✍
አንዳንድ ሰው አለ……
እሱው በበደለው እሱው ረጋሚ
ለገዛ ጥፋቱ ይቅርታን አላሚ
መጥቀም እየቻለ ለመጉዳት የሚጥር
አብሮህ እየሳቀ ክፋት የሚቋጥር
መምከር እየቻለ ሀሜት የሚያወጋ
አልጋ እየሆንክለት ደርሶ ሚሆን ቀጋ
አንዳንድ ሰው አለ………
በደስታህ ተገኝቶ ለችግር የሚሮጥ
ከጎንህ ለመሆን ቀን ጊዜ የሚመርጥ
እንቅልፍ የሚነሳው ብርታትህ ጥንካሬህ
ብስጭት የሚያደርገው ሲያየው ስኬትህ
አብሮህ እየኖረ በውሎና አዳሩ
የማይገኝ ሆዱ የበዛ ሚስጥሩ
አዎ አለ አንዳንድ ሰው………
እንዲህ የማትለው የማይገባህ ፍፁም
ሰአት ስጠይቀው ሰፈር የሚጠቁም።
ይሰውራችሁ
https://t.me/hamdquante
አንዳንድ ሰው አለ……
እሱው በበደለው እሱው ረጋሚ
ለገዛ ጥፋቱ ይቅርታን አላሚ
መጥቀም እየቻለ ለመጉዳት የሚጥር
አብሮህ እየሳቀ ክፋት የሚቋጥር
መምከር እየቻለ ሀሜት የሚያወጋ
አልጋ እየሆንክለት ደርሶ ሚሆን ቀጋ
አንዳንድ ሰው አለ………
በደስታህ ተገኝቶ ለችግር የሚሮጥ
ከጎንህ ለመሆን ቀን ጊዜ የሚመርጥ
እንቅልፍ የሚነሳው ብርታትህ ጥንካሬህ
ብስጭት የሚያደርገው ሲያየው ስኬትህ
አብሮህ እየኖረ በውሎና አዳሩ
የማይገኝ ሆዱ የበዛ ሚስጥሩ
አዎ አለ አንዳንድ ሰው………
እንዲህ የማትለው የማይገባህ ፍፁም
ሰአት ስጠይቀው ሰፈር የሚጠቁም።
ይሰውራችሁ
https://t.me/hamdquante