በትክክል የኦርቶዶክስ አማኝ የሆነ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ያከብራል። አዋልድ መጻሕፍትንም ያከብራል። ቃላቸውን ይሰማል ያምናል። ነገር ግን እኛ አናምንም። እምነቱ የለንም።
አዋልድ መጻሕፍትን ስናነብ መጽሐፈ አክሲማሮስ ምድር ዝርግ ናት ይላል። እግዚአብሔር ምድርን እንደ ቄጤማ ባሕሩ ላይ አንጥፎ፣ ጎዝጉዞ ፈጠራት ይላል። ፀሐይን ከእሳት፣ ጨረቃን ከውሃ ፈጠራቸው፣ ሁለቱንም ሰሌዳ አድርጎ ፈጠረ ይለናል።
የአባ ጊዮርጊስን መጽሐፍ ስናነብ እግዚአብሔር ፀሐይና ጨረቃን እንደ ክብ መስታወት አደረጋቸው ይላል። ምድርን በውሃ ትከሻ ላይ አስቀመጣት፣ ፀሐይና ጨረቃን በነፋስ ሰረገላ እየመራ በሰማይ ላይ እንዲመላለሱ አደረጋቸው ይለናል።
ስለ ዓለም አፈጣጠር ለማወቅ ከነዚህ መጻሕፍት በላይ መረጃ የሚሆነን አይኖርም ነበር። እምነቱ ቢኖረን ኖሮ።
እኛ ግን እምነቱም እውቀቱም ስለ ሌለን የፈረንጅን ቲዎሪ በጭፍን እንከተላለን። ያውም በቀላሉ disprove የሚሆንን ቲዎሪ። በራሱ በሳይንስ መመዘኛ እንኳ ውድቅ የሆነውን የፈረንጅ ውዳቂ ቲዮሪ እናሳድዳለን።
በራስ እጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ነውና የሚቆጠረው፤ በሰው እጅ ያየነውን መዳብ ከወርቅም በላይ አድርገን እሱን ማምለካችን እጅግ አሳዛኝ ነው።