TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
Russian
Язык сайта
Russian
English
Uzbek
Вход на сайт
Каталог
Каталог каналов и чатов
Поиск каналов
Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов
Рейтинг чатов
Рейтинг публикаций
Рейтинги брендов и персон
Аналитика
Поиск по публикациям
Мониторинг Telegram
©Legal details center© :የህግ ማብራሪያ ማዕከል©
9 Jan, 10:19
Открыть в Telegram
Поделиться
Пожаловаться
ለዛና ቁም ነገር
😀 🤔
የተዛወረውን ወደ ቦታው ...
═══ 😁 ═══
አንድ ተማሪ መምህሩን ተከትሎ ወደ ተዝካር ይሄዳል። እንደደረሰ ተሜ ከመጠን በላይ መጠጥ ጠጣና ከጓደኞቹ ጋር ጠብ ፈጠረ። ሁኔታውን ያዩ መምህር ተማሪያቸውን «ተው አንተ!» ብለው ቢቆጡት ተማሪው ሰክሮ ስለነበር «ምን አገባህ አንተ ደደብ ደንቆሮ!» በማለት በሰው ፊት ሰደባቸው።
በማግስቱ ተማሪው ስካሩ ሲያልፍለት በጣም ቆጨው። በመሆኑም መምህራን ሽማግሌዎች መርጦ ከመምህሩ እንዲያስታርቁት ለምኖ ላካቸው። ሽማግሌዎችም ሄደው ነገሩን በሰላም ጨርሰው በመመለስ ላይ እያሉ መንገድ ላይ አንድ የሚያውቃቸው ሰው ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ «ወዴት ሄዳችሁ ኖሯል?» በማለት ጠየቃቸው።
በዚህን ጊዜ ከሽማግሌዎች አንዱ የነበሩት አለቃ ለማ «ትናንት ተማሪ አስተማሪውን ሰድቦ አስታርቁን ብሎ ስለላከን ወደዛ ሄደን የተዛወረውን ስድብ ወደቦታው መልሰን መምጣታችን ነው።» አሉ ይባላል።
😂🤔😂🤔
መነኲሴና ሽፍታ
═══😁═══
ወሎ ውስጥ መነኲሴ እና ሽፍታ የሚባሉ አካባቢዎች አሉ። አንዱ ታዲያ መነኲሴ ከሚባል ስፍራ ለቆ ሽፍታ ከሚባል አገር መኖር ጀመረ።
ይህ ሰው ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምስክርነት ተጠርቶ ፍርድ ቤት ይሄዳል። ችሎት ተሰይሞ ተራው እንደደረሰ ዳኛው ስሙን ከመዘገቡ በኋላ አድራሻውን ጠየቁት። በዚህን ጊዜ ሰውየው
«በመጀመሪያ መነኲሴ ነበርኩ፤አሁን ግን ሽፍታ ነኝ።» ሲላቸው ዳኛው በመልሱ ተገርመው
«ምነው የፊቱን ኋላ ማድረግህ?» አሉት ይባላል።
😁 😁 😁 😁
📓 ኅብረ-ብዕር - ሦስተኛ መጽሐፍ
✍ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር
📖 📖 📖 📖 📖
671
0
2
1
×