ለእግዚር ፈቃድ አለመገዛትን ነዉ፡፡
እግዚር በሙሴ ዘመን በሠራዉ አሠራር በኢያሱ ዘሜን የመለኮቱን ፈቃድና ኃይል አልገለጠም፡፡እግዚር በሙሴ ጋር ቀይ ባህርን የከፈለዉ ዉሃዉን በብትር እንድመታዉ አዘዘዉ፡፡ እንዲሁም ዉሃዉን በብትር በመታዉ ጊዜ ባህሩ ተከፈለዉ፡፡
እግዚር ኢያሱን ደግሞ ዮርዳኖስ ከህዝቡ ፍት እንድከፈል የካህናቶች በእግራቸዉ ዉሃዉን እንድረግጡ ወይም እግራቸዉን ዉሃ ዉስጥ እንድያጠልቁ አዘዘዉ፡፡ታድያ ይህ ማለት ምን ማለት ነዉ፡፡እግዚር በሙሴ ዘመን በሠራዉ መንገድ ብቻ ሥራዉን አይሠራም፡፡
ይህን ሃሳብ ያነሳሁበት አንድ ምክንያት አለኝ ሰዎች የእግዚር ፈቃድ በቀድሞ መንገድ ብቻ እየጠበቁ እግዚር በእኛ ዘመን እንድህ አልሠራም ብሎ የእግዚር ፈቃድን ሳይረዱ እነርሱ በምያቁትና በተረዱበት መንገድ ብቻ እግዚር ሥራዉን እንደምሠራ አድርጎ ሌላዉ ስቃወሙና ስኮንኑ የመስማትና የማየት ዕድል ስላጋጠመኝ ለዚህ ሃሳብ የራሴን አስተያየት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እዉነታ ማቅረብ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ስለሆነ የእግዚርን መለኮታዊ ፈቃድ በጭፍኝ ላሌመቃወም ና ላሌመኮነን ይህን ሃሳብ አቀርባለሁ፡፡ ደግሞም የእግዚርን ፈቃድ በእኛዉ በቀድሞ በሠራዉ መንገድ እንደማይሠራዉ ማወቅ ከእግዚር ቁጣ ይጠብቀናል፡፡የእግዚር ፈቃድ በቀድሞ ልማድ መፈፀም ሙሴ እግዚር ወደ ኬንአን ሳይገባዉ መንገድ ላይ የመቀረቱ ምሥጥር የእግዚርን ፈቃድ በልምድ መፈፀሙ ነዉ፡፡እግዚር አድስ አሰራር ለሁሉም ነገር እንዳለ አለማወቅ አለመረዳት ትልቅ ስህተት ነዉ፡፡ እግዚር ባህርን የከፈለዉ ዉሃዉን በብትር በመምታት እንደሆ ብቻ በመቁጠር የእግዚአብሔር ን የመለኮቱን ፈቃድ በራሱ ልምድ እና በቀድሞዉ አሠራር መገደብ ትልቅ መንፈሳዊ ክሳራ ነዉ፡፡ ሙሴ እግዚርን በራስሱ መንገድ ልመራዉ ፈለገዉ፡፡ ይህም እግዚር ሙሴን አለቱን ላይ ተናገር ሲለዉ በእጁ በነበረዉ ብትር ዓለቱን መታዉ ፡፡እግዚር ሙሴና ወንድሙን አሮንን ተቆጣዉ፡፡ነገርግን ለህዝቡ ስል ዉሃን ከዓለቱ አፈለቀዉ ፡፡ለሙሴ የቀድሞ ልምድ ጉድ አደረገዉ ፡፡ የእግዚር አድስን ምሪትና አሠራር በቀድሞ ልማድ ስቀይረዉ እግዚር ተቆጥቶ ወደ ተስፋዉ ምድር እንዳይ ገባዉ ከለከለዉ፡፡
አድስ ነገር ሲሆን ሁለ ለመቃወም ከመሮጥ እና ከመነሳሳት ነገሩ በእግዚር ቃል እዉነት መመዘን ብልህነት ነዉ፡፡ እግዚር በሁሉም ነገር የራሱ ሥራ የሚያከናወን የሚሠራበት መንገድ አለዉ፡፡ ዛሬ በተለይ የእግዚርን አሠራር ከመከተል የቦርን ዉሳኔ መከተል ሌላኛዉ የዘመናችን ትልቁ የመለኮቱ አሠራር ዕንቅፋት ነዉ፡፡ ስለ ጉዳዩ እግዚር ምን አለ ?ቃሉስ ምንይላል? ከማለት ቦርዱ ምን አለ ኮምቴዉ ምን አለ ማለት ትልቅ ሥፍራ ይዞአል፡፡ ይህ ደግሞ በራሱ ቦታ ጥሩና ጠንካራ ጎን እንዳለ ብታወቅም በልዩ መሰጠትና በእግዚር ፈቃድን በማስቀደም ካልተወሰኔ የእግዚርን ፈቃድ መጋፋቱ አይቀርም፡፡
እግዚአብሔር በሙሴ ዘመን በሠራበት መንገድ በኢያሱ ዘመን ካልሠራ እንደየ ትዉልዱ ዘመንና ጊዜን የመጠኔ አድስ መለኮታዊ መንገድ መዘርጋት የእግዚር ሥልጣን ነዉ እንጅ የእኛን ቦርድ ዉሳኔ መሠረት ለመስራት እርሱ አይገደድም፡፡
የአባቶችን ምክርና ሃሳብ እየቃዉሙክ እንዳደለሁ እንድትረዱኝ እፈልጋለሁ፡፡ እያወራ ያለዉ ሃሳብ የእግዚርን መለኮታዊ አሠራር ልዩ ልዩ እንደሆነ ለመግለፅ ነዉ፡፡
ስለዚህ እግዚአብሄር ፈቃድ እና አሠራር በቀደሞዉ መንገድ እንድሆንና እንድሠራ መሞከር እጅግ የከፋ ቅጣት ስለ ሚያመጣ ምሪትና የአሠራር መንገዱን ከእርሱ መጠበቅ አስፈላግ ነዉ፡፡
እግዚር በእኛ ዘመን እየሠራ ባለዉ መንገድ በሚቀጥለዉ ትዉልድ አይሠራም፡፡ እኛም ደግሞ የቀድሞ የእግዚር የአሠራሩ መንገድን ይህ ብቻ ነዉ ብሎ ትዉልድን መጫን የለብንም፡፡ ይህን እዉነት ለራሳችንና ሌሎች በሚንወሰንበት አባቶች በልቤ ሰፊነት እና በቃሉ እዉነት ሚዛናዉ ሃሳብ መያዝ አለባቸዉ፡፡ሌላዉ ደግሞ የእግዚር አሠራር መንገድ ነዉ ብሎ ከእግዚር በትክክል ሳይሰሙና ምሪትን ሳይቀበሉ ከእግዚር ፈቃድ ዉጭ የራሳቸዉ ስመትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገዉ ልምምዶች በቃሉ ብርሃን ልጣሩ ይገባል፡፡የአሮን ልጆች የራሳቸዉ እሳት በመሰዉያዉ ላይ አነደዱ እግዚርም ተቆጥቶ ቀሰፋቸዉ፡፡ የራሳችን ፈቃድና ስሜት በእግዚር ፈቃድ ላይ መጨመርም የባሰ ፍርድ አለዉና ሁለቱንም በጥንቃቄ ማየት ያስፈልጋል፡፡
የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃድ አሠራርን ምሪትን ከእርሱ እየቀበልን ለሌሎች በረከትና መትረፍረፍ እንድንችል ለሁሉም ይህንን ከቃሉ እዉነት የተረዳሁትን ሃሳብ አቅርብያለሁ፡፡
እግዚአብሔር ፈቃዱንና የፈቃዱን አሠራር መንገድን ይገግለጥልን፡፡
አሜን !!!!

በወንድም ዳግም ዳንኤል

| @GITIM_ALEM
| @GITIM_ALEM


ለመረጃ ያህል

"ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።" ማቴ 24;44

ስለ አለም ፍፃሜ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ከአለም ፍፃሜ አመልጣለሁ ብላችሁስ ትገምታላችሁ?

እኔ እንደ አንድ ክርስትያን የአለም ፍፃሜ መኖሩንም ሆነ መቅረቡን አምናለሁ እንጂ እንደዚህ ሰውዬ ከአለም ፍፃሜ አመልጣለሁ ብዬ ለሠከንድም ቢሆን የሞኝ ሃሣብ አስቤ አላውቅም !""!

ሰውየው ሁላችንም የምንጠቀመው የ #FACE BOOK ባለበት ነው ማርክ ዙከምበርግ ይባላል ። በፈጠራ እውቀቱ ጣራ የነካና የተከበረ የናጠጠ ባለሃብት ነው !!""!!

ከዚህ በፊት አንድ ጅል ባለሃብትም ከአለም ፍፃሜ አመልጣለው ብሎ ከፍተኛ ግንባታ እንደገነባ ሠምቼ በሞኝነቱ ተገርሜ ነበር አሁን ደግሞ ይሄ በቀለም ዕውቀቱ "ጥግ ነክቷል" የሚባለው የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከምበርግ ከአለም ፍፃሜ አመልጣለሁ ብሎ በማሠብ ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ በመመደብ ከአስር ቅንጡ ህንፃዎች በላይ የሚሆኑ የተካተቱበትን የምድር ለምድር ግንባታ እያከናወነ እና በብዙ ቴክኖሎጂዎች የታገዘ ስራን እየሠራ ይገኛል !!"""!!

ለሰው ልጅ ስጋዊ ብቻ ሣይሆን መንፈሣዊ ምግብም ያስፈልገዋል የሚባለው እዚህ ጋር ነው ። ምክንያቱም በሁሉም እምነቶች እንደሚታመነው የአለም ፍፃሜ ብቸኛ መዳኛው እምነትህና በጎ ተግባርህ እንጂ ዛሬ የምትገነባው ድንጋይና ብረት ሊሆን አይችልም !""!!

ምናልባት… ምናልባት… የኒውክሌር ጦርነት በቅርብ አመታቶች ከተከሠተ ከሱ ሊታደገው ከቻለ እንጂ ከአለም ፍፃሜ በድንጋይና ብረት ግንባታ እንዴት መዳን ይቻላል ? 🤔

እናንተ ምን ትላላችሁ ለዚህ ተግባሩ?

| @GITIM_ALEM
| @GITIM_ALEM


ይሄ መዝሙር ግን😌

የማልተወው ቅኔ የማልተወው ቦታ
የማልረሳው ልማዴ የሕይወቴ ተርታ
ከአንተ ጋር መሆን ነው መክረም ባለህበት
የህይወቴ ዋና የእስትንፋሴ ርዝመት
ከአንተ ጋር መሆን ነው መክረም ባለህበት
የህይወቴ ዋና የእስትንፋሴ ርዝመት

ካልደገፍከኝ የማልቆም ካልያዝከኝ የምወድቅ
ካልመራኸኝ የምስት ካላንተ የማልደምቅ
ሳትፈቅድልኝ የማልኖር የሆንክ እስትንፋሴ
ሁሉዬ ነህ እየሱሴ
ሳትፈቅድልኝ የማልኖር የሆንክ እስትንፋሴ
ሁሉዬ ነህ እየሱሴ

የሁሌ መናዬ ከላዬ የወረድህ
በደረቅ መሬት ላይ ነፍሴን ያረጠብህ
ከሙታኖች ሰፈር ትንፋሽ ከሌለበት
ሆንክልኝ ድልድዬ አብን የምደርስበት
ሆንክልኝ ገመዴ አብን የምደርስበት

ስምህን ጠራሁ ደስ አለኝ
ቃልህን በላው ደስ አለኝ
መንፈስህ አጽናናኝ ቀለለኝ
አብሬህ ዋልኩኝ ደስ አለኝ

አንተን አግኝቼ ሌላ መሄጃ አላስፈለኝ
አንተን ሰምቼ ሌላ የሚወራም አላስፈለገኝ
በአንተ ተጽናናሁ ሌላ ሲጨመር አላስደሰተኝ
ከአንተ ጋር ቆየሁ ሌላ የሚያጽናናም አላስፈለገኝ

ብቻህን በቃኸኝ....

| @GITIM_ALEM
| @GITIM_ALEM


አየሁ አንድ ፍቅር

ከዘመን ዘመናት
ከዘላለም በፊት
ካ'ምላክ ዘንድ የኖረ
አምላክ የነበረ

ኢየሱስ የሚባል የአብ ልጅ ነበረ
ክብር የሞላለት በአብ የከበረ
የፍጥረት ፈጣሪ የሁሉ ጀማሪ
ከጥንት የነበረ የዘላለም ኗሪ


መላዕክት ሚሰግዱለትም ጌታ ባለክብር
ራሱን አዋረደ መጣ ወደ ምድር
የሰውን ልጅ ሊያድን ከሀጢአት ቀንበር
አምላክ ተዋረደ አየሁ አንድ ፍቅር


Loading..........የኢየሱስ ልደት


ከወድሁ ተዘጋጁ ገናን በልዩ ሁነታ እናከብራለን

አቡ ነኝ እወዳችኋለሁ 😍

@gitim_alem


አንተ አናጢው...

አንተ አናጢ ፥ እኔ ሸንበቆ
ይላገኝ እጅህ ፥ ሲሻው ሰንጥቆ
ጎባጣ ስሆን ፥ ጥመት ቢበዛኝ
እሸኝ በመላህ ፥ እስክታወዛኝ።
:
በልክህ አቅናኝ...
በወራጅ ሳይሆን፥  በ'ጅህ ልሻገር
ልጣበቅ ካንተው ፥ ከልብህ ማገር ፤

ቅጣኝ ለመልካም ፥ መልምለኝ ለወ'ጥ
አንድ አይበቃኝም ፥ እስከምለወጥ
ቋሚ አ'ርገኝ ቆርጠህ ፥ ቅርንጫፎቼን
ብቻየን ልሁን ፡ እስበርራቸው ፥ ወረት ወፎቼን፤
:


#ከአዋዋል የተገጠመ ....😁
ኢየሱስም አናጢ ነበረ!

Like👍❤  share   React

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem            @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8


ትኩረት ሁሉ ወደ ኢየሱስ


ከአብትኩረት ከሆነው ከኢየሱስ በቀር
ከመንፈስ ቅዱስ ፈገግታ ከልጁ በቀር
ምን እምነት አለን
ምን ህይወት አለን
ምን መዝሙር አለን
ምን ስብከት አለን
ምን ትምህርት አለን
ምን ክርስትና ......
ምን ግጥም አለን
ከኢየሱስ ውጭ ምን እንላለን

እስት ኢየሱስ ቢላችሁ Comment ለይ ጻፉ

@gitim_alem


አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን
በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (፪x)

በመላክት እየታጀበ በእግዚአብሔር መለከት
ኢየሱስ ይመጣል ከላይ ከሰማያት
የአባቴ ብሩህ ቃል ኑ እረፉ ይለናል
እንደ ድካማችን ዋጋ ይከፍለናል
ተስፋ እንደሌላችሁ ፈጽሞ አትዘኑ
እርስ በእርሳችሁም በዚህ ቃል ተጽናኑ

አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን
በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (፪x)

በጌታ የሞቱ ቀድመው ይነሳሉ
ሰማያዊ አካል ፈጥነው ይለብሳሉ
እኛ ሕያዋን እንለወጣለን
አብረን በደመና እንነጠቃለን
ተስፋ እንደሌላችሁ ፈጽሞ አትዘኑ
እርስ በእርሳችሁም በዚህ ቃል ተጽናኑ

አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን
በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (፪x)

ዓለም በክፋቷ እየባሰች ሄደች
ሕያዋንን አልፋ በድን አሳደደች
አዲስ ነገር የለም ነው እንደተጻፈው
በክርስቶስ ትዕግስት ሁሉን እንለፈው
የሚረዳን ጸጋ ጌታ ይሰጠናል
ኋላም በመምጣቱ በክብር ይገልጠናል

አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን
በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (፪x)

ጌታ የሚዘገይ መስሎ ቢታያቸው
በዚህ ዓለም አምላክ ታውሮ ዐይናቸው
እንደ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም በእውነት
እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል በድንገት
የወጉት ያዩታል በዘውድ አሸብርቆ
በግርማው ሲገለጥ ከከዋክብት ደምቆ

አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን
በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (፪x)

ነቀፋና ስድብ ስደትና ዛቻ
የጠላት ተግዳሮት የዘመድ ጥላቻ
እጦትና ህመም ሃዘንና እሮሮ
ያለው የሚመጣው ሁሉም ተደምሮ
ይገለጥ ዘንድ ካለው ሰማያዊ ክብር
ያሁን ዘመን ስቃይ አይወዳደር

አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን
በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን


⚠️ ማሳሰቢያ !! ለዚህ ለቻናሉ አባላት በሙሉ 😊

እስቲ አንድ ጊዜ ሁላችሁም ከቻናላችን ስር ያለው Button ምን እንደሚል ተመልከቱ።

❌ #UNMUTE የሚል ከሆነ አንድ ጊዜ ተጫኑት። ከዛ #MUTE ላይ ይሆናል ማለት ነው።

✅ #MUTE የሚል ከሆነ ግን ምንም አትንኩትም ።

🔔 በየ ሰዓቱ አዳዲስ መንፈሳዊ ግጥሞ ስንፖስትላችሁ  Notification ይደርሳችኋል በተጨማሪም የዚህ ቻናል ቤተሰብ መሆናችሁ የሚታወቀው #Mute ✅ ላይ ሲሆን ብቻ ነው ፖስታችንም ብዙ እይታ ይኖረዋል ። 🔥

ስለ ትብብብርዎ እናመሰግናለን 🙏

➡️ Join @gitim_alem 🔔


ዝም ባልኩት ዘመን

እሳቱን አንድደው በእጅ ተጫወቱ
በረከሰ አንደበት ለላን አመነቱ
በፈጣር ፋንታ ፍጡርን ገንዘው
አቆሙት ልሰግዱ መጻፉን በርዘው
አንዱ በሞተበት አርባ አራት አመጡ
ያነሰ ይመስል ሰገዱ እያዋጡ
ከፈጣር ይልቅ ፍጡር ስያምርባቸው
አምስለው ሳሉበት አቅም ስያጥርባቸው
አንዱ በሞተበት ለላ ይመለካል
ከሰማይ መውረዱ በተረት ይለካል
አይምሰላቹ አሁን በዝህ ዘመን ጊዜ
በውሸት ተታሎ መከተል አባዜ
ለጳውሎስ የበራ ለኛም በርቶልናል
ከእናንተ ተረት ይልቅ እውነት ያዋጣናል


በድጋም የቀረበ


ይቀላቀሉ🥰

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem            @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8

Показано 20 последних публикаций.