TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
Russian
Язык сайта
Russian
English
Uzbek
Вход на сайт
Каталог
Каталог каналов и чатов
Поиск каналов
Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов
Рейтинг чатов
Рейтинг публикаций
Рейтинги брендов и персон
Аналитика
Поиск по публикациям
Мониторинг Telegram
©Legal details center© :የህግ ማብራሪያ ማዕከል©
10 Jan, 06:34
Открыть в Telegram
Поделиться
Пожаловаться
ይግባኝ ምክረ ሕግ:
#ምስክሮች_በፍርድ_ቤት_ሊጠየቋች_የሚችሉ_አራቱ_ጥያቄዎች
📌በፍርድ ቤት ክርክር ላይ አንድን ጉዳይ ለማስረዳት ከሚቀርቡ የማስረጃ ዓይነቶች ውስጥ ዋነኛው የምስክርነት ቃል ነው። የምስክርነት ቃል በዋነኝነት ከሳሽና ተከሳሽ ስለሚከራከሩበት ነገር የሚያስረዱ ግለሰቦች ናቸው።
👉በምስክርነት የተቆጠረ ግለሰብ እነዚህን አራት ዓይነት ጥያቄዎችን ሊጠየቅ ይችላል።
1ኛ
ዋነኛ ጥያቄ
📌ጥያቄው የሚቀርበው በምስክርነት ከቆጠረዎት ወገን በኩል ሲሆን ተከራካሪው በቆጠረዎት አግባብ ጉዳዩን እንዲያስረዱለት የሚያቀርብልዎት ጥያቄ ነው። የትኛውም ተከራካሪ ወገን በምስክርነት ሲቆጥርዎት ያውቁልኛል በማለት በመሆኑ ስለተጠየቁት ጉዳይ በሚያውቁት ልክ የሚያውቁትን በአግባቡ ቀጥተኛ መልስ መስጠት ወይም የማያውቁትን ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለኝም በማለት ወይም እርግጠኛ ባልሆኑበት ጉዳይ እርግጠኛ ባልሆንም በግምት ይህ ይመስለኛል በማለት ምላሽ ይስጡበት።
2ኛ
መስቀለኛ ጥያቄ
📌ይህ ጥያቄ በዋና ጥያቄ ላይ ለሰጡት የምስክነት ቃል በተቃራኒ ተከራካሪ ወገን የሚቀርብልዎት ጥያቄ ስለሆነ በትኩረት አዳምጠው ምላሽ መስጠት ይገባዎታል።
📌የመስቀለኛ ጥያቄ መሠረታዊ ዓላማው ቀድሞ ከሰጡት የምስክርነት ቃል ውስጥ ስህተትን ፈልጎ ማውጣት በመሆኑ ምስክር ለቆጠረዎት ወገን እና ለእውነታው ሲሉ ባለመደናገጥ ተረጋግተው ይመልሱ።
📌ልብ ሊሉት የሚገባው ነጥብ በዋና ጥያቄ ላይ ስላልተናገሩት ጉዳይ ጥያቄ ቢቀርብልዎት ስለዚህ ጉዳይ የተናገርኩት ነገር የለም፤ ብለው ምላሽ ይስጡ።
3ኛ
ድጋሜ ጥያቄ
📌ይህ ጥያቄ በዋና ጥያቄ የመለሱትን በመስቀለኛ ጥያቄ ሲጠየቁ በምስክርነት ቃልዎት ላይ ስህተት ወይም ልዩነትን ፈጥረው እንደሆነ ለማቃናት የሚቀርብ ጥያቄ ነው። በዋና ጥያቄ ላይ እንዲህ ብለህ መስክረህ በመስቀለኛ ጥያቄ ደግሞ እንዲህ ብለሃል የትኛው ነው እውነተኛ? በሚል መልኩ የሚቀርብልዎት ጥያቄ ነው።
📌ድጋሜ ጥያቄን ሲመልሱ እንዲህ ስለተባለው ጉዳይ ልናገር የፈለኩት እንዲህ በማለት ነው ብለው መልስዎትን በግልጽ ይስጡ።
4ኛ
የማጣሪያ ጥያቄ
📌የሚመሰክሩት ለከሳሽ፣ ለተከሳሽ ወይም ለጣልቃ ገብ ጥቅም ብቻ ብለው ሳይሆን ለትክክለኛ ፍትሕ በመሆኑ የሚሰጡትን ቃል ትክክለኛነትና እውነትነት ለማጥራት በማሰብ የምስክርነት ቃልዎትን ከሚቀበለው ዳኛ የሚቀርብልዎት ጥያቄ ነው።
📌የማጣሪያ ጥያቄ በማንኛውም ሰዓት እና ጊዜ እንዲህ ሲሉ ምን ለማለት ፈልገው ነው? በሚል አግባብ ሊቀርብልዎት ይችላል።
ይግባኝ መብት ነው
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
690
0
4
2
×