Репост из: ስለ ህግ
ሰ-መ-ቁ. 200482
ግራ ቀኙ ኢትዮጵያውያን ሆነው በውጭ አገር ህግ መሰረት በዛው አገር ጋብቻ በመካከላቸው እንደተደረገ በመግለጽ አንደኛ አመልካች ጋብቻ እንዲፈርስ እንዲሁም የጋራ ንብረት ክፍፍል እንዲደረግ ዳኝነት ሲጠይቅ ጉዳዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት በመሆኑ አቤቱታውን ተቀብሎ የመዳኘት ስልጣን ያለው በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 መሰረት የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው።
ሕጋዊ ጋብቻ ተፈጽሟል ለማለት የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል? የሚለዉ ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ነው። እንዲሁም በግራ ቀኙ መካከል በውጭ አገር ተፈጽሟል የተባለዉ ጋብቻ፣ በሕግ አግባብ የተፈጸመ ጋብቻ ነዉ የሚባል ከሆነና ጋብቻቸዉ በፍቺ ውሳኔ እንዲፈርስ የሚወሰን እንደሆነ የፍቺ ውጤት በምን አግባብ ይታያል? የሚለዉ ነጥብ ይነሳል። ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙን የጋብቻ ይፍረስልን ክርክር በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ የትኛዉ ነዉ? የሚለዉን ነጥብ መወሰንን ይጠይቃል ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙ ክርክር የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ጥያቄ ያስነሳል፡፡
የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ የዉጭ አካል ተካፋይ የሆነበትን የህግ ክርክር የሚመለከቱ መርሆዎችና ደንቦችን የሚያካተት ነዉ፡፡ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ ወይም የሕግ ግጭት [Conflict of laws] የሚመለከተዉ በተያዘዉ የህግ ክርክር የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት እንዳላዉ እና የትኛዉ ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን እንዳለዉ የሚወስኑ የህግ መርሆችን ነዉ፡፡ የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 (1፣ ሀ) መሰረት የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱ የፍትሕ ብሔር ጉዳዮችን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን ይደነግጋል፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 (1፣ ሀ)