✍
የእስራኤል ካቢኔ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በዛሬው እለት የሚያጸድቀው ከሆነ ከእሁድ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።
በረቂቅ ሰነዱ ላይ እስራኤል ማሻሻያ ካላደረገች በስተቀር በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለው የጋዛ ተኩስ አቁም እና የታጋቾች ማስለቀቅ ስምምነት ቀጣዩን እንደሚመስል አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
ምዕራፍ 1 (42 ቀናት)
-ሃማስ 33 ታጋቾችን ይለቃል፤ የሚለቀቁት ታጋቾች ሴቶች፣ ህጻናት እና ከ50 አመት በላይ የሆናቸው እስራኤላውያን ይሆናሉ
- እስራኤል ከጋዛ አንድ ሲቪል ታጋች ሲለቀቅ በምትኩ 30 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ትፈታለች፤ አንዲት ሴት ወታደር ስትለቀቅ ደግሞ 50 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ትፈታለች
- ሃማስ የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ በሚደረግበት የመጀመሪያ ቀን ሶስት ታጋቾችን ይለቃል፤ በሰባተኛው ቀን አራት ከለቀቀ በኋላ በየሳምንቱ ታጋቾችን ይለቃል
- ውጊያ ቆሞ እስራኤል ወታደሮቿን ህዝብ በብዛት ወደማይኖርበት የጋዛ ሰርጥ ታሰፍራለች
- የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን ወደ ቤታቸው መመለስና ሰብአዊ ድጋፍ በፍጥነት እንዲገባ ይደረጋል
ምዕራፍ 2 (42 ቀናት)
- ሃማስ ቀሪ ወንድ ታጋቾችን (ወታደሮች እና ሲቪሎች) ይለቃል
- እስራኤል በምትኩ ምን ያህል ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትለቅ በቀጣይ ድርድር ይደረግበታል ተብሏል
- የእስራኤል ወታደሮች ከጋዛ ሙሉ በሙሉ ይወጣሉ
ምዕራፍ 3
- በጋዛ የሞቱ እስራኤላውያን ታጋቾች እና በእስራኤል ህይወታቸው ያለፈ የፍልስጤም ተዋጊዎች አስከሬን ልውውጥ ይደረጋል
- ጋዛን መልሶ የመገንባት ስራ ይጀመራል
- ከጋዛ መግቢያ እና መውጫ መስመሮች ሙሉ በሙሉ ይከፈታሉ
https://t.me/hamdquante