Ibn Yahya Ahmed


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎችን ብቻ የማስተላልፍበት ቻናሌ ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


▪️የሚያጠራጥርህን ተው

🔻ከሐሰን ቢል ዐሊይ - ረዲየሏሁዐንሁማ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ ከአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - ይህን ሐፍዤያለው ፦ " የሚያጠራጥርህን ነገር ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ነገር ሂድ። ". (ቲርሚዚይ ፥ 2518 ላይ ዘግበውታል.) ትርጉሙም ፡ የምትጠራጠርበትን ነገር ተውና የማትጠራጠርበትን ነገር ያዝ ማለት ነው በማለት ኢማም አንነዊ አብራርተዋል።

@ibnyahya777


▪️ኑዛዜ

🔻ለወራሽ ኑዛዜ ማድረግ አይቻልም። እዳ ካለበት ደግሞ እዳ አለብኝ ብሎ ኑዛዜ ማድረጉ ግዴታ ነው። ከወራሾቹ ውጭ ለሌላ አካል የንበረቱን ሲሶ(1/3ተኛ) ኑዛዜ ማድረግ ይፈቅድለታል። ለምሳሌ መስጂድ ለማሰርያ እና መሰል መልካም ነገራቶች ማለት ነው። ነገር ግን ወራሾቹ በጣም ብር ሚያስፈልጋቸው ከሆነ ይህንን ኑዛዜ ባያደርግ መልካም ነው። ምክንያቱም ነብዩ - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - ይህን ብለዋልና ፡ " ወራሾችህን ደሀ ሆነው ሰዎችን የሚለምኑ አድርገህ ከምትተዋቸው ይልቅ ሀብታም አድርገህ ብትሞት የተሻለ ነው። ". (ቡኻሪ ፥ 4409 / ሙስሊም ፥ 1627)
~~
ኢብኑዑሰይሚን * ሸርሕ ሪያዱሷሊሒን ፥ 2/352-3
@ibnyahya777


▪️ችግር ቢደርስባችሁም ሞትን አትመኙ

🔻ከአነስ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ አንድኛችሁ ለደረሰበት ችግር ብሎ ሞትን አይመኝ ፤ መስራቱ የማይቀር ከሆነ እንዲህ ይበል ፡ አሏህ ሆይ! ህይወት መኖሬ ለኔ መልካም ከሆነ አኑረኝ ፤ መሞቴ ለኔ መልካም ከሆነ ውሰደኝ(አሙተኝ)። " (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777


▪️ሞትን አትመኙ

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ አንድኛችሁ ሞትን አይመኝ ፤ መልካም ሰሪ ከሆነ ምናልባት ሊጨምር ይችላል ወይም ደግሞ መጥፎ ሰሪ ከሆነ ተውበት ሊያደርግ ይችላልና። " (ሙተፈቁን ዐለይህ * ቃልበቃል ንባቡ የቡኻሪ ነው)

@ibnyahya777


▪️ቀብርን መዘየር

🔻ከቡረይደህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ቀብርን ከመዘየር ከልክያችሁ ነበር ፤ ዘይሯት " (ሙስሊም ዘግቦታል). በሌላ ዘገባ ላይ አኺራን ታስውሳችኋለች የሚልም አለ።

@ibnyahya777


▪️ጥፍጥና ቆራጭ

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ጥፍጥና ቆራጭ የሆነውን (ሞት) ማስታወስን አብዙ። ". (ቲርሚዚይ ፥ 2307)

@ibnyahya777


▪️ልክ እንደመንገደኛ

🔻ከኢብኑዑመር - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - በትከሻዬ ያዙኝ እና እንዲህ አሉኝ ፦ " ዱንያ ላይ ልክ እንደእንግዳ ሁን ፤ ወይም ልክ እንደ መንገድ የሚያልፍ ሰው ሁን። " ኢብኑዑመር - ረዲየሏሁዐንሁ - ደግሞ ይህን ይሉ ነበር ባመሸህ ጊዜ ንጋትን አትጠባበቅ ፤ ባነጋህ ጊዜ ደግሞ ምሽትን አትጠባበቅ ፤ ከጤንነትህ ለበሽታህ ያዝ ፤ ከህይወትህ ደግሞ ለሞትህ ያዝ። (ቡኻሪ ዘግቦታል።)

@ibnyahya777


▪️ምቀኝነት በ2ነገር

🔻ከዐብዲሏህ ቢን መስዑድ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " እንደሱ በሆንኩ ብሎ መመኘት በሁለት ነገሮች እንጂ የለም ፤ (1ኛው) አሏህ ገንዘብ የሰጠው ሆኖ በሐቅ ላይ ገንዘቡን በማጥፋት ላይ ያመቻቸው የሆነ ሰው እና ሌላኛው ደግሞ አሏህ እውቀት የሰጠው ሰው ሆኖ በእውቀቱ ፍርድ ይፈርድበታል እውቀቱንም ያስተምርበታል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777


▪️የ2ለ3 ፣ የ3ለ4

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " የሁለት ሰው ምግብ ለሶስት ሰው ይበቃል ፤ የሶስት ሰው ምግብ ለአራት ሰው ይበቃል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ).

@ibnyahya777


▪️በደል እና ስስትን ተጠንቀቁ!

🔻ከጃቢር - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " በደልን ተጠንቀቁ ምክንያቱም በደል የቂያማ ቀን ብዙ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ ምክንያቱም #ስስት ከእናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦችን ያጠፋው እሱ ነው ፤ ደሞቻቸውን እንዲያፈሱ እና ክልክል የሆኑ ነገሮችን የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳሳቸው። ". (ሙስሊም ፥ 2578 ላይ ዘግቦታል).

@ibnyahya777


▪️ትከሻዋ ሲቀር

🔻ከዓኢሻህ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - ተይዞ እንደተወራው እነሱ ፍየል አረዱና (ሰደቃ አደረጉ) እና ነብዩ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - " ከሷ ምኗ ቀረ?" አሉ ፤ (ዓኢሻም) "ትከሻዋ እንጂ ሌላ የቀረ ነገር የለም" አለች ፤ እሳቸውም " ከትከሻዋ ውጭ ሁሉም ቀርቷል " አሏት. (ቲርሚዚይ ፥ 2470 ላይ ዘግበውታል). ቲርሚዚይ ሐዲሱን ሲያብራሩ ነብያችን ከፍየሏ ትከሻዋ ሲቀር ሁሉንም ሰደቃ አወጡ እና ትከሻዋ ሲቀር ሌላው ሰደቃ የወጣው የፍየሏ ክፍል አኺራችን ላይ ቀርቶልናል አሉ።

@ibnyahya777


▪️ገንዘብን አይቀንስም

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ሰደቃ ከገንዘብ ምንም አትቀንስም ፤ አሏህ አንድን ባርያ ይቅርታ በማድረጉ ልቅናን እንጂ አይጨምርለትም ፤ አንድ ሰው ለአሏህ ብሎ አይተናነንስም ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ። ". (ሙስሊም ፥ 2588).

@ibnyahya777


▪️ስጥ

🔻ከአቢሁራይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " አሏሁ - ተዓላ - ይህን አለ ፥ የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ይሰጥሃል። "|| (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777


▪️ሁለት መላኢካዎች

🔻ከአቢሁራይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ባርያዎች በውስጡ የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መላኢካዎች የሚወርዱ ቢሆኑ እንጅ ፤ አንድኛው እንዲህ ይላል ፡ አሏህ ሆይ! የሚሰጥን ሰው ምትክን ስጠው ፤ ሌላኛው ደግሞ እንዲህ ይላል ፡ ለሚይዝ ሰው ጥፋትን ስጠው። " (ሙተፈቁን ዐለይህ).

@ibnyahya777


▪️የቴምር ቁራጭ

🔻ከዐዲይ ቢን ሓቲም - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " እሳትን በቴምር ግማሽ ቢሆን እንኳ ተጠንቀቁ! ". (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777


▪️ያንተ ገንዘብ

🔻ከዐብደሏህ ቢን መስዑድ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ ውስጥ የወራሾቹ ገንዘብ ከራሱ ገንዘብ ይልቅ ተወዳጅ የሆነ ማነው? ". የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ገንዘቡ ተወዳጅ የሆነ እንጂ ከኛ ውስጥ ማንም የለም አልናቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦ " የሱ ገንዘብ ማለት (ሰደቃ ሰጥቶ) ያስቀደመው ነው ፤ የወራሾቹ ገንዘብ ደግሞ ያቆየው(የተውከው) ነው። ". (ቡኻሪ ፥ 6442 ላይ ዘግቦታል)

@ibnyahya777


▪ትክክለኛ ሚስኪን ማለት

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ |" በሰዎች ዘንድ እየዞረ አንድ ወይም ሁለት ጉርሻ የሚመልሰው ሰው እንዲሁም አንድ ወይም ሁለት ቴምር የሚመልሰው ሰው ሚስኪን አይደለም ፤ ሚስኪን ማለት ፍላጎቱን የሚዘጋለት የሚያብቃቃውን ነገር የማያገኝ ነው ፤ ሰዎች ለሱ ሰደቃ እንዳያደርጉለት ደግሞ ስለሁኔታው አያውቁም ፤ ሰዎችን ለመለመንም አይቆምም። "| (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777


▪️እሳትን ነው ሚጠይቀው

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ |" ገንዘብን ለማብዛት ብሎ ሰዎችን የለመነ ሰው የሚጠይቀው የእሳት ፍም ነው ፤ ያሳንስ ወይም ያብዛ። "| (ሙስሊም ዘግቦታል).

@ibnyahya777


▪️የተብቃቃ ያብቃቃዋል

🔻ከሐኪም ቢን ሒዛም - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ነብዩ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " የላይኛው(ሰደቃ ሰጪ) እጅ ከታችኛው(ከሰደቃ ተቀባይ) እጅ በላጭ ነው ፤ ሰደቃን ከቅርብ ቤተሰብ ጀምር ፤ ከሰደቃ በላጩ ለራስህና ለቤተሰብህ ከተረፈ ከተብቃቃህ በኋላ የምትሰጠው ነው ፤ የተቆጠበ አሏህ ይቆጥበዋል ፤ የተብቃቃ አሏህ ያብቃቃዋል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777


▪️ዱንያ እንደተሰበሰበችለት

🔻ከዑበይዲሏህ ቢን ሚሕሰን አልአንሷሪይ አልኸጥሚይ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ ውስጥ በነፍሱ/በቤተሰቡ ሰላም ሆኖ ያነጋ ፣ በሰውነቱ ጤናማ ከሆነ ፣ እሱ ዘንድ የቀኑ ምግብ ካለው ዱንያ በአጠቃላይ እንደተሰበሰበችለት ይቆጠራል። " (ቲርሚዚይ ፥ 2346 ላይ ዘግበውታል ፤ አልባኒይ ሶሒሑልጃሚዕ ፥ 6042 ላይ ሐሰን ብለውታል)

@ibnyahya777

Показано 20 последних публикаций.