"ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል ” በሚል መሪ ቃል የዓድዋ ድል በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡
----
የካቲት 21/2017ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በበዓሉ የዓድዋ ድል ተግዳሮቶች ፣ትሩፋቶች እና አስተምሮቶች፣The Dramatic Irony Of Ethiopia’s victory at Adwa እና የዓድዋ ድል እሳቤ እና ትውልድ፣በክብርት ዶ/ር እጅጋሁ ሽባባው ሙዚቃ የሚሉ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በበዓሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል ስናከበር የዓድዋ ድል የነጭን የተሳሳተ የዘረኝነት እና የበላይነት አስተሳሰብ በመሰረታዊነት የቀየረ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የድል በዓል በመሆኑ ብለዋል፡፡ ዶ/ር ክንዴ አያይዘውም እኛ ኢትጵያዊያን የዓድዋ ድልን በየዓመቱ ከመዘከር ባሻገር አንድነታችንን እንደ ትናንት የአድዋ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ማጠናከር እና የዓድዋ ድልን የይቻላል መንፈስን በመላበስ ተከባበብረንና እጅ ለእጅ ተያይዘን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02xPH9Wj2AZHABEh543oHArX89jNxnhSMToNwsSmsHb7NCJAoKPWj21V8eki2dCacal/?app=fbl