ከጥሩ ጋር ዋል ጥሩ ትሆናለህ..!
አንድ አባት ከስራ ቦታው ሲመለስ ልጁን ከቦዘኔ ልጆች ጋር ሲጫወት ያየዋል ልጁን ጠራውና ልጄ ተው ከነሱ ጋር አትዋል ያበላሹሀል አለው። ''ኧረ አባቴ እኔ ከነሱ ጋር ጨዋታ ብቻ ነው ምጫወተው እነሱ ሚሰሩትን መጥፎ ስራ አልሰራም'' ሲል መለሰለት እና በተደጋጋሚ ቢመክረውም እንቢታውን ቀጠለበት። አባት ከቀናት ቡሀላ ከስራ ሲመለስ በካኪ ወረቀት የሆነ ነገር ይዞ መጣ እና እንካ ሳጥን ላይ አስቀምጠው ብሎ ሰጠው።
ልጁም አባቱ ያመጣውን ለማየት ጓጓና ከፍቷ አየው ልጁ ተደሰተ ያለበሰለ ፖም ነበር በዛ ላይ አንዷ ፍሬ ተበላሽታለች አና ላውጣት ተበላሽታለች ሲል አባቱን ጠየቀው አይ ተወው ዝም ብለህ አስቀምጠው አለው። እናም ከሳምንት በኋላ እስቲ ያንን ያስቀመጥከውን ነገር አምጣው አለው እናም ልጁ በጉጉት ይጠብቅ ስለነበር ደስ አለው ፖም እንደሚወድም ስለሚያቅ ልጁም ተስፈንጥሮ ተነስቷ አመጣና በጉጉት እና በተስፋ ካኪውን ከፈተው።
ነገር ግን ሁሉም የፖም ፍሬዎች ተበላሽተው ነበር ልጁ በጣም ተናደደና አየሀ አባዬ ያኔ የተበላሸውን የፖም ፍሬ ላውጣው ስለህ እሺ ብትለኝ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም አለው አባትም ሌላ ካኪ ወረቀት አመጣና ሰጠው አሁንም ደስ ብሎት ከፍቶ ሲያይ ፖም ነበር ነገር ግን አባቱ አሁንም ያመጣው አልበሰለም እና ልጅ አልበሰለም እኳ ሲል ጠየቀው አባትም አዎ ሂድ ሳጥኑ ላይ አስቀምጠው አለው ልጅም እሺ ብሎ ከማስቀመጡ በፊት የተበላሸ እንደሌለው አረጋግጦ አስቀመጠው።
አሁንም ከሳምንት ቡሀላ አባት እስቲ ያንን ነገር አምጣው አለው ልጅም በደስታ እና በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆኖ ካኪውን አመጣው የፈራው እንደበፊቱ እንዳይበላሽ በመስጋቱ ሲሆን ደስ ያለው ደሞ ፖም ስለሚወድ ነበር እና ልጅ ካኪውን ከፈተው ማሻአላህ ሁሉም ሳይበላሽ በስለው ነበር ልጅም በጣም ደስ ተሰኘ እና አባት ያኔ ፖም ለምን የተበላሸ ይመስልሀል? ሲል ጠየቀው ልጅም "አንዱ ተበላሽቶ ስለነበር ሁሉንም አበላሻቸው እኔ ላውጣው ስልህ ባወጣው ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር" አለው።
አባትም "አየህ እኔም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ምልህ ለዚ ነው ልክ እንደ ፖሙ ሁሉ አንተንም በጊዜ ሂደት እንዳያበላሹህ ነው የተበላሸውን ፖም ላውጣው ስትለኝ አውጣው ብልህ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር አንተም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ስልህ ካልዋልክ አትበላሽም ነገር ግን የኔን ምክር ችላ ብለህ ከነሱ ጋር ከዋልክ በጊዜ ሂደት እንደነሱ መሆንህ አይቀርም : በሌላ ቀን የመጣሁት ፖም ደግሞ ያልተበላሸው በአጠገቡ የተበላሸ ነገር ሰለሌለ ነው ከጥሩ ነገር ጋር ስላለ ነው ሰለዚህ አንተም ከጥሩ ጋር ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ"። "ከጥሩ ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ: ከመጥፎ ጋር ከዋልክ መጥፎ ትሆናለህ።
@heppymuslim29