በደብረብርሃን ከተማ በ2012 በጀት ዓመት ብቻ በ504 ባለሀብቶች 31. 6 ቢሊዮን ብር ያህል ኢንቨስት ተደርጓል፡፡
በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /10/2013 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ውስጥ በፈጣን የኢንዱስትሪ ግስጋሴ ላይ ከሚገኙ ከተሞች የደብረ ብርሃን ከተማ በቀዳሚነት ይጠቀሳል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኝና በመካከለኛ ከተማ አስተዳደር ደረጃ ያለች ስትሆን፣ ከከልሉ ርዕሰ ከተማ ባሕር ዳር 695 ኪ/ሜ፤ ከፌደራሉ ከተማ አዲስ አበባ ደግሞ 130 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ ከባሕር ጠለል በላይ 2,700 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡
የከተማዋ ስፋት 18,000 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፣ በከተማው ፕላን የተካተተው ከማስፋፊያው ውጭ 5,711 ሄክታር ይሸፍናል፡፡ የቦታውም አቀማመጥ 86 በመቶ ሜዳማ፤10 በመቶ ዳገታማና 4 በመቶ ተራራማ የሆነና ከዚህም ውስጥ 95 በመቶ ለግንባታ ምቹ የሆነ ቦታ ነው፡፡
የከተማዋን አየር ንብረት ስንመለከትም በቀዝቃዘማ አየር ንብረት ብትታወቅም አሁን ላይ ቀዝቃዛነቱ እየቀነሰ የመጣ፤ በአማካይ 14.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሙቀትና 964 ሚሊ ሜትር አመታዊ የዝናብ መጠን ያለት ከተማ ነች፡፡
ከአስተዳደራዊ አደረጃጀት አንጻር ሲታይም ከተማዋ በ9 የከተማና በ5 የገጠር ቀበሌ አስተዳደርና በ19 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተዋቅራለች፡፡
የከተማው ህዝብ የተሰማራበት የሥራ መስክ በአብዛኛው በንግድና በግብርና ሲሆን ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢንዱስትሪዎች እየተመሙባት የምትገኝ ከተማ እንደሆነች መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስካጅ አቶ ኃይለማርያም ንጉስ ከተማዋ ለአዲስ አበባ ካላት ቅርበት፤ ምቹ አየር ንብረት፤ ሠላማዊና ሥራ ወዳድ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ በመሆኗ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ በኢንቨስተሮች ተፈላጊ ከተማ እንድትሆን አስችሏታል ያሉት ም/ ሥራ አስካጁ እስከ 2012 በጀት ዓመት መጨረሻ ብቻ በ504 ባለሀብቶች 31ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ያህል ኢንቨስት እንደተደረገ ተናግረዋል፡፡
ኢንቨስትመንቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሌሎች ባለሀብቶች ወደ ከተማ መስተዳድሩ በብዛት መምጣት እንዲችሉ መስተዳድሩ ከምንጊዜውም በላይ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በቅንነት በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ ኃ/ማርያም ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ኢንቨስትመንቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ለበርካታ ዓመታት ሲጓተት የነበረው የመሠረተ ልማት አገልግሎት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ አዳዲስ የምስረታ ሠፈሮችን ከነባሩ ሠፈር ጋር ለማገናኘት የመሠረተ ልማት አውታሮችን በዋናነት መንገድ ዝርጋታ፤ ውሃና መብራት መስመር አቅርቦት እየሠራ ይገኛል ብለዋል አቶ ኃለማርያም፡፡
መሠረተ ልማት ለአንድ ሀገር ህዝብ ዕድገት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንደ ደም ሥር የሚታይ ነው ያሉት አቶ ኃ/ማርያም በመሠረተ ልማት መጓተት ምክንያት ኢንቨስትመንቱ እንዳይስተጓጎል ከተማ አስተዳደሩ በራሱ በሚሰበስበው፤ በክልሉና በዓለም ባንክ በጀት በመጠቀም የመሠረተ ልማት አውታሮችን እየገነባ ይገኛል ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በደብረብርሃን ከተማና በዙሪያዋ እየተገነቡ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የከተማዋ ህብረተሰብ ታላቅ ተስፋን የሰነቀ በመሆኑ መስተዳድሩም አስፈላጊ የመሰረተ ልማቶችን ለማሟላት የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል እንላለን፡፡
መረጃውን ያደረሰን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ነው።
@bernosmedia24