ሰውዬው መጠጥ ቤት ሲገባ ሁልጊዜ በአንዴ 3 ጠርሙስ ቢራ ያዛል። ሶስቱን ሲጨርስ ደግሞ ሌላ 3 ያዝዝና ይጠጣል። በቃ ልማዱ ይኸው ነው።
የመጠጥ ቤቱ ባለቤት በዚህ ልማዱ ተገርሞ ሰውዬውን ጠየቀው፣
"ሁልጊዜ በአንዴ ሶስት ጠርሙስ እያዘዝክ ስትጠጣ አይሃለሁ፣ ቢራው እንዳይሞቅብህ ለምን ተራ በተራ አንድ አንድ አታዝም?"
"ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየከኝ። ይኸውልህ ሁለት ጓደኞች አሉኝ። እነሱ አሁን ለሥራ ወደ ሌላ አገር ሄደዋል። ታዲያ ስንለያይ ማንም ሰው ብቻውን ሆኖ መጠጥ ሲያዝዝ ለማስታወሻ አብረን እንዳለን እንዲመስለን አንዱ 3 አዝዞ ይጠጣል። እሱን ሲጨርስ ደግሞ መድገም ከፈለገ አሁንም 3 አዝዞ እንዲጠጣ ቃል ተግባብተናል" ሲል መለሰለት።
አንድ ቀን ግን ሰውዬው መጣና 2 ብቻ አዘዘ። የመጠጥ ቤቱ ባለቤት በሁኔታው አዝኖ ሰውዬውን አነጋገረው፣
"በጣም አዝናለሁ! አንዱ ጓደኛህ ሞቶብህ ነው?"
"አይደለም?"
"ምነው ታዲያ ሁለት ብቻ አዘዝክ?"
"እኔ መጠጥ አቁሜ ነው"
ባሻዬ! እንዲህ ዓይነት ጓደኛ የት ይገኛል? እንዲህ ዓይነት ሰው ቢኖር አገራችን የት ትደርስ ነበር!!!
Via Tesfaye Hailemariam