🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ
በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ
ስልክ- 0935439820
ኢሜይል- khalidbinkebe@gmail.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ሽልማት ያለው ጥያቄ
***
👉የተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ በስር ወረዳ ፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ የከሳሽ ክስ በይርጋ ቀሪ ቢደረግ እንዲሁም

👉ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ቀሪ ሊሆን አይገባም በሚል መዝገቡን ወደ ስር ፍ/ቤት በነጥብ ቢመልሰው፤

👉"ተከሳሽ በዝህ የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ ያለበት ጊዜ መቸ ነው?"

ሀ/ ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ውሳኔ በሰጠ (እንደጉዳዩ አይነት) በ2 ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

ለ/ የስር ወረዳ ፍ/ቤት (በነጥብ በተመለሰለት አግባብ) በመዝገቡ የፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ ውሳኔ እስኪሰጥ ጠብቆ (እንደጉዳዩ አይነት) በ2 ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

🔥ቀድሞ ከነማብራሪያው (ሰበር የሰጠውን የህግ ትርጉም ጨምሮ) ለመለሰ የ15 ብር ካርድ እንሸልማለን🔥
https://t.me/khalidkebede


የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ? (ጠበቃ ካሊድ ከበደ)
***
ፍ/ቤቱ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ እና ተከሳሽ ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት በአንድ ላይ ሲያከራክር:-

👉ተከሳሽ ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከሳሽ ባቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ መሰረት ውድቅ አድርጎ ከሳሽ ወዳቀረበው ክስ ፍሬ ነገር ጉዳይ በማለፍ ግራ ቀኙን ለአንድ ዓመት ያክል ካከራከረ እና መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ሰጠ ብንል፤

"👉ተከሳሽ ፍ/ቤቱ ከአንድ ዓመት በፊት በሰጠው ብይን ውድቅ ባደረገበት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ (ጉዳይ) ላይ ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ የነበረበት/ያለበት ጊዜ መቸ ነው?"

ሀ/ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ውድቅ በማድረግ ብይን በተሰጠ እንደ ጉዳዩ ዓይነት በ2 ወር ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

ለ/ ፍ/ቤቱ ከሳሽ ባቀረበው የፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ ውሳኔ በሰጠ እንደ ጉዳዩ ዓይነት በ2 ወር ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

መልሱ:- "ለ" ነው። (የፌ/ጠ/ፍ/ሰ/ሰ/ ችሎት  በመ/ቁ. 231324 በቀን 26/03/2015 ዓ.ም የሠጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ይመልከቱ)


Репост из: Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
ገንዘብ እንዲከፍል የተወሰነበት የፍርድ ባለእዳ አፈጻጸም መዝገብ ሳይከፈት ገንዘቡን በፍርድ ባለመብት የባንክ አካውንት ቢያስገባ እና አፈጻጸሙ ሲጀመር የፍርድ ባለእዳ የተከፈለኝ ገንዘብ የለም ብሎ ቢከራከር አፈጻጸሙን የያዘው ፍርድ ቤት ገንዘቡ ከፍርድ ቤት ውጭ ተከፍሏል አልተከፈለም የሚለውን ማጣራት አለበት ከታች ያለው ውሳኔ

እዚህ ጋር የሚነሳው በሰበር መዝገብ ቁጥር 98263 ቅጽ 17 ላይ በፍርድ የተወሰነን ነገር በእርቅ ጨርሰናል ብሎ ፍርዱን ለማስለወጥ እርቁ ፍርድ ቤት ቀርቦ መመዝገብ እንዳለበት;ይህም መደረግ ያለበት በፍርድ የተገኘን መብት ፈጽሚያለው አልፈጸምኩም በሚል መቋጫ የሌለው ክርክር ስለሚከፍት ነው ከሚለው የሰበር አቋም ጋር እንዴት ይታያል


Репост из: Mizan Law / ሚዛን ሎዉ⚖️
የፌደራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_የሰበር_ሥነ_ሥርዓት_መመሪያ_ቁጥር_17_2015_.pdf
610.3Кб
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የሰበር ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ቁጥር
17/2015


Репост из: ስለ ህግ
ሰ/መ/ቁ. 237198
ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም
በፍታብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358 መሠረት በሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ (የመቃወም አቤቱታ ባቀረበው ላይ) ሊስተናገድ አይችልም።




Репост из: ነገረ ፈጅ Negere Fej
ሰ/መ/ቁጥር 221828 ሕዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም
አስተዳደራዊ መፍትሔ ለማግኘት የተደረገ ጥረት ይርጋን አያቋርጥም። አስተዳደራዊ መፍትሔ በመሻት ለጉምሩክ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት አቤቱታ በመቅረቡ የጠፋው ጊዜ ይርጋን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ኣለመሆኑን፣ ይርጋ ሊቋረጥ የሚችለው ስልጣን ለሌለው ፍርድ ቤት እንጂ ስልጣን ለሌለው አስተዳደራዊ ቅሬታ ሰሚ ተቋም አቤቱታ ሲቀርብ አይደለም።


የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረግበት ሁኔታ

ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሠረት

👉በስራ ባህሪው ምክኒያት ስራውን ከቦታ ወደቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን
ተቀጣሪ በአንድ ወር ጉዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ
የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ
ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር2200
የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የትራንስፖርት አበል በማንኛውም ሁኔታ
ከብር 2200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

👉 አንድ ተቀጣሪ በስራ ባህሪው ምክኒያት በመዘዋወር ለሚሰራው ስራ ለነዳጅ
ወጪ የሚከፈለው ጥሬ ገንዘብ ለትራንስፖርት አበል እንደተከፈለ ተቆጥሮ ከገቢ
ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ
መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ
ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የነዳጅ ወጪ በማንኛውም
ሁኔታ ከብር 2200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

👉አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታ እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ
መኖሪያ ቤቱ የሚጓጓዝበት የመስርያ ቤቱ የትራንስፖርት ሰርቪስ ቢቀርብም
ባይቀርብም ለዚህ ዓይነቱ የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር
600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

👉አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታው እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ
መኖሪያ ቤቱ ለመሄድ ለነዳጅ ወጪ በጥሬ ገንዘብ የሚፈለው የትራንስፖርት
አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

👉 አንድ ተቀጣሪ ሥራው ለማከናወን መደበኛ የሥራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ
ውጪ ሲንቀሳቀስ ለመጓጓዣ ወጪ የሚሰጠው ክፍያ ከግብር ነፃ ሊሆን
የሚችለው በስራ ላይ ባለው የትራንስፖርት ታሪፍ ወይም በሚያቀርበው ማስረጃ
ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከከፈለው የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት
የአገልግሎት ዋጋ ሊበልጥ አይችልም፡፡

👉አንድ የውጭ አገር ዜጋ ሥራን ለማከናወን ወደ የኢትዮጵያ ሲመጣ እና የውል
ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን
የሚችለው በተፈጸመው የቅጥር ውል መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ
ትራንስፖርት የአገልግሎት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚሆነው ለግል
መገልገያ ዕቃዎቹ የሚከፈለው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪሎ ግራም ሊበልጥ
አይችልም፡፡

👉አንድ ግብር ከፋይ ከመደበኛ መኖሪያ ቦታቸው ርቀው ሥራቸውን የሚያከናወኑ
ሠራተኞች ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ የሚያደርጉትን ጉዞ ውጪ የሚሸፍን
በሚሆንበት ጊዜ የዚህ ዓይነት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈፀመው
የቅጥር ውል ውስጥ ቀጣሪው ይህ ግዴታ ያለበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ሆኖም ለዚህ
ዓይነቱ ጉዞ የሚከፈለው ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረገው በአንድ የግብር ዓመት
ከሁለት የደርሶ መልስ ጉዞ ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

Source:- Ministry of Revenue


Репост из: የኢትዮጵያ ሕጎች / Ethiopian Laws 🇪🇹
254672 .pdf
892.3Кб
"...አንድ ዳኛ በየደረጃዉ ባሉት ሁለት ፍርድ ቤቶች ተሰይመዉ በጉዳዩ ላይ ዉሳኔ የሰጡበት አግባብ ከላይ በተጠቀሱት በነባሩ ሕግም ሆነ አሁን ተፈጻሚ እየሆነ ባለዉ የክልሉ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ ስለችሎት አሰያየም እና ዳኛ ከችሎት ስለሚነሳበት አግባብ በአስገዳጅነት የተዘረጉትን ደንቦች የጣሰ ሥነ ሥርዓታዊ ጉድለት ብቻ ሳይሆን የተከራካሪ ወገኖች ሥነ ሥርዓታዊ መብት፣ በሕገ መንግሥቱ እና በሌሎች ሕግጋት ጥበቃ የተደረገላቸዉ መሠረታዊ መብቶች እንዲጣስ፣ የሕግ የበላይነት እንዲሸረሸርና ሕዝቡ በዳኝነት አካሉ ላይ እምነት እንዲያጣ የሚያደርግ ዉጤት የሚያስከትል በመሆኑ እንደመሠረታዊ የሕግ ስህተት ተቆጥሮ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አለመታረሙ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4/ሀ እና ሸ) እና 10(1/ሐ) መሠረት ሊታረም የሚገባዉ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ብለናል፡፡"


Репост из: ስለ-ሕግ ⚖️ ABOUT-LAW
Unpublished Cassation v. 6.pdf
26.9Мб
ያልታተሙ የሰበር ውሳኔዎች

ቅፅ - 6

በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃና የህግ አማካሪ) ተሰብስበው የተዘጋጁ

ውሳኔዎቹ ሁሉም በ2014 ዓ.ም. የተወሰኑ ናቸው።


Репост из: ስለ ህግ
ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት
የሞት አደጋ በደረሰ ግዜ አንዳንድ የቅርብ ዘመዶች የሚኖራቸው መብት የሚታየው በፍ/በ/ህ/ቁ 2095 መሠረት ሰለመሆኑ እና የማች ሚስት ቀለብ በራሶ ስም መጠይቅ ምትችለው በራሶ ሰርታ መብላት የማትችል ወይም ቀለብ ለማገኝት በማትችለበት ደረጃ ላይ መሆኖን ስታረጋግጥ ነው።

















Показано 19 последних публикаций.