▪️ቢድዓ ለሁለት ይከፈላል የሚሉ ሰዎች ሚያመጧቸው ማምታቻዎች እና ምላሹ ክፍል 3.
🔻#ሶስተኛው_ማምታቻ ፡ كل بدعة ضلالة" የሚለው ሐዲስ ላይ "كل" የምትለዋ ቃል ሁሉም ማለትን አትጠቅምም ፤ ለዚህም ቁርአን ውስጥለምሳሌ አላህ የሑድ ህዝቦችን ለማጥፋት የተላከችውን ንፋስ
በጌታዋ ትዕዛዝ አንዳቹን ሁሉ ] { تُدَمِّرُكُلَّ شَيْءٍبِأَمْرِرَبِّهَا } አስመልክቶታጠፋለች ] (አሕቃፍ ፥ 25) ብሏል ፤ ነገር ግን ሁሉም ነገሮች አልጠፉም ፤ እናም "كل" የሚለው ቃል ሁሉንም የሚለውን ስለማያመላክት ሐዲሱ ላይ ሁሉም ቢድዓ ጥሜት ነው ተብሎ አይተረጎምም ፤ ስለዚህ መልካም እና መጥፎ ቢድዓ አለ በማለት መከራከሪያ ያቀርባሉ።
°
🔻ለዚህ ማምታቻ በአራት መልኩ መልስ መስጠት ይቻላል ፦
1⃣ኛ."كل" የሚለው ቃል ሁሉን አካታች መሆኑን ያስጠቅማል። ይህንንም ከተናገሩ ዑለማዎች ውስጥ እንደምሳሌ አስነዊ (አት-ተምሂድ ሊልአስነዊ ፥ 302) ላይ የጠቀሱትን ንግግር መመላከት ይቻላል። ፤ ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉን ነገር ለማለት እንዳያመላክት የሚገድበው ነገር ከተገኘ በዛ ነገር ይገደባል። በቁርአን ውስጥም ሆነ በሐዲስ ላይ "كل" የሚለውን ቃል ሌላ ነገር የሚገድበው መልእክት እስካልመጣ ድረስ በዛው ሁሉን ነገር ለማለት ነው የሚጠቁመው።
°
2⃣ኛ.ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - በሐዲሳቸው ላይ "كل بدعة ضلالة " [ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው ] በማለት የተናገሩትን ጠቅላይ የሆነን ንግግር ጠቅላይነቱን የሚገድበው ሌላ ንግግር ስላልመጣ በዛው በጠቅላይነቱ ነው የሚተረጎመው። ይህን አስመልክቶ (አሪ-ረሳለቱ - ሻፍዒያ ፥ 295) ላይ የኢማሙ ሻፊዒይን ንግግር ይመልከቱ።
°
3⃣ኛ. ይህ ሐዲስ ሁሉንም ቢድዓ ለማለት እንደተፈለገበት ደግሞ የሚያመላክቱ ነጥቦች አሉ ፦ ከነዚህም ውስጥ ፡ 1.ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - በተደጋጋሚ በየጁሙዓ ኹጥባቸው ላይ ሳይገድቡ መናገራቸው ፤ 2. ከሱ ቀጥለው [ ሁሉም ጥሜት እሳት ውስጥ ነው ] በማለትማጠናከራቸው ፤ 3.በተጨማሪም "كل" የምትለዋ ቃል በ"ነኪራ" ወይም ያልታወቀ ስም ላይ ስትገባ ጠቅላይነትን እንደምታመላክትሁሉም የኡሱሉል-ፊቅህ ሊቃውንት መስማመታቸው ነው(ሸርሕ ከዋኪቡል ሙኒር ፥ 3/123-125 * በሕሩል ሙሒጥ ፥ 4/84). ላይ ይመልከቱ። ስለዚህ ሐዲሱ ላይ ቢድዓ ሁሉም ጥሜት እንደሆነ
ይጠቁመናል።
°
⃣4ኛ.ቁርአኑ ላይ ሁሉንም ታጠፋለች የተባለችው ንፋስ ሁሉንም አላጠፋችም ለሚለው ሐሳብ የሚሰጠው መልስ ሁለት አይነት ነው ፡
1.ንፋሷ ሁሉንም ነገር አጥፍታለች ፤ ነገር ግን ያጠፋችው እንድታጠፋ የታዘዘችበትን ሁሉንም ነገር ነው። የቁርአኑ ትርጉም ለማጥፋት በታዘዝችበት ሁሉንም ነገር ታጠፋለች ለማለት እንደሆነ የተፍሲሮችኢማም የሆኑት አብኑ ጀሪር አጥ-ጦበሪ ተፍሲራቸው (26/27) ላይ ተናግረዋል።
°
🔻የታዘዘችበትን ነገር በሙሉ አጥፍታለች ተብሎ እንዲተረጎም ያደረገው ደግሞ አመላካች ነገር ስላለ ነው። አመላካች ነገሩንም አሏሁ - ተዓላ - በሌላም አንቀጽ ላይ እንዲህ ሲል ይገልፃል ፦
{َِمَا تَذَرُمِن شَيْءٍأَتَتْ عَلَيْهِ إِلاَّجَعَلَتْهُ كَالرَّمِيم }
°
[| በላዩ ላይ #የመጣችበትን_ማንኛውንም_ነገር እንደ በሰበሰ አጥንትያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወውም፡፡ |] (አዝ-ዛሪያት ፥ 42). ስለዚህ "كل" የሚለው ቃል ጠቅላይነቱን ይዞ ይተረጎማል ማለት ነው። 2.ወይም ደግሞ "كل" የሚለው ቃል የሚገድበው ነገር ከመጣ ተገድቦይተረጎማል ባልነው መሰረት ከሆነ እዚህም አንቀጽ ላይ ተገድቦሊተረጎም ይችላል። ምክንያቱም እዛው አንቀጽ ላይ መገደቡን የሚያመላክት ቃል ስላለ ማለት ነው ፡ እሱም
{ .. ْۚفَأَصْبَحُوا لاَيُرَى إِلاَّمَسَاكِنُهُم ..}
[| .. #ከመኖሪያዎቻቸውም_በስተቀር ምንም የማይታዩ ሆኑ፡፡ .. |] (አሕቃፍ ፥ 25).
°
🔻አሏሁ - ተዓላ - ሁሉንም ነገር ታጠፋለች ብሎ እዛው ቀጥሎ ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር በማለት መኖሪያዎቻቸው እንዳልጠፉ ተናግሯል። ስለዚህ "كل" የሚለው ቃል የሚገድበው ነገር ስለመጣ ተገድቦ ይተረጎማል ማለት ነው።
°
🔻ሌሎች የቁርአን አንቀጾች እና ሒዲሶች ላይም እንደዚሁ "كل" የሚለው ቃል ከጠቅላይነቱ እንዲገደብ የሚያደርገው "ቀራኢን" ወይም አመላካች ነገር ከመጣ በዛ ምክንያት ተገድቦ ይተረጎማል ፤ ካልሆነ ግን ጠቅላይነቱን ይዞ ይተረጎማል። ሐዲሱ ላይ ግን ከላይ እንዳየነው "كل" የሚለው ቃል የሚገድበው ነገር ምንም ስለሌለ ሁሉም ቢድዓ ተብሎ ነው የሚተረጎመው ማለት ነው። በመሆኑም ይህን እና መሰል ማስረጃዋች ላይ ተመርኩዘው የሚያመጧቸው ማምታቻዎች ላይመልስ መስጠት ይቻላል። ነገር ግን ፅሑፉ እንዳይረዝም ሲባል በዚሁእንብቃቃለን።
____
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
ሰኞ ሶፈር 27/1440ሂ. # ጥቅምት 26/2011.ላይ የተፃፈ.
https://telegram.me/ibnyahya777