“አዋጅ! #የጌታዬን_ንግግር ወደ ህዝቦቹ እንዳደርስ የሚወስደኝ ሰው ይኖራልን? ቁረይሾች የጌታዬን ንግግር እንዳላደርስ በርግጥም ከልክለውኛል።” [አቡ ዳውድ፡ 4734] [ቲርሚዚ፡ 2925] [ኢብኑ ማጀህ፡ 201]
በሃሰት “ብዙሃን ነን” እያሉ የሚጀነኑት አሽዐርዮች እምነታቸው ይሄ ነው፡፡ ቁርኣን በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም ማለት! ለምሳሌ ያክል
قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ ٱللَّهُ ٱلصَّمَدُ
የሚለውን የአላህ ንግግር ነው ያለ ሰው እልፍ አእላፍ እርግማን በሱ ላይ ይሁንበት እስከማለት የደረሰ አለ። ከዚህ ንግግር ስር ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ብለዋል፡-
بل على من يَقُول أَن الله عز وَجل لم يقلها ألف ألف لعنة تترى وعَلى من يُنكر أننا نسْمع كَلَام الله ونقرأ كَلَام الله ونحفظ كَلَام لله ونكتب كَلَام الله ألف ألف لعنة تترى من الله تَعَالَى فَإِن قَول هَذِه الْفرْقَة فِي هَذِه الْمَسْأَلَة نِهَايَة الْكفْر بِاللَّه عز وَجل وَمُخَالفَة لِلْقُرْآنِ وَالنَّبِيّ صلى الله عَلَيْهِ وَسلم وَمُخَالفَة جَمِيع أهل الْإِسْلَام قبل حُدُوث هَذِه الطَّائِفَة الملعونة
“እንዲያውም አላህ - ዐዘ ወጀል - እሷን አልተናገራትም ባለ ሰው ላይ እልፍ አእላፍ እርግማን ይውረድበት! እኛ የአላህን ንግግር እንደምንሰማ፣ የአላህን ንግግር እንደምናነብ፣ የአላህን ንግግር እንደምንሐፍዝ፣ የአላህን ንግግር እንደምንፅፍ በሚያስተባብል ላይም እልፍ አእላፍ እርግማን ከላቀው አላህ ተከታትሎ ይውረድበት! በዚህ ጉዳይ የዚች አንጃ (አሽዐርያ) አቋም በአላህ - ዐዘ ወጀል - ፣ በቁርኣን፣ በነብዩ ﷺ ላይ ጫፍ የደረሰ ክህደት ነው። ይቺ የተረገመች አንጃ ከመምጣቷ በፊት የነበሩ ሙስሊሞችን እንዳለ መፃረርም ነው።” [አልፈስል፡ 4/160]
ሆኖም ግን ይህን እምነታቸውን ሃገር እየመሩ እንኳን አደባባይ አያወጡትም። ይልቁንም እየተዋሸባቸው እንደሆነ ከፍ አድርገው ይጮሃሉ። እየዋሹ “ተዋሸብን!” ይላሉ፡፡ ወደ ጓዳቸው ሲመለሱ ግን “ቀለምና ወረቀት እንጂ ሌላ ምን አለው?” ይላሉ፡፡ የኢብኑ ቁዳማ (620 ሂ.) “አልሙናዞራ ፊል ቁርኣን” ኪታብ ይመልከቱ። [ገፅ፡ 34፣ 35] እንዲያውም “በትምህርት ጉባኤ ላይ ካልሆነ በስተቀር ቁርኣንን ፍጡር ነው ከማለት መቆጠብ ይገባል” የሚለው የአሽዐርዩ በይጁሪ ንግግር እዚህ ላይ ቁልፍ ምስክርነት ነው። [ጀውሀረቱ ተውሒድ፡ 72] [ቱሕፈቱል ሙሪድ፡ 94] ይሄ የበይጁሪ ኪታብ በሃገራችንም በሰፊው የሚታወቅ ነው።
በ2004 ይመስለኛል በፖሊስ የታጀቡ አሕባሾች በአንድ የሃገራችን ከተማ ውስጥ ህዝብ ሰብስበው “ቁርኣን የአላህ ንግግር አይደለም” ሲሉ ታዳሚው በመገንፈሉ ከ80 በላይ ወጣቶች ታፍሰው እስር ቤት ገብተው ነበር። ክስተቱን ለአንድ መሀል አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኝ የመስጂድ ኢማም ስነግረው ምን አለ መሰላችሁ? “ይሄ በህዝብ ፊት ይወራል እንዴ?!”
የሚለው ገብቷችኋል? ተስማሚ ቦታ መምረጥ ነበረባቸው እንጂ ነገሩ እንኳን እውነት ነው ማለቱ ነው። አስተውሉ! እያፈኑት እንጂ እምነታቸው ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለም የሚል የጥንቶቹ ሙዕተዚላ እምነት ነው። ባይሆን ቦታና ጊዜ እየተመረጠ እንጂ አያወጡትም፡፡ ጥሬዎቹ ግን “ሒክማ” ያጥራቸውና “ቁርኣን የአላህ ንግግር አይደለም” እያሉ ባደባባይ በመጮህ እርቃናቸውን ከህዝብ ፊት ይቆማሉ። አሁን አሁን ካለፈው ስህተታቸው የተማሩ ይመስላሉ። በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ድምፃቸውን አጥፍተው በተሕፊዝ ማእከላት ውስጥ መርዛቸውን እየረጩ ነው። ወገኔ ሆይ! ልጆችህ የት ነው የሚማሩት? ቁርኣን ይሐፍዝልኛል ብለህ የላከው ልጅህ በቁርኣን ክዶ እንዳይመለስ ተጠንቀቅ!
ይህን እምነታቸውን ከህዝብ ለመደበቃቸው የሚያነሱት ምክንያት “ህዝቡ ይህን ካወቀ ለቁርኣን ያለው ክብር ይቀንሳል” የሚል ነው። ስለዚህ እምነታቸው እንዲህ አይነት አደጋ አለው ማለት ነው። ከአማኞች ልቦና ውስጥ የቁርኣንን አክብሮት ማጥፋት፡፡ በእርግጥ የሚደብቁበት ሌላ ወሳኝ ምክንያት አላቸው። እሱም ለቡድናቸውም ለህይወታቸውም ህልውና መስጋት ነው። ህዝበ ሙስሊሙ ከነ ድክመቱ በቁርኣን ላይ ያለው እምነት ከአለት የጠነከረ ነው። በቁርኣኑ ለሚመጣ ህይወቱን አሳልፎ ይሰጣል። በ521 ሂ. አሽዐርዩ አቡል ፈቱሕ አልኢስፊራይኒ በብልሹ ዐቂዳው የተነሳ በኸሊፋው ትእዛዝ ከባግዳድ ሲባረር ከባልደረቦቹ አንዱ ዘንድ የቁርኣንን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ነገር በመገኘቱ መቀጣጫ አድርገው በከተማ አዙረውታል። እንዲያውም ህዝቡ ተከልክሎ እንጂ በቁሙ በእሳት ሊያቃጥለው ነበር። [ዘይል፡ 1/388] አሕባሽም ቢሳካለት ይህንን ክህደት ነው ለህዝባችን ሊግት ቆርጦ የተነሳው፡፡ ለጊዜው አቅሙ ስለሳሳ ነው ብዙ ጉዱቹን ደብቆ ተዋሸብኝ የሚለው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 27/2012)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor