#የወንጀል_ክስ_መመስረቻ_ጊዜ
ፍርድ ቤት እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰርት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 9/1 የተከለከለዉን በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት የሚቆጠር ስለመሆኑ፡፡
ተጠርጣሪው የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄዉ ውድቅ ከሆነ በኋላ የዋስትና ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ይህንኑ አዲስ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለዚያዉ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ ሥነ ሥርዓታዊ መብት ያለዉ ስለመሆኑ፡፡
ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ያለቀ ከሆነ ተጠርጣሪው በድጋሚ ዋስትና ለመጠየቅ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑና በድጋሚ የሚያቀርበዉ የዋስትና ጥያቄ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ሳይመረመር በደፈናዉ ጥያቄዉ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል የተያዘዉ ሰዉ ክስ ሳይመሰረትበት ላልተወሰነ ጊዜ ታስሮ እንዲቆይ የሚያደርግ ትእዛዝ/ዉሳኔ መስጠት ስነስርዓታዊ አለመሆኑን አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 252231 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል