Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates. This page is not a gov't page.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የቢሮው ማሳሰቢያ!!

በተለምዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ከወዲሁ እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራ የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩ ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ካሳዬ እንደገለፁት በመዲናዋ 429 ሺህ 829 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል፡፡
ይሁንና እስካሁን ባለው ሂደት 228 ሺህ 222 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር መፈፀማቸውን በመግለፅ ይህም የዕቅዱ 51 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የቤትና ቦታ ግብራቸውን ከከፈሉ ግብር ከፋዮችም 2 ነጥብ 24 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
እንደሚታወቀው የቤትና ቦታ ግብር ከአዋጅ ከ1968 ጀምሮ በተለምዶ የአፈር፣ የቤትና ጣሪያ በሚሉና መሰል ስያሜዎች እስከ የካቲት 30 ድረስ የሚሰበሰብ የግብር አይነት መሆኑ ይታወቃል፡፡
(አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ)

16.5k 0 177 40 182

አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአጠቃላይ 45 አባላት ያለው ሲሆን 10 ሴቶችን አካቷል።

#ኦሮሚያ_ክልል

1. ዶክተር ዐቢይ አህመድ
2. ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
3. ኦቦ አወሉ አብዲ
4. ኦቦ ፍቃዱ ተሰማ
5. አዴ አዳነች አቤቤ
6. አዴ ጫልቱ ሳኒ
7. ኦቦ ሳዳት ነሻ
8. ኦቦ ከፍያለው ተፈራ
9. ዶክተር ተሾመ አዱኛ
10. ዶክተር እዮብ ተካልኝ

#አማራ_ክልል

11. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
12. አቶ መላኩ አለበል
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
14. አቶ አረጋ ከበደ
15. አቶ ይርጋ ሲሳይ
16. ዶክተር አብዱ ሁሴን
17. አቶ ጃንጥራር አባይ
18. ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ

#ሶማሌ_ክልል

19. አቶ አደም ፋራህ
20. አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
21. አቶ አህመድ ሺዴ
22. ወ/ሮ ሃሊማ ዋሽራፍ

#ትግራይ_ክልል

23. ዶክተር አብርሃም በላይ
24. አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር

#ሀረሪ_ክልል

25. አቶ ኦርዲን በድሪ
26. ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም

#አፋር_ክልል

27. ሀጂ አወል አርባ
28. መሀመድ ሁሴን አሊሳ
29. መሀመድ አህመድ አሊ

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ_ክልል

30. ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
31. አቶ ፍቅሬ አማን

#ሲዳማ_ክልል

32. አቶ ደስታ ሌዳሞ
33. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
34. ዶክተር ፍፁም አሰፋ

#ጋምቤላ_ክልል

35. ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ
36. ዶዶክተር ካትሏክ ሩን ናቸው።

#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ_ክልል

37. አቶ አሻድሊ ሀሰን
38. አቶ ጌታሁን አብዲሳ

#ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል

39. አቶ እንዳሻው ጣሰው
40. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
41. ዶክተር ዴላሞ ዶቶሬ

#ደቡብ_ኢትዮጵያ_ክልል

42. አቶ ጥላሁን ከበደ
43. ወ/ሮ ⁠ሸዊት ሻንካ
44. ዶክተር ተስፋዬ ቤልጅጌ
45. ዶክተር አበባየሁ ታደሰ

16.8k 0 74 10 181

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ወይ አዲስ አበባ...

21k 0 120 25 126

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አዲሱ የቤቶች ፋይናንስ ስረአት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram

43.1k 0 437 45 135

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር ያስከተለው ምስቅልቅል እና ምሬት

(መሠረት ሚድያ)- ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በተለይ ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻ ከተደረገ ወዲህ የኑሮ ውድነት ተባብሶ ቀጥሏል።

የመገበያያ ዋጋቸው እጅግ እየጨመሩ ከመጡ ምርቶች አንዱ ነዳጅ ነው። የዛሬ ሁለት አመት በዚህ ወቅት ቤንዚን በሊትር 61 ብር ነበር፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ይሸጥ ነበር፣ ኬሮሲንም በሊትር 67 ብር ነበር።

አሁን ላይ ቤንዚን 101 ብር ከ47 ሳንቲም ገብቷል፣ ናፍጣ ደግሞ በሊትር 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፣ በሌሎች የነዳጅ ምርቶች ላይም በትንሹ ከ8 ብር በላይ ተጨምሯል።

ታድያ የዚህ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ የህዝብ ትራንስፖርቱ ዋጋም በእጅጉ እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኗል። በተለይ በተለይ በአዲስ አበባ ዳርቻ አካባቢዎች በሰፈሮችና በኮንዶሚኒየምዎች የሚኖሩ ዜጎች ለትራንስፖርት የሚያወጡት ወጪ እጅግ በጣም ጨምሮ ኑሮን እንዳከበደባቸው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

ለምሳሌ በኮዬ ፈጬ፣ በአራብሳ፣ በቂሊንጦ፣ በቱሉዲምቱ ወዘተ... የሚኖሩ ዜጎች ከነዚህ መኖሪያ መንደሮች እስከ መገናኛ እንኳን ለመድረስ በአውቶብስ 20 ብር፣ በታክሲ ደግሞ 50 ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

"ወቅታዊ ታሪፉ ደርሶ መልስ በአውቶቡስ 40 ብር፣ በታክሲ 100 ብር ነው መገናኛ ድረስ ብቻ። እኛ ግን አልፈን ሄደን መሀል ከተማ ነው የምንሰራው፣ ለትራንስፖርት ብቻ በቀን እስከ 130 ብር በትሹ እናወጣለን" በሚል አስተያየት የሰጡት እነዚህ ዜጎች ይህንንም ለማግኘት ብዙ ተሰልፈው እና ተንገላተው እንደሆነ ያስረዳሉ።

"ይሄ እጅግ በጣም ኑሮአችንን አክብዶብናል፣ ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል። አቤቱታችንን በሚዲያችሁ አስተላልፉልን፣ የሚመለከተው አካል መፍትሔ ሊሰጠን ይገባል" የሚሉት እነዚህ ዜጎች የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ መነሳት ላልተጠበቀ እና እጅግ አቅምን ለሚፈታተን ከባድ ወጪ እንደዳረጋቸው በምሬት ይናገራሉ።

"በአንድ ቤት ውስጥ ብቻ ስራ ለመሄድ፣ ልጆችን ት/ቤት ለማድረስ እንዲሁም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን እንቅስቃሴ ሳይጨምር ለአንድ ሰው  ይሄን ያህል ወጪ በቀን እያወጡ እንዴት መኖር ይቻላል?" በማለት አስተያየታቸውን በጥያቄ ቋጭተዋል።

መረጃን ከመሠረት!

@MeseretMedia


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Perfect idea to reduce time and traffic jams

32.3k 0 12 11 153

ዛሬ በመንግስት እና ግል አጋርነት መርሀ ግብር ከአያት አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር የ13,752 ቤቶች ግንባታን አስጀምረናል::

በካዛንቺስ አካባቢ ከኦቪድ ግሩፕ ጋር ካስጀመርነው ጋር ከ15 ሺሕ በላይ ቤቶችን የምናለማ ሲሆን ቅድሚያ የማልማት መብታቸውን በመጠቀም የሚገነቡ የግል አልሚዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 20 ሺሕ ቤቶችን የሚገነቡ ይሆናል::

በከተማችን ያረጁ እና ለመኖር ምቹ ያልሆኑ እንደ ካዛንቺስ ያሉ አካባቢዎችን መልሰን ስናለማ በዋነኛነት የህዝቡን ዋንኛ  አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤትን ለመመለስ ሲሆን የመኖሪያ ቤቶችን ስንሰራ ቤት ብቻ ሳይሆን ለኑሮ ምቹ የሆነ አካባቢዎችን እንገነባለን::
ካሳንችስ ከመልሶ ማልት በፊት ነባር 8000 መኖሪያና ንግድ ቤቶች በጥቅሉ ወደ 21ሺ ነዋሪዎችን የሚገለገሉበት አካባቢ የነበረ ሲሆን በመልሶ ማልማት ስራችን  ሁለት ሺሕ የንግድ ሱቆች እና ሀያ ሺሕ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ከ100 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች የሚገለገሉበት አካባቢ ይሆናል።

ካዛንቺስ ላይ የምንገነባው ይህ የካዛንቺስ አያት መንደር በውስጡ ማህበራዊ ግልጋሎትን የሚሰጡ ተቋማት ጨምሮ የመማሪያ ቦታዎች፣ የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ አረንጏዴ ቦታዎች፣ ሞሎች፣ ሱቆች እንዲሁም ሰፋፊ የመኪና ማቆሚያዎችን ያካተተ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ነው::

በሚቀጥሉት 18 ወራት ጊዜ ውስጥ የ15 ሺህ ቤቶች ግንባታን ለማጠናቀቅ ያቀድን ሲሆን ሁላችንም ለፕሮጀክቱ ስኬት በጋራ እንድንሰራ አደራ እያልኩ ንጹህ፣ ፅዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተወዳዳሪ የሆነች አለም አቀፍ ከተማ መገንባታችንን አሁንም አጠናክረን ቀጥለናል::

ያስጀመረን ፈጣሪ በድል እንድናጠናቅቅ ይርዳን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

24.1k 0 63 36 239



Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram

37.6k 0 48 23 121

የንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል?

ዜጎች የሚከፍሉት የግብር መጠን የሚወሰነው ባለፈው ታኅሳስ በጸደቀው የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት እና ግመታ አዋጅ መሠረት ነው። ይኸ የግብር አይነት አንድ ንብረት ከዓመት ዓመት በሚያሳየው የዋጋ ለውጥ ላይ የሚጣል ነው።

በአዋጁ መሠረት የንብረት ታክስ የሚከፈልበት ከአንድ ንብረት የገበያ ዋጋ 25 በመቶው ብቻ ነው። ይሁንና የገንዘብ ሚኒስቴር በጥናት ላይ በመመሥረት ታክስ የሚከፈልበትን ዋጋ ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል።

አቶ ደሳለኝ ወዳጄ “ለቤት ከ0.1 በመቶ እስከ 1 በመቶ፤ ለመሬት ደግሞ ከ0.2 በመቶ እስከ 1 በመቶ” የንብረት ታክስ እንደሚከፈል አስረድተዋል። “የትኛውም ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ሲጀምር ከ0.1 በመቶ ነው” ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ “በአራተኛው ዓመት ላይ የመጨረሻው ላይ መድረስ አለበት” ሲሉ ሒደቱን አስረድተዋል።

“20 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቤት ያለው ሰው በዓመት አንድ ጊዜ ክፍያው 5,000 ብር ነው ሊሆን የሚችለው” ብለዋል።

10 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ቤት 2,500 ብር፤ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቤት 1,250 ብር፤ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ቤት ያለው 250 ብር ሊከፍል እንደሚችል ተናግረዋል። የንብረት ባለቤቶች ክፍያውን በአንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ማከናወን ይችላሉ።

የፌድራል እና የክልል መንግሥታት ተቋማት የንብረት ታክስ አይከፍሉም። “ለሕብረተሰቡ ነጻ የማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ለዚሁ አገልግሎት የሚጠቀሙበት ቦታ እና ሕንጻ” ከንብረት ታክስ ነጻ ሆኗል። የኃይማኖት ተቋማት ለአምልኮ እና ለመካነ-መቃብር አገልግሎቶች የሚጠቀሙባቸው ቦታዎች እና ሕንጻዎችም ተመሳሳይ ዕድል አግኝተዋል።

አዩዘሀበሻ

38k 0 178 19 152

አሽከርካሪዎች በቀን እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ እንደሚከፍሉ በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአዲስ አበባ ኮሪደሮች ላይ የሚጠየቀው የመኪና ማቆሚያ ዋጋ የሕብረተሰቡን አቅም  ያላገናዘበ እንደሆነ ጥናት ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ጥናት በፒያሳ ፣ በቦሌ ፣ በአራት ኪሎ ያሉ አራት የኮሪደር መንገዶችን ላይ ባሉ የመኪና ማቆሚያዎች ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን  በቀን  አሽከሪከዎች ከ40 እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ ወጪ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ በቀን ለመኪና ማቆሚያ የማያወጡት ብር አቅማቸውን ያላገናዘበ እንደሆነ ተናግረዋል።

አንድ ወር የፈጀው ጥናት በእነዚህ ኮሪደር መንገዶች የእግረኛም ሆነ የመኪና ፍሰቱ ቀልጣፋ መሆኑን ከ400 የጥናቱ ተሳታፊዎች 65 በመቶ የሚሆኑት የገለጹ ቢሆንም የመንገድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና የመኪና መጨናነቅን ቀንሷል ብሎ ቢያመላክትም ከንግድ ሱቆችና ከመኖሪያ ቤቶች መፍረስ እግረኛንም ሆነ የመኪናን ቁጥር ከመቀነሳቸው ጋር ያያያዘው ነገር የለም ተብሏል፡፡

ጥናቱን ያጠኑት ሻካ አናላይቲክስ ከ አለም አቀፍ የቢዝነስ ልማት  ጋር በመተባበር ሲሆን የቢዝነስ ልማቱ  በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ አሰፋ " ጥናቱ ያተኮረባቸው ኮሪደሮች  ከፒያሳ አራት ኪሎ ፣ ከአራት ኪሎ እንግሊዝ ኤንባሲ ፣  ከአራት ኪሎ ቦሌ ድልድይና   ከሜክሲኮ ሳርቤት እንደሆነና  አጠቃላይ ጥናቱ አንድ ወር ፈጅቷል" ማለታቸው ተገልጿል፡፡

32.8k 0 23 15 119

Gondar Castle’s New Look: A Restoration Raising Eyebrows!
———————————-
(Note: This is not politics)

The restoration of Gondar Castle has caused public curiosity. The castle, known for its yellowish appearance, seems so much whiter now, and many wonder why.

I have visited the castle multiple times and had the opportunity to supervise several conservation studies on it conducted by my MSc students at AAU.

Here are a few points from a professional perspective:

1) Using new lime mortar in the restoration resulted in a generally whiter color, which will gradually turn light yellow over time.

2) The stone surfaces, which algae and lichens had darkened before restoration, were cleaned during restoration, resulting in a new whitish look.

3. The difference in lighting—Pictures taken at different times and in different lighting can significantly change the color.

Limestone buildings turn yellow over time as iron impurities oxidize when exposed to moisture and air.
Yohanes Mokenen

37k 0 22 4 147


35k 0 186 30 50

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በቦሌ ለሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ይስተዋል የነበረውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ የተከናወነ የማስፋፊያ ስራና በአካባቢው የሚገኙ ደንበኞች አስተያየት !


የት ነው?

Показано 20 последних публикаций.