እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
-----
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አየሁ ጓጉሳ ወረዳ ለሚገኘው ለፕ/ር ጌትነት ታደለ ትምህርት ቤት ከ500ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የቤ ሙከራ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው ተልዕኮ አንዱ በሆነው ማህበረሰብ አገልግሎት አማካኝነት በአካባቢው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ መምህራን የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ከመስጠት ባሻገር ተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማሟላት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ተመራማሪ እና በጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ በሚታወቁት በፕ/ር ጌትነት ታደለ አማካኝነት አዊ ብሄ/አስተዳደር አየሁ ጓጉሳ ወረዳ ለተሰራው ለአዘና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚሆን የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ ትምህርቶች የተግባር ትምህርት ለመስጠት የሚያገለግሉ ከ500 ሺብር በላይ የሚገመቱ የኬሚካል እና የቤተ ሙከራ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ዶ/ር ክንዴ አስረድተዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የአዘና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት መ/ር አምሳሉ አስራ እና የትምህርት አጋርነት በኢትዮጵያ የትምህርት ቤቱ አስተባባሪ መ/ር መዓዛው ደሳለኝ ናቸው፡፡
ጥር 30/2017 ዓ.ም፤ እንጀባራ ዩኒቨርሲቲ