hulumale.com / ሁሉም አለ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


www.hulumale.com ሁሉም አለ የመገበያያ ድረ ገጽ ሲሆን ሁሉንም አይነት የንግድ አይነቶች እንዲያካትት ተደርጎ የተገነባ ነው

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ሻተር ፈላጊ ደንበኞች ጋልቫናይዝድ ሻርፕ 08 ይዘዙን


ሻተር በር ማሰራት ይፈልጋሉ ?
#በሪሞት እና ያለሪሞት የሚከፈቱ ሻተሮች

*የተለያዩ አይነቶች ሻተሮችን በተለየ ጥራት አቅርበንሎታል።

በሚፈልጉት መጠን, ከለር ,አንዲሁም ዲዛይን
ይዘዙን እናቀርብሎታለን።

👉ቤቶን 🏠
👉ህንፃዎን 🏨
👉ሱቅ 🏢
*መጋዘኖን ባስተማማኝ ሻተር ያስውቡ

🚧ሪሞት ኮንትሮል ሻተር
(REMOTE CONTROL SHUTTER)
⚙️ተጠቅላይ ሻተር
(ROLLING SHUTTER)

*ከ 2 አመት ዋስትና ጋር!

መለያችን ጥራታችን ነው።

በ 0911456794 / 0900066000 ይደውሉ
በስራችን ይረካሉ😁


የመኪና ማቆሚያ ጥላ Carport shade ማሰራት ይፈልጋሉ ???
በዚህ ሳምንት #ለቡ_ሙዚቃ_ቤት አካባቢ በጥሩ ሁኔታ ሰርተን ያስረከብነው ነው ።

አሁኑኑ ይደውሉልን
0911 45 67 94
0900 06 60 00


የኅዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዓመት ሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ ላይ የተጀመረውን የሦስትዮሽ ድርድር ማስቀጠል አስፈላጊነት ላይ ስምምነት ቢደረስም፤ ሱዳን የድርድር ሂደቱ ካልተቀየረ አልሳተፍም ማለቷ ተሰማ፡፡

የሶስቱ አገራት የውሃና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኅዳር 10 በበይነ መረብ ድርድር አድርገዋል፡፡የአፍሪካ ኅብረት አስፈፃሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ለመሪዎች ሊቀርብ የሚችል ውጤት ሊመዘገብ ይገባል ሲሉ አሳስበው ስብሰባውን ዘግተውታል፡፡
@bernosmedia24


የአሮጌው ብር ኖት የቅያሬ ጊዜ ታህሳስ 6 ቀን ይጠናቀቃል።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /10/2013 ዓ.ም

ከያዝነው ወር ህዳር 22 ጀምሮ ደግሞ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈጸም የማይቻል መሆኑን አስታውቋል።

ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም ይታወሳል።

በመሆኑም የአሮጌው የብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከዚህ ቀን በኋላ በባንኮች አሮጌ የብር ኖት እንደማይኖርም ገልጿል።

በዚሁ መሰረት የተፈቀደው የብር መቀየሪያ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 25 ቀናት ብቻ እንደቀሩት ይፋ አድርጓል።
@bernosmedia24


ሰበር ዜና

ህወሓት ባህርዳር ከተማ ላይ የሮኬት ጥቃት ፈፀመ።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /10/2013 ዓ.ም

ህገወጡ የትህነግ ቡድን ዛሬ ሌሊት 7፡40 አካባቢ ወደ ባህርዳር ከተማ የሮኬት ጥቃት ፈጽሟል።

በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩ ያጣራ ሲሆን እስካሁን ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌሉ የክልሉ መንግስት አሳውቋል።
@bernosmedia24


በጠገዴ ማክሰኞ ገብያ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር/10/2013 ዓ.ም

በክልል፣በዞንና በወረዳ ሀላፊዎች እንዲሁም በኮማንድ ፖስት አመራሮች አስተባባሪነት በርካታ ቁጥር ያለው የከተማው ነዋሪ በተገኘበት ውይይት ተካሂዷል። የአካባቢው ነዋሪዎች በውይይቱ እንደተናገሩት በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ሰብዓዊና ዴምክራሲያዊ መብታውን ተነጥቀው ፣በቋንቋቸው እንዳይናገሩ በባህላቸው እንዳይኖሩ ፣አንዳቸው ከአንዳቸው በጥርጣሬ እንዲተያዩ በማድረግ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ሲደረጉ እንደነበር፣በአካባቢው ተሰሚነት የነበራቸውና ስለ ማንነታቸው ያቀነቅኑ የነበሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሳደዱና ሲገደሉ አንደቆዩ ያስረዳሉ።

አስተያየት ሰጭዎቹ እንደሚሉት አሸባሪውን ቡድን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ያለው እንቅስቃሴ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረና አሁን ከትህነግ ጭቆና ቀንበር በመዉጣታቸዉ ደስታቸውን እጥፍ ድርብ እንደሆነ ገልፀዋል።

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ሙሉቀን ተገኘ በውይይቱ ማጠቃለያ እንደተናገሩት ወጣቶች አሁን ላይ የተገኘውን የነፃነት ድል ለማስቀጠል በመደረጀት አካባቢያቸውን በንቃት መጠበቅ እንዳለባቸው፣ማህበረሰቡ ተረጋግቶ የተለመደው ተግባሩን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከማከናወን ጎን ለጎን መረጃዎችንና ጥቆማዎችን ለሚመለከተው አካል ማድረስ እንዳለበት እንዲሁም ለአካባቢ ሰላምና ደህንነት ሲባል ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻልና ማንኛውም አካል ከምሽቱ 3:ዐዐ በሗላ መንቀሳቀስ የማይቻል መሆኑን አሳስበዋል።

ሀላፊው አክለውም እስካሁን ድረስ በምህረት ያልገቡ በወረዳው ሲያገለግሉ የነበሩ ፖሊሶች፣ልዩ ሀይሎች፣ አመራሮች፣ ፀረ ሽፍታዎችና ዞባዊ ሚሊሻዎች እስከ ህዳር 14 ድረስ ትጥቃቸውን አውርደው እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡና በራሳቸው ፈቃድ ካልገቡ ግን ህጋዊ እርምጃ የሚጀመር እንደሆነና ቀጣይ መንግስት እንደመንግስት ጠንካራ አቋም በመያዝ ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ለመስራት ጥረት የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል ሲል የጠገዴ ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።
@bernosmedia24




አሳዛኝ ዜና፤

የምዕራብ ጎጃም ዞን የፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ልዑል መኮንን በግዳጅ ላይ እያሉ በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /10/2013 ዓ.ም

በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ልዑል መኮንን የአማራ ክልል መንግስት በጠራው የአማራ ልዩ ሀይል:ሚሊሻና መከላከያ ነጻ ባወጣቸው አካባቢወች ህዝብን የማረጋጋትና አመራርን ማደራጀት ተልዕኮ (ዘመቻ ማይካድራ) የክልሉን መንግስት ጥሪ ተቀብለው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በታማኝነትና በቁርጠኝኘት እያገለገሉ ባሉበት ትላንትናው ዕለት ማለትም ህዳር 9/2013 ስራቸውን ሲሰሩ ውለው ሲመለሱ በወልቃይት ልዩ ስሙ አድርመጺ በሚባል አካባቢ የተሳፈሩበት መኪና ተገልብጦ ህይወታቸው አልፏል።

አቶ ልዑል መኮንን በሰራባቸው ቦታወች ሁሉ ታማኝ: ቅን ውጤታማና ጠንካራ አመራር በመስጠት ህዝብን ያገለገለ ወጣት መሪ ነበር።

በወንድማችን መሰዋት ጥልቅ ሀዘን ቢሰማንም ለህዝብና ለሀገር ደህንነት ሲባል የተከፈለ መስዋትነት በመሆኑ ለሌሎች የትግል ጓዶቹ ህዝብን ማገልገል እስከመስዋትነት መሆኑን አስተምሮን አልፏል ።

ለሀገርና ለህዝብ መስዋት መሆን ሞት ሳይሆን ክብር ነው!!
@bernosmedia24


በአዲስ አበባ ከተማ በቀጣዩ ቀናቶች በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል ኃይል ይቋረጣል!

አርብ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣
• በኦሎፒያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮሚያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ፣ በለቡ፣ በጆሞ 1 በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፣

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:30 ድረስ፣
• በደራርቱ ት/ቤት፣ በአየር ኃይል ካምፕ፣ በወርቁ ሰፈር፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤ/ክ፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤ/ክ እና አካባቢዎቻቸው፣

ዕሁድ ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣
• በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በጉርድ ሾላ፣ በአየር መንገድ ቤቶች እና አካባቢዎቻቸው፣

እንዲሁም ሰኞ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣
• በቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞርያ፣ በመቀጠያ፣ በታቦት ማደርያ እና አካባቢዎቻቸው፣

በተጨማሪም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ፣
• በደራርቱ ት/ቤት፣ በአየር ኃይል ካምፕ፣ በወርቁ ሰፈር፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ በካኦ ጄጄ፣ በጊዮን በረኪና፣ በዊንጌት ት/ቤት ጀርባ፣ በታይዋን ገበያ፣ በኮልፌ ቁሳቁስ፣ በገርጂ ኮንደሚኒየም፣ በኢፔሪያል ሆቴል፣ በገርጂ ጤና ጣቢያ፣ በዳችያ ቀለም፣ በገርጂ አንበሳ ጋራዥ፣ በጎሮ፣ በሰሚት ለስላሳ፣ በሰሚት ኪዳነምህረት ቤ/ክ፣ በፍርድ ቤት እና አካባቢዎቻቸው፣ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ክቡራን ደንበኞች ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲይያደርጉ ተብሏል፡፡

#ሼር_ይደረግ፣
@bernosmedia24


በደብረብርሃን ከተማ በ2012 በጀት ዓመት ብቻ በ504 ባለሀብቶች 31. 6 ቢሊዮን ብር ያህል ኢንቨስት ተደርጓል፡፡

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /10/2013 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ውስጥ በፈጣን የኢንዱስትሪ ግስጋሴ ላይ ከሚገኙ ከተሞች የደብረ ብርሃን ከተማ በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኝና በመካከለኛ ከተማ አስተዳደር ደረጃ ያለች ስትሆን፣ ከከልሉ ርዕሰ ከተማ ባሕር ዳር 695 ኪ/ሜ፤ ከፌደራሉ ከተማ አዲስ አበባ ደግሞ 130 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ ከባሕር ጠለል በላይ 2,700 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡

የከተማዋ ስፋት 18,000 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፣ በከተማው ፕላን የተካተተው ከማስፋፊያው ውጭ 5,711 ሄክታር ይሸፍናል፡፡ የቦታውም አቀማመጥ 86 በመቶ ሜዳማ፤10 በመቶ ዳገታማና 4 በመቶ ተራራማ የሆነና ከዚህም ውስጥ 95 በመቶ ለግንባታ ምቹ የሆነ ቦታ ነው፡፡

የከተማዋን አየር ንብረት ስንመለከትም በቀዝቃዘማ አየር ንብረት ብትታወቅም አሁን ላይ ቀዝቃዛነቱ እየቀነሰ የመጣ፤ በአማካይ 14.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሙቀትና 964 ሚሊ ሜትር አመታዊ የዝናብ መጠን ያለት ከተማ ነች፡፡

ከአስተዳደራዊ አደረጃጀት አንጻር ሲታይም ከተማዋ በ9 የከተማና በ5 የገጠር ቀበሌ አስተዳደርና በ19 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተዋቅራለች፡፡

የከተማው ህዝብ የተሰማራበት የሥራ መስክ በአብዛኛው በንግድና በግብርና ሲሆን ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢንዱስትሪዎች እየተመሙባት የምትገኝ ከተማ እንደሆነች መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስካጅ አቶ ኃይለማርያም ንጉስ ከተማዋ ለአዲስ አበባ ካላት ቅርበት፤ ምቹ አየር ንብረት፤ ሠላማዊና ሥራ ወዳድ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ በመሆኗ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ በኢንቨስተሮች ተፈላጊ ከተማ እንድትሆን አስችሏታል ያሉት ም/ ሥራ አስካጁ እስከ 2012 በጀት ዓመት መጨረሻ ብቻ በ504 ባለሀብቶች 31ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ያህል ኢንቨስት እንደተደረገ ተናግረዋል፡፡

ኢንቨስትመንቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሌሎች ባለሀብቶች ወደ ከተማ መስተዳድሩ በብዛት መምጣት እንዲችሉ መስተዳድሩ ከምንጊዜውም በላይ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በቅንነት በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ ኃ/ማርያም ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ኢንቨስትመንቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ለበርካታ ዓመታት ሲጓተት የነበረው የመሠረተ ልማት አገልግሎት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ አዳዲስ የምስረታ ሠፈሮችን ከነባሩ ሠፈር ጋር ለማገናኘት የመሠረተ ልማት አውታሮችን በዋናነት መንገድ ዝርጋታ፤ ውሃና መብራት መስመር አቅርቦት እየሠራ ይገኛል ብለዋል አቶ ኃለማርያም፡፡

መሠረተ ልማት ለአንድ ሀገር ህዝብ ዕድገት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንደ ደም ሥር የሚታይ ነው ያሉት አቶ ኃ/ማርያም በመሠረተ ልማት መጓተት ምክንያት ኢንቨስትመንቱ እንዳይስተጓጎል ከተማ አስተዳደሩ በራሱ በሚሰበስበው፤ በክልሉና በዓለም ባንክ በጀት በመጠቀም የመሠረተ ልማት አውታሮችን እየገነባ ይገኛል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ በደብረብርሃን ከተማና በዙሪያዋ እየተገነቡ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የከተማዋ ህብረተሰብ ታላቅ ተስፋን የሰነቀ በመሆኑ መስተዳድሩም አስፈላጊ የመሰረተ ልማቶችን ለማሟላት የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል እንላለን፡፡

መረጃውን ያደረሰን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ነው።
@bernosmedia24


የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ወርቅ የሰረቁ ተጠርጣሪዎች ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /10/2013 ዓ.ም

የግል ተበዳይ አቶ አቤል አሰፋ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ ፖሊሶች ነን ያሉ ግለሰቦች በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መጥተው በር እንዲከፍቱላቸው ሲጠይቋቸው ማንነታችሁን ሳላረጋግጥ እና ለቤተሰቦቼ ሳላሳውቅ አልከፍትም ማለታቸውንና ከዚያም ፖሊስ ነን ያሉት ግለሰቦች ተጨማሪ ሃይል ያስፈልገናል እያሉ እየተነጋገሩ ወደመጡበት እንደተመለሱ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ የግል ተበዳይ አቶ አቤል ቀን ወደ ስራ ከሄዱ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ ከቀኑ 9 ሰዓት ሲሆን የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው እና ሽጉጥ ታጥቀው ተመልሰው በመምጣት « አቶ አቤል ወንጀል ሰርተው ስለታሰሩ እኛ ቤታቸውን ልንበረብር ነው የመጣነው » ብለው ለጎረቤት ከተናገሩ በኋላ የተቆለፈውን በር ሰብረው በመግባት በካዝና ውስጥ ለንግድ አገልግሎት የተቀመጡ አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ብር ግምት ያላቸውን የወርቅ ጌጣጌጦች ሰርቀው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-20411 አ.አ በሆነ ፒካፕ ተሽከርካሪ ጭነው መውሰዳቸውን የግል ተበዳይ ገልፀዋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጃንሜዳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ለውጥአየሁ ከበደ እንዳስረዱት የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው ጣቢያው የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማቋቋም እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የክትትል ክፍል ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡

የፈፃሚዎቹን ማንነት ለማወቅ ቀን እና ለሊት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትል ካዝናውን ጭኖ የተሰወረውን ተሽከርካሪ፣በወንጀሉ ተሳትፈዋል የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎችን፣ ለወንጀል ተግባር ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የፖሊስ የደንብ አልባሳት፣ሽጉጥ፣ ካቴና እና ስለቶችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ፣ የፖሊስ የደንብ አልባሳቱንም ከየት አምጥተው እንደለበሱ የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተር ለውጥአየሁ ከበደ ተናግረዋል፡፡

የተሰረቁት ወርቆች በ600 ሺ ብር ለሌላ ግለሰብ ተሽጠው እንደነበር ያስታወሱት ምክትል ኢንስፔክተር ሄኖክ የተሸጡት ወርቆች መርካቶ አካባቢ እንደተገኙ እና ገዢውም በቁጥጥር ስር እንደዋለ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ፖሊስ ቀንና ለሊት ደክሞ በመስራትና ተጠርጣሪዎቹን አውቆ በመያዝ ያከናወነው ተግባር እንዳስደሰታቸው የግል ተበዳይ አቶ አቤል አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ምርመራውን ለማስፋት በተደራጀ መንገድ እየተሰራ ነው ያሉት ዋና ኢንስፔክተር ለውጥአየሁ ከበደ ፖሊስ ሳይሆኑ የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው ወንጀል የሚፈፅሙ እና የከተማችንን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሣቀሱ ግለሰቦች በመኖራቸው ህብረተሰቡ መታወቂያ በመጠየቅም ሆነ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ስልክ በመደወል ህጋዊነታቸውን ሊያረጋግጥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም ለሚመለከተው አካል ሊያሳውቅ ይገባል ብለዋል፡፡

የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ለስራ ጉዳይ በሚል ምክንያት ወደተለያዩ መኖሪያ ቤቶች እና ተቋማት የሚሄዱ ግለሰቦችን ማንነት መለየት እና ማረጋገጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማሳሰቡ ይታወሳል ብሏል ኮሚሽኑ።


የህወሃት ቡድን በአስቸኳይ እጅ በመስጠት ህዝብን ከእንግልት ራስንም ከአጉል ውርደት አድኖ በፍርድ አደባባይ እንዲዳኝ የብልጽግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር/10/2013 ዓ.ም

መጥፊያው እየቀረበ የመጣው የማፊያ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት እየደረሰበት ካለው ሽንፈት የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ የመዳከም እና የመፈረካከስ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ፓርቲው ገልጿል።

ይህ ቡድን የመጨረሻ አማራጮቹን ሁሉ ተጠቅሞ እየፈነቀለ ያለው ድንጋይ ሁሉ እንቅፋት እና መጥፊያው እየሆነ ከፍርድም እንደማያስመልጠው እየተረዳው መጥቷል ብሏል ፓርቲው።

ፓርቲው መቐለ የመሸገው ሽፍታ ቡድን እና ያሰማራው ሰራዊት በቀለበት ውስጥ እየተሽከረከረ መውጫው ጨንቆት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሽንፈትን እየተከናነበ መሆኑ ግልጽ ነው ብሏል፡፡

“በነፍስ ግቢ እና ውጪ ውስጥ ሆኖ ዝብርቅርቁ የወጣ መግለጫ መስጠት፣ ሲዘርፍ የኖረውን ጥሪት ሁሉ ለጦር ሜዳ መገበር፣ መከላከያ ሰራዊታችን ላይ የጫረውን እና የፈፀመውን ግፍ ክዶ ቀኑን ሙሉ ተወረርኩ ብሎ ማላዘን መገለጫው ሆኗል” ብሏል ፓርቲው።

ታሪክ የሚያበላሽ ጦርነት ውስጥ አልሳተፍም ብሎ ለጦርነቱ ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው የትግራይ ህዝብ ምላሽ መጨረሻውን እያፈጠነው እና ህዝቡ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እየተሰለፈ መሆኑ ቡድኑን ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንደከተተው ፓርቲው ገልጿል።

የትግራይ ህዝብም ባለውለታው ከሆነው የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት ጎን በመሰለፍ የጁንታው ቡድን ግብአተ መሬት እንዲፈፀም የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል፡፡
@bernosmedia24


ቀና ትብብር #ለበርኖስ_ቤተሰቦች!

ውድ የበርኖስ ሚዲያ ቤተሰቦቻችን የእናንተን ክብር በሚመጥን መልኩ ፈጣን እና እውነተኛ መረጃዎችን #በዮቲዮብ ቻናላችን ወደ እናንተ እያደረስን እንገኛለን።

ከዚህ በበለጠ የተለያዮ መረጃዎችን ወደ እርሶ እንድናደርስ #የዮቲዮብ ቻናላችንን #ሰብስክራይብ በማድረግ ወዳጅ እንድትሆኑን እንጠይቃለን!

እርሶዎ ካሎት ጥቂት ደቂቃ ብቻ በመቀነስ ከታች ያለውን ሊንክ በቀላሉ በመጫን #ሰብስክራይብ እንድታደርጉን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ስለ መልካም ወዳጅነትዎ እናመሰግናለን!

https://youtu.be/LB8P0Uw9vQo


በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በሁለት አጎራባች ወረዳዎች ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቅሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ ።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /9/2013 ዓ.ም

የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ጥቃቱ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት የተፈጸመው በኮንሶ ዞን ፣ በአማሮ አና በቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው።

በአካባቢዎቹ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ያረጋገጡት የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እየተለየ ይገኛል ብለዋል።

በአሁኑወቅት መንግስት ጥቃቱ ወደ ተፈጸመባቸው ቀበሌዎች የፀጥታ አባላትን ያሰማራ ሲሆን የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ ለመያዝም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ሃላፊው ተናግረዋል።

ዘገባው የዶቼቬሌ ነው።
@bernosmedia24


በምዕራብ ወለጋ በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር 9/2013 ዓ.ም

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በኦነግ ሸኔ ቡድን የፈጸመውን ጥፋት ተከትሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው፣48 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉና፣ 64 ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ ከተበታተኑ በኋላ መለቀማቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

አክለውም ለኦነግ ሸኔ አባላት የሎጂስቲክስና ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 1341 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ከእነዚህ ውስጥም 104ቱ የህወሃት ቡድን አባላት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተወሠደዉ እርምጃም 57 የእጅ ቦንቦችና ክላሾች፣ 681 ጥይቶች፣ 600ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብና የተለያዩ የጦር ሜዳ ሬድዮዎችና የጦር መነጽሮች በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልጸዋል።

በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እንደሰፈነም ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በመግለጫው ወቅት ጠቅሰዋል፡፡
@bernosmedia24


"የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ መስዋዕትነት ከፍሎ ነጻ ያወጣቸውን ህዝቦቹንና ግዛቶቹን መልሶ ለትግራይ ክለል አስተዳደር የሚሰጥበት ምክንያት የለም።"

ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /9/2013 ዓ.ም

የወልቃይት ጠገዴና የራያ ጉዳይ አሁንም አነጋጋሪ ሆኖ መቀጠሉን የሚያመላክቱ ሀሳቦች እየተራመዱ ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታ በወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች መካከል የተከሰተ የተለየ ነገር ባይኖርም የራያ ህዝብ አሁንም በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር እንዲቆይ የሚፈልጉ ጉዶች/ከሀዲዎች መኖራቸው ግልጽ እየሆነ መጥቷል።

አሳዛኙ ነገር የራያም ሆነ የወልቃይት ጠገዴ አካባቢና ህዝብ በትህነግ ተገዶ ወደ ትግራይ በመሄዱ ምክንያት እንደቅደም ተከተሉ ላለፉት 35 እና 28 አመታት ሲሰቃይ መቆየቱ እየታወቀና የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ክቡር መስዋዕትነት ከፍሎ በጀግንነት ነጻ እንዳወጣቸው ግልጽ ሆኖ እያለ እነዚህ አካባቢዎች በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር እንዲቆዩ የሚል አቋም መያዝ ፍጹም ሀላፊነት የጎደለውና የአማራን መስዋዕትነት መናቅ የመሆኑ ጉዳይ ነው።

በቅርቡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስሩ የተሾሙት ዶ/ር ሙሉ ነጋ ስለወልቃይትና ራያ ሁኔታ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ አካባቢዎቹ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር ቆይተው ጥያቄያቸው በከስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሊታይ እንደሚችል ገልጸዋል። ይህም ከእሳቸው የሚጠበቅ ስለሆነ ከዚህ በላይ ከዶ/ር ሙሉ ነጋ መጠበቅ የዋህነት ነው።

ይኸ በዚህ እንዳለ የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ጉዳይ መታየት ያለበት በሀይል ተወስደው ስለነበር በሀይል እንዲመለሱ ተደርገዋል። እናም የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ መስዋዕትነት ከፍሎ ነጻ ያወጣቸውን ህዝቦቹንና ግዛቶቹን መልሶ ለትግራይ ክለል አስተዳደር የሚሰጥበት ምክንያት የለም።

ከሁሉም በላይ ግን ይኸ ህዝብ ማንም እየመጣ ፍላጎቱን የሚጭነበት ሁኔታ ስለማይኖር በአማራ ክልል ውስጥ ሆኖ ሀሳቡን በነጻ የሚገልጽበት አሰራር ነው መመቻቸት ያለበት። በዚህ ረገድ የአማራ ክልል መንግስና ገዥው ፓርቲ የአማራ ብልግና ግልጽ አቋም በመያዝ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይኖርበታል። በፍጹም ያ ታሪካዊ ስህተት መደገም አይኖርበትም።
@bernosmedia24


"የአማራ ህዝብ ለድል የተፈጠረ ነው፣ ከድል ማግስት የሚያደራጀው ልሂቃን ነው ያጣው።"

ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /9/2013 ዓ.ም

የአማራ ፖለቲከኞች በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ራያ ግዛቶች ዙሪያ ከወዲሁ የመፍትሔ ሀሳብ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ከጦርነቱ ድል ማግስት ችግር ይፈጠራል።

ሁላችንም የአማራ ልሂቃን ከወዲሁ ጠንካራ አቋም መያዝ ይኖርብናል። ፌደራል መንግስቱ ጊዜ ስጡኝ፣ ነፃ የወጡት ግዛቶች አሁንም በትግራይ ክልል በሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ስር ይተዳደሩ የሚል ከሆነ የሗላ ሗላ ችግር መፈጠሩ አይቀርም።

የአማራ ህዝብ ለድል የተፈጠረ ነው፣ ከድል ማግስት የሚያደራጀው ልሂቃን ነው ያጣው። ሁሉም የአማራ ምሁራን የጦርነት ዘጋቢ መሆን የለበትም። ግፋ በለው የሚል ብዙ ሃይል ስላለ። አማራ የሚያስፈልገው በጉልበት የተወሰዱበት ግዛቶቹን በልጆቹ ደም ካስመለሰ በሗላ፣ በምን መንገድ ይተዳደሩ በሚለው ዙሪያ ጠንካራ ሀሳብ የሚያቀርብ ነው።
@bernosmedia24


"ክብር የምሰጠው ትናንት የኦነግን፣ ዛሬ የህውሃትን ወራሪ ድባቅ ለመታው ለአማራ ልዩ ሃይል ነው!"

የፓለቲካ ተንታኝ ሀብታሙ አያሌው

በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /9/2013 ዓ.ም

የአማራ ልዩ ሃይል ትናንት ከሚሴ ላይ ኦነግን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ መልሶታል፣ የኦሮሙማን ኘሮጀክትንም ለጊዜው አሳፍሮ መልኮታል። ዛሬም መከላከያን ከትግራይ ልዩ ሃይል ከበባ አውጥቶ ከመብረቃዊ ጥቃት ታድጎታል። በእሳት ውስጥ እየተራመደም ድል እየተጎናፀፈ ይገኛል። ለዚህም የላቀ ክብር አለኝ።

ህውሃት ለምን በሽብር አልተፈረጀም ይላሉ የዋሆች። እንኳን በሽብር ሊፈረጅ፣ ከምርጫ ቦርድ የሰጡትን ህጋዊ ሰርትፊኬትም አልሰረዙትም። ምክንያቱም የአማራ ጠላቶች ጨርሰው እንዲጠፉ አይፈለግም።

እነ ወልቃይት እና ራያ የአማራ የደም እና የግፍ መሬቶች ናቸው። ነፃ ከወጡ በሗላም የአማራ ሚሊሻ እና ልዩ ሃይል አካባቢውን ለቅቀው መውጣት የለባቸውም። ሪፈረንደም፣ የወሰንና ማንነት ኮሚሽን የሚባል ነገር የለም።

አማራ ርስቱን ለማስመለስ ተጋድሎ ያደረገው ሰሞኑን ብቻ የሚመስለው ሰው ካለ ስህተት ነው። የአማራ ህዝብ ለአፅመ ርስቶቹ ሲዋደቅ የነበረው ከ30 አመት በፊት ነው።
@bernosmedia24


በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ጥቆማና መረጃ ለመስጠት የሚያስችሉ አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 93 መሰረት ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ሲባል በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ የሚታወስ ነው።

በዚህ መሰረት ነው ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ጥቆማና መረጃ ለመስጠት አድራሻዎች ይፋ የሆኑት።

በመሆኑም÷

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ

የኢሜል አድራሻ:-Stateofemergency2013@gmail.com

የፌስቡክ አድራሻ:- የአስቸኳይ ጊዜ መርማሪ ቦርድ

የስልክ ቁጥር Tel.:- 0111544181 / 0111239980

ፖ.ሳ.ቁ :- 80001

ፋክስ ፡- 0111544641

የነጻ ስልክ:- 8557

የቴሌግራም አድራሻ:- State of emergency enquiry board FDRE እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ መርማሪ ቦርድ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ የቢሮ አድራሻ አራት ኪሎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት መረጃ እና ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@bernosmedia24

Показано 20 последних публикаций.

3 050

подписчиков
Статистика канала