🌙
የሰሁር በረካ እና ቱሩፋቶች……… አነስ ኢብኑ ማሊክ ባስተላለፈው ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ ይላሉ፦
«تَسَحَّرُوا فَإِنَّ في السُّحُورِ بَركَةً»
«ሰሁርን ተጠቀሙ (ብሉ) በሰሁር ላይ በረካ አለበት።» ዐምር ኢብኑል ዓስ ባስተላለፈው በሌላ ሐዲስ እንዲህ ይላሉ፦
«إِنَّ فَصْلَ مَا بَيْنَ صِيَامِنَا وَصِيَامِ أَهْلِ الْكِتَابِ أَكْلَةُ السَّحَرِ »
«በእኛ ጾም እና በአህለል ኪታቦች ጾም መሃል ያለው ልዩነት ሰሁርን መብላት ነው» በሌላ ሐዲስ አንድ የመልዕክተኛው ባልደረባ ቀጣዩን ክስተት ይጠቅሳል፦
"دخلت على رسول الله عليه الصلاة والسلام وهو يتسحر، فقال: «إنها بركة أعطاكم الله إياها؛ فلا تدعوه»"
"የአላህ መልዕክተኛ ሰሁር እየተጠቀሙ ሳለ ገባሁባቸው። እንዲህም አሉኝ «እሷ (ሰሁርን) በረካ ናት; አላህ ሰጥቷችኋልና እንዳትተዋት»" ከእነዚህ እና ካልተጠቀሱ ሐዲሶች በመነሳት ሰሁር መጠቀም ያለው በረካ እና ተወዳጅነት ምን ያህል እንደሆነ ዑለሞች ከሚጠቅሷቸው ነጥቦች ውስጥ……
🧆
ሰሁርን መጠቀም👇🏾
💫
አንደኛ; የመልእክተኛውﷺ ሱና መከተል ነው።
💫
ሁለተኛ;
አህለል ኪታቦችን መቃረን ነው።
💫
ሶስተኛ;
ዒባዳ ለመስራት ያጠናክራል።
💫
አራተኛ;
ነሻጣ ይጨምራል።
💫
አምስተኛ;
በረሀብ ምክንያት የሚከሰቱ አላስፈላጊ ስነ ምግባሮች እና ስሜቶችን ይከላከላል።
💫
ስድስተኛ;
በሰሁር ወቅት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰደቃ ለማድረግ ያመቻቻል።
💫
ሰባተኛ;
ወቅቱ ዱዓ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ የሚከጀልበት ወቅት ከመሆኑ አንፃር በዚህ ወሳኝ ወቅት ዱዓ ለማድረግ ይጋብዛል።
💫
ስምንተኛ;
ድንገት ኒያን ያላስገኘ (የረሳ) ሰው ከነበረ ኒያውን ያስገኝ ዘንድ ይረዳዋል።
🖊
ከፉርቃን ሰማይ ስርhttps://t.me/hamdquante