ቅንጭብጭብ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ
እነሆ #ቅንጫቢ
ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።
ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


© Eyob Mihreteab Amlesom
#ተፃፈ: 02 March 2023

[ኒኮላይ ስቴፋኖቪች ሊዮንቴቭቭቭ!]
∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞

.

ቦምብም ወረወሩ፣ መትረየስ ደገኑ
አሉ ጋደም ጋደም፣ አሉ ጎንበስ ጎንበስ

አውሬ መስያቸው፣ አውሬ መስያቸው
ከሠው መፈጠሬን፣ ማን በነገራቸው

ቆርጬ ስነሳ፣ ቆርጬ ስነሳ ልበኔን ሳነሳ
ይፈሩኝ የለም ወይ፣ እንደ ዳልጋ አንበሳ

.
-
.

. [ጌታዬ]

እኛ እኮ በአድዋ ድል የምንኮራው፣ የምንመካው፣ አውርተን አውርተን፣ ተናግረን ተናግረን፣ ተደንቀን ተደንቀን፣ ተመክተን የማንጨርሰው በ'ዘራፍ ዘራፍ'፣ በ'አሉ ምናሉ' ሳይሆን የሚነበብ #አንብበን፣ አገናዝበን፣ አሠናስለን አወራርደን፣ የዚህን ዓለም የያኔና የአሁን ሁናቴ ጠንቅቀን አውቀን ነው፡፡

-

[እስኪ ይሄንን አንብብና አንተነትህን ውደደው። ቀንህን ምሉዕ አድርገው]

-

የዋሺንግተን ዩንቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር የሆኑት Raymond Jonas ስለ አድዋ የጻፉት ታዋቂ መጽሃፍ አላቸው፡፡ ርዕሱም ‘The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire’ ይላል፡፡

ኦሪጂናሉን ቨርዥን በዶላር ሂሳብ ከመግዛት አድዋ ሄዶ መዋጋት ይቀላል ብዬ ትቼው ነበረ፡፡ Muluken Tariku የተባለ ወሳኝ ሰው ተርጉሞት 100 ብር ገዛሁት፡፡

እንገርበው እስኪ፡፡

.
-
.

#ሀ

[ለመሆኑ፣ አድዋ ለኦሮሞው ምኑ ነው?]

“የጣልያን ሠራዊት በመገስገስ ላይ የነበሩትን የኦሮሞ ፈረሰኞች በተመለከተበት ወቅት የሚገባበት ጠፋው፡፡ ቀድሞ በሠራዊቱ ውስጥ ስለ ኦሮሞ ፈረሰኞች የተነገራቸው ኋላ ቀር እና ተራ ተዋጊዎች እንደሆኑ ነበር፡፡ በጦር ሜዳ ላይ የተመለከቱት ግን ፈረሰኞቹ እጅግ የተካኑ መሆናቸውን ነው፡፡

የጀነራል አርሞንዲ የበታች ከሆኑት መሃል ጂዮቫኒ ቴዶኒ ለሠራዊታቸው መሸነፍ ቁልፍ ሚና የተጫወቱት የኦሮሞ ፈረሰኞች መሆናቸውን መስክሯል፡፡ የወቅቱን አስፈሪ ሁኔታ ሲገልጽም “ፈረሰኞቹ ወደ ሸለቆው ሲወርዱ በድንገት የገነፈለ ጥቁር ባህር ይመስሉ ነበር” ብሏል፡፡

በርካታ የጦር መሪዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡ ሌተናል ኮሎኔል ጋሪባልዲ ፔናዞ እና ሌ/ኮ ማዞሊኒ የኦሮሞ ፈረሰኞችን ጦርና ጎራዴ በመፍራት በራሳቸው ሽጉጥ ራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡”

(ገጽ- 195/196)

.
-
.

#ለ

[ከድል በኋላ ዓለም ምን አለ?]

“የምኒሊክ እና የጣይቱ ዝና በሠፊው መናኘቱን ተከትሎ የተለያዩ አዳዲስ ክስተቶች ታይተዋል፡፡ በርካታ አውሮፓውያንም አዳዲስ ለተወለዱ ልጆቻቸው “ምኒልክ” የሚል ስም ሰጡዋቸው፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአድናቆት ደብዳቤዎች የምኒሊክን ቤተ-መንግስት አጣበውት ነበር፡፡ አንዳንድ ደብዳቤዎች ንጉሱን የገንዘብ ውለታ የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ አንዲት አድናቂያቸው በጻፈችላቸው ደብዳቤ አፄ ምኒልክ ለጅምር ቤቷ ማስጨረሻ የሚሆን 200 ፍራንክ እንዲልኩላት ጠይቃቸው ነበር፡፡”

(ገጽ 218)

.
-
.

#ሐ

[ጥልያንስ ምን አለ?]

“የጣልያን ሕዝብ ለድጋፍና ለተቃውሞ እጅግ ፈጣን ነው፡፡ ጦራቸው በ1895 ራስ መንገሻን ሲያሸንፍ ከፍተኛ የድጋፍ ሰልፍ አድርገው ነበር፡፡ በአምባላጌ፣ መቀሌ እና አድዋ አውደ ግምባሮች ሽንፈት ያጋጠመው ጦራቸውን ለማውገዝም ጊዜ አልፈጁም፡፡ የሮም ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የተቃውሞው ዋና መሪ የነበሩ ሲሆን “ቪቫ ምኒልክ” የሚል መፈክር ይዘው ነበር ለሰልፍ የወጡት፡፡”

(ገጽ- 236)

.
-
.

#መ

[ወደ ገደለው፣ የአድዋ ቁልፍ ትርጉም ምንድን ነው?]

“የአድዋን ድል ተከትሎ አፄ ምኒልክ የአፍሪካ የምንጊዜም ታላቅ መሪነታቸውን በደማቅ ቀለም አስጽፈዋል፡፡ ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን መፃኢ እድል የወሰነ ነበር፡፡ በዚህም የአድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነው፡፡ ምክኒያቱም በቀጣይ መቶ አመታት የአውሮፓ የበላይነት እና አገዛዝ በአፍሪካ አክትሟል፡፡ የዘመናዊት አፍሪካ የሉዓላዊነት መሠረት ድንጋይ የተጣለው አድዋ ላይ ነበር፡፡”

(ገጽ-244)

.
-
.

#ሠ

. [በመጨረሻም]

“ፈጣጣ ሁን፣ አትፍራ!” ይልሃል ኒኮላይ ስቴፋኖቪች ሊዮንቴቭ፡፡ ይሄንን ፀዴ ሠውዬ ተመልከትልኝ እስኪ!

[“ራሱን (በራሱ) የሾመው ዲፕሎማት”]

.
-
.

“ኒኮላይ ስቴፋኖቪች ሊዮንቴቭ በዩክሬን የተወለደ ሩስያዊ ነው፡፡ በወታደርነት ተቀጥሮ ሳለ የመጓዝ ልምድ ያካበተ ሲሆን በከፍተኛ ብድር ውስጥ በመዘፈቁ ከሩስያ በመውጣት ወደ ሌላ አገር ተጉዞ ሥራ ለመሥራት ይስናል፡፡ በመሆኑም ዕዳውን ለመሸሽ ከአገሩ በመውጣት በ1895 ወርኃ ጥር ላይ ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ፡፡

በአዲስ አበባ ቆይታው ከአፄ ምኒሊክ ጋር በመገናኘት የሩስያ ንጉስ መልዕክተኛ መሆኑን ገለጸላቸው፡፡ በቆይታውም ከጥር 1895 ጀምሮ የሩስያ አምባሳደር በመሆን ራሱን ሾመ፡፡ በመቀጠልም አፄ ምኒሊክን አግባብቶ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችን በመያዝ ወደ ሞስኮ ተጓዘ፡፡

ህዳር 1894 ላረፉት ንጉስ አሌክሳንደር የመታሰቢያ ስጦታ እንዲሆን ከአፄ ምኒሊክ የተለያዩ የኢትዮጵያ ውድ ጌጣጌጦችን ለሞስኮው ንጉሥ ልከዋል፡፡ ሐምሌ 17 ቀን 1895 ልዑካኑ በፒየትሮቭ ቤተ-መንግስት አቀባበል ያደረጉላቸው ንጉስ ኒኮላስ ነበሩ፡፡

ልዑካኑ ፒተርስበርግ ሲደርሱ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸው በንጉሱ ትዕዛዝ መሠረት በአገሪቱ ታላቅ በሆነው ሆቴል ዩሮፕ እንዲያርፉ ተደርገዋል፡፡አጋጣሚውን መጠቀም የቻለው ሊዮንቲቭ በንጉሡ ዘንድ ተመራጭ ሆነ፡፡ በመሆኑም ንጉሡ በኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አድርገው ሾሙት፡፡ ልዑካኑ ነሐሴ 9 ቀን 1895 የመልስ ጉዞአቸውን ሲጀምሩ 135 የቤርዳን ጠመንጃዎች በስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ራሱን የሾመው ሊዮንቲቭ ምስጋና ይግባውና በአዲስ አበባ ከነበሩ በርካታ አውሮፓውያን መካከል የሩስያ ተወካይም እድል አገኘ፡፡

አፄ ምኒሊክ ወደ አድዋ ለመዝመት በሚዘጋጁበት ወቅት ሊዮንቲቭ ወደ አውሮፓ አቀና፡፡ በአውሮፓ ቆይታውም ኢትዮጵያን እና ጣልያንን ለመሸምገል ሞክሯል፡፡ ከጣልያን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አልቤርቶ ዲ ብላንክ ጋር ያደረገው ውይይት ውጤት ስላላስገኘለት ድርድሩ ሳይሳካ ቀረ፡፡

ሊዮንቲቭ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው ከጦርነቱ በኋላ ነበር፡፡ በወቅቱ አፄ ምኒሊክ ለጣልያኗ ንግስት ማርጋሪታ የልደት ስጦታ ይሆን ዘንድ 50 ምርኮኞችን በነፃ ለቀቁ፡፡ በመቀጠልም በሊዮንቲቭ አግባቢነት ለሩስያው ንጉስ በዐለ ሹመት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በወርኃ ሐምሌ ሌላ 50 ምርኮኞችን ለቀቁ፡፡”

(ገጽ 239-240)

-

ሠው ሞቷል ሠው ሊያድን
ሠው ሠውን ሲያከብር፡፡

-

እመነኝ፣ ከየትኛውም አፍሪቃዊ የተለየው ኩሩው ማንነትህ የተገነባው #በዛሬው_ቀን ላይ ነው፤ #አድዋ ላይ ነው፡፡


መልካም የድል በዓል


ዓድዋ . . .


Репост из: መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine
መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 10.pdf
14.0Мб
ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባቢያን

መጽሔታችን እንዲህ እንዲህ እያለች ቅጽ አንድን ወደማገባደዱ ደርሳለች። ይህ የቅጽ አንድ የመጨረሻ እትም ነው። እስከዛሬ ለቃለ መጠይቅ በመተባበር፣ ጽሑፍ በመላክ፣ ሃሳብ አስተያየቶቻችሁን በመለገስ፣መጽሔታችንን በማንበብና በማስተዋወቅም ጭምር ለተራዳችሁን ወዳጆች መኮንን ደፍሮ፣ ሄኖክ አባይነህ፣ መንበረ ማርያም ኃይሉ፣ ፀደይ ወንድሙ (ዶ/ር)፣ አንተነህ አክሊሉ፣ ጉቺ ሽመልስ፣ ሱራፌል አየለ፣ ምግባር ሲራጅ፣ ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ፣ ሲራክ ወንድሙ፣ ሳራ አህመድ፣ ትሬዛ ዮሴፍ፣ ዕፀ ገነት መልካሙ፣ ሳሚያ ጡሃ፣ ጽዮን ልሳኑ፣ በረከት ጌታነህ፣ ተኩ ዣን፣ ይርዳው ግፎ (መምህር)፣ ሰሎሜ መብራቱ፣ ትዕግስት ደሣለኝ፣ ውብ አረገ አድምጥ፣ ናትናኤል ማናዬ፣ ጃፈር መጻሕፍት፣ ኤዞፕ መጻሕፍት እና ሌሎችም በስም ላልጠቀስናችሁ ወዳጆች በሙሉ ምስጋናችን ከልብ ነው። አንባቢያንም እንዲሁ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ስለምታነቡን ደስ ይለናል። እናመሰግናለን። ለቅፅ ሁለት ቢስተካከል የሚሉትን በኢሜይል አድራሻችን ይላኩልን። እስከምንመለስ ቸር ሰንብቱልን።

መልካም ንባብ!

https://t.me/Medinamagazine

በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL

https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj

ለአስተያየትዎ

medinadigitalmagazine@gmail.com

ጥር 2017 ዓ.ም


Репост из: መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine
መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 9.pdf
15.7Мб
ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን፥ መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 9 እትሟን ይዛ ተመልሳለች።

ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል።

ስለምታነቡን እናመሰግናለን።

https://t.me/Medinamagazine

በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL

https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj

ለአስተያየትዎ

medinadigitalmagazine@gmail.com

ኅዳር 2017 ዓ.ም


Репост из: መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine
"ዋቢ ሳቢ ሕይወትን ከነጉድለቱ እንድንቀበል የሚያስተምር ውብ የአኗኗር ዘይቤ ነው። አንድ ገጸ-ድር ላይ ያገኘኹት ጽሑፍ አንድ ሰው አብርሆት ላይ የሚደርሰው ጉድለቱን መቀበል ሲችል እንደሆነ ይናገራል።"

መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 6
ሚሊየን


Репост из: መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine
መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 8 (1).pdf
18.7Мб
ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን፥ መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 8 እትሟን ይዛ ተመልሳለች።

ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል።

ስለምታነቡን እናመሰግናለን።

https://t.me/Medinamagazine

በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL

https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj

ለአስተያየትዎ

medinadigitalmagazine@gmail.com

ጥቅምት 2017 ዓ.ም


መልክአ ሕይወት

ቧልትን ከፈገግታ
ሣቅን ከፌዝ ጋራ
ባንድ ላይ ቀይጠን
አቅልመን በጥብጠን
በሐዘን ባሕር ላይ ብናንቆረቁርም
ባሕሩ ሰፊ ነው መልኩን አይቀይርም

ከበዕውቀቱ ስዩም (ስብስብ ግጥሞች)
Art work by Edvard Munch - Melancholy (1894-96) https://t.me/daily
t
houghtsdailythoughts
href='' rel='nofollow'>


#amazing_facts

1. የአለም ትንሹ መፅሃፍ፡ ትንሹ የታተመ መጽሐፍ "Teeny Ted from Turnip Town" ነው የሚለካው 0.07 ሚሜ x 0.10 ሚሜ ብቻ ነው።  focused ion beam በመጠቀም የተፈጠረ ሲሆን በኤሌክትሮን ማይክሮስኮፕ ብቻ ነው የሚነበበው።


2. በጽሕፈት መሳርያ ላይ የተጻፈ የመጀመሪያው ልቦለድ፡ ማርክ ትዌይን የቶም ሳውየር አድቬንቸርስ (1876) በጽሕፈት መሳርያ ላይ የተጻፈ የመጀመሪያው ልቦለድ እንደሆነ ይታመናል፣ ይህም በሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ጊዜ ነው።


3. ረጅሙ የመፅሃፍ ርዕስ፡ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የረዥሙ መጽሐፍ ርዕስ 3,777 ቃላትን ይዟል!  እ.ኤ.አ. በ2019 የታተመው የህዝብ ፖሊሲ ​​ላይ የጣልያን መጽሐፍ ነው።


4. የመጀመሪያው ኢ-መጽሐፍ፡ የመጀመሪያው ኢ-መጽሐፍ በ1971 ሚካኤል ኤስ ሃርት የዩኤስ የነጻነት መግለጫን ዲጂታል ሲያደርግ ተፈጠረ ነው ።  ይህ ፕሮጀክት በመጨረሻ የዓለማችን ትልቁ ዲጂታል ቤተ መፃህፍት ፕሮጀክት ጉተንበርግ እንዲፈጠር አድርጓል።

5. የመጀመሪያው የህዝብ ቤተ መፃህፍት፡ በአለም የመጀመሪያው የህዝብ ቤተ መፃህፍት የተቋቋመው በ1833 በፒተርቦሮ ፣ ኒው ሃምፕሻየር ፣ አሜሪካ ነበር።  መጽሐፍትን በነጻ ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ በታክስ ዶላር የተደገፈ የመጀመሪያው ቤተ መጻሕፍት

via jafer books


#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ለጊዜ_ጌታ_የተፃፈ_ደብዳቤ!
.
.
ፈጣሪዬ ሆይ በሰማያት የምትኖር..
ብዙ መንገድ መተናል፣
ብዙ ትዝታዎችን ቋጥረናል፣
ብዙ ተስፋዎችን ሰንቀናል፣
ብዙ ሰዎችን አቅርበናል፣
ልብ ለልብ ተሳስረናል፣
መኖር አስከፊ ገፅ ቢኖረውም!
ለመሰንበት ጓጉተናል፣
ገና መኖርን ናፍቀናል፣
አዲስ ትዝታዎችን መመስረት አስበናል፣
በጥልቅ ፍቅር ወድቀናል፣
አብሮ ማርጀትን ተመኝተናል፣
ሞትን አርቀህ ትንሽ ጊዜ ስጠን ብለናል፣

እባክህ ጌታ ሆይ..
ቅጣት ያልካት ምድር አቅፋ አኑራኛለች፣
ስረግጣት ቢመራት ልትውጠኝ 'ጠብቃለች..!
እማይቻልህ የለ
ሁሉ በጅህ አይደለ!
በቃ ጊዜን አቁመው ቀናተም ይዘግዩ፣
የሰው እድሜ ይርዘም የወጣትነቱ፤

ኧረ ባክህ ጌታ ያላየነው አለ..
አታሳልፍብን ትንፋሽህን አትንሳን
ከመምጣታችን በፊት መቆየት እንሻለን..
ወይ ደግሞ ሁሉም ይቅር! ሁሉም ባንዴ ይጥፋ፣
የቀደመው ሞቶ! ቀሪው ከሚከፋ!
ወይ ሁሉም ባንድ ይሁን..!!
.
.
.

✍️Aman😑 YTZ


#Arichitecture


ሰውዬው መጠጥ ቤት ሲገባ ሁልጊዜ በአንዴ 3 ጠርሙስ ቢራ ያዛል። ሶስቱን ሲጨርስ ደግሞ ሌላ 3 ያዝዝና ይጠጣል። በቃ ልማዱ ይኸው ነው።

የመጠጥ ቤቱ ባለቤት በዚህ ልማዱ ተገርሞ ሰውዬውን ጠየቀው፣

"ሁልጊዜ በአንዴ ሶስት ጠርሙስ እያዘዝክ ስትጠጣ አይሃለሁ፣ ቢራው እንዳይሞቅብህ ለምን ተራ በተራ አንድ አንድ አታዝም?"

"ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየከኝ። ይኸውልህ ሁለት ጓደኞች አሉኝ። እነሱ አሁን ለሥራ ወደ ሌላ አገር ሄደዋል። ታዲያ ስንለያይ ማንም ሰው ብቻውን ሆኖ መጠጥ ሲያዝዝ ለማስታወሻ አብረን እንዳለን እንዲመስለን አንዱ 3 አዝዞ ይጠጣል። እሱን ሲጨርስ ደግሞ መድገም ከፈለገ አሁንም 3 አዝዞ እንዲጠጣ ቃል ተግባብተናል" ሲል መለሰለት።

አንድ ቀን ግን ሰውዬው መጣና 2 ብቻ አዘዘ። የመጠጥ ቤቱ ባለቤት በሁኔታው አዝኖ ሰውዬውን አነጋገረው፣

"በጣም አዝናለሁ! አንዱ ጓደኛህ ሞቶብህ ነው?"

"አይደለም?"

"ምነው ታዲያ ሁለት ብቻ አዘዝክ?"

"እኔ መጠጥ አቁሜ ነው"

ባሻዬ! እንዲህ ዓይነት ጓደኛ የት ይገኛል? እንዲህ ዓይነት ሰው ቢኖር አገራችን የት ትደርስ ነበር!!!

Via Tesfaye Hailemariam


#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ትንሽ_ስለ..!

ክፍል - ፫
.
.
.
የህይወት መንገዷ ሰፊ ነው፤ ገደሏ ጥልቅ ነው፤ ወንዞቿ ለሁሉም እኩል አይፈሱም፤ ተራራዎቿ ሁሉን አይማርኩም!! አየህ ላንተ የተፈጥሮ ድንቅ ውበት ያልከው ተራራ የሌላ ሰው አድካሚ መመላለሻ መንገድ ነው!!
 
    እሩቅ ሳንሄድ እዚሁ ከሰፈራችን እንኳ ባለፈው ጫማ እያስጠረኩ ሰማዩ ማንጎዳጎድ ጀመረ ከዚያም "እሰይ ተመስገን ዝናብ ሊዘንብ ነው በቃ ወደ ቤት ሄጄ ወይ መጽሐፍ አነባለሁ ወይ ጥሩ እንቅልፍ እተኛለሁ!" አልኩ። ይሄኔ ታዲያ ጫማዬን የሚያፀዳው ፈላ ፊቱን ኩስኩስ አድርጎ "እኔ ግን እንዳይዘንብ እማፀናለሁ ምክንያቱም ከዘነበ የኔና የወንድሜን ምሳና እራት ይቀማናል!" አለኝ።

እኔም በመገረም 'እንዴት?' አልኩት..

እርሱም.."ትናንት ሲዘንብ ውሎ ለቁርስና ምሳ ምንም ስላልሰራን ፆማችን ነው የዋለን!! አሁን እሚዘንብ ከሆነ ደግሞ በዝናቡ መስራት ስለማንችል ምሳና እራታችንን ይቀማናል!" አለኝ።
በህይወቴ እንደዚያን ቀን አፍሬ አላውቅም!!
.
.

(ከ #ትንሽ_ስለ..! ተከታታይ ልቦለድ የተቀነጨበ)

👇👇👇👇👇👇👇

t.me/YelbeDrset

👆👆👆👆👆👆👆
ቤተሰብ ይሁኑ!


የሆነ ቀን አሞኝ አልጋ ላይ ብዙ ጌዜ ከረምኩ ምኔም እምድን አይመስልም ነበር እሚያስቡልኝ አምላክ ሞቴን ቢያፋጥንልኝ ጥሩ እንደሆነ በልባቸው የተመኙልኝ ይመስለኛል ...

እኔ ግን ዳንኩ

የሆነ ግዜ ሱስ ጀመርኩ ጫት ሲጋራ መጠጥ ፊቴን እስኪቀይረው ተከተብኩ አዬ መና ቀረ ተባልኩ

እኔ ግን ሱስ አቆምኩኝ ።

የሆነ ቀን ጓደኞቼ ሁሉ አልፈው እኔ አስረኛ ክፍል ወደኩ ሁሉም በጋራ አዘኑልኝ ብለን ነበረ አሉኝ ሰፈር ቀረ አሉኝ እኔ ግን ተመልሼ private ተፈትኜ አልፌ እስከሁለተኛ ድግሪ ድረስ ተማርኩ

የሆነ ግዜ እናቴ ለቆሶ ልቴድ ፈልጋ ነጠላ ስትበደር አይቻት እኔ ሳድግ አምስት ቅያሪ ነጠላ እገዛልሻለሁ አልኩኝ የሰሙ ሰዎች ሳቁብኝ ለምን እንደሳቁ አላቅም እኔ ግን ስራ ስይዝ አረ አምስት ነጠላ ምን ይሰራል እያሉኝ ጥለቱን እየቀያየርኩ ገዛው ....

ትላንት ብዙ አይሆንምን አልፌያለሁ ። ብዙ አበቃለትን ተሻግርያለሁ ፣ ነገ የተሻለ እንደሚሆን ትላንት ምስክሬ ነው ።

መሞከር ፣መማር፣ ለመሻሻል መጣር ፣መታገስ አናቆምም ሁሉም ይስተካከላል ❤
©Adhanom Mitiku


Репост из: መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine
መዲና ቅጽ1 ቁጥር 7.pdf
18.5Мб
ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን

መጽሔታችን በአዲስ ዓመት ቅጽ 1 ቁጥር 7 እትሟን ይዛ ተመልሳለች።
ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል።
ስለምታነቡን እናመሰግናለን።

https://t.me/Medinamagazine

በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL

https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj

ለአስተያየትዎ

medinadigitalmagazine@gmail.com

መስከረም 2017 ዓ.ም


ገላጣ
(በእውቀቱ ስዩም)

ዛሬ የተከበረውን የዓለም አቀፍ ራሰ በራዎች ቀን ሳልዘክር ወደ ምኝታየ ብሄድ የሶቅራጥስ አጽም ይወጋኛል፤

ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “በራሕ”የሚለውን ቃል ሲተረጉሙት-“ በራ፥ መላጣ፥ ራሰ ገላጣ፥ ከቦታው የታጣ፥ የራሱ ቁርበት፥ ሳንባና ጉበት የሚመስል “ ይላሉ (መጽሀፈ ስዋሰው ወግስ ፥ ገጽ 287፤ በትርጉሙ ውስጥ ያሉትን አሉታዊ ቃላት ብዛት ለተመለከተ አለቃ ባለ ሙሉ ጠጉር እንደሆኑ መገመት አያቅተውም፤

አለቃ “ራሰ ገላጣ “ ቢሆኑ ኖሮ “ራሰ በራ ” የሚለውን ሲተረጉሙ “ራሱ የበራለት፤ ታጥቦ የተወለወለ የንጉስ ብርሌ የመሰለ፥ መላጣ፥ ከፎረፎርና ከቅማል ስጋት ነጻ የወጣ “ብለው ሊተረጉሙት ይችሉ ነበር፤

በታሪካችን ትልልቅ ራሰ በራ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ነበሩ፤ ከጌቶች መካከል ብንጠቅስ፥ ራስ ስኡል ሚካኤል፥ አጤ ምኒልክ፥ ራስ ዳርጌ፥ መለስ ዜናዊ፥ ከደራሲ ፥ሀዲስ አለማየሁ፥ ጃርሶ ኪሩቤል ሞትባይኖር፥ መንግስቱ ለማ፥ ሊጠቀሱ ይችላሉ፤ ( ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ራሰ በራ ነው ወይስ የተሸጋሸገ ጎፈሬ ነው የሚለው በታሪክ ሲያከራክር ይኖራል )

“ለኔ እየሰጠችኝ ደረቁን እንጀራ
እስዋ በነካካው በራሰው ልትበላ"

የሚለውን ጥንታዊ ውስጠ ወይራ ዘፈን መናሻ አድርገን ብንናገር ፥ ሴቶች ከሚያበጥር ይልቅ የሚወለውል ወንድ የበለጠ እንደሚማርካቸው መረዳት አያቅትም፤

ስለ ጸጉር ጨዋታ በተነሳ ቁጥር ፈገግ የምታሰኝኝ ድምጻዊ አብነት አጎናፍር የተናገራት ናት፤ አብነት እንዲህ አለ፤

“ ከጥቂት ጊዜ በፊት ጸጉር ላስተክል ቱርክ ሄጄ ፤ ጸጉር የሚተከለው ሰውየ መላጣ መሆኑን ሳይ ትቸው ተመለስኩ"🙂

በዚህ አጀንዳ ላይ ሌሎች የከተማው ነዋሪዎች ያላቸውን አስተያየት ለመስማት ከፈለጉ ከታች የጫንኩትን ትረካ ያድምጡ።


የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።
የቱ ጋር መሰለህ?
በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴት ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።
የቱ ጋር መሰለህ?
የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በሀይኪንግ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ሳትቆም ለፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።
ትዝ አለህ?
ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።
ምላሹስ የከፋው መቼ ላይ ሆነና?
ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።
ትዝ አለህ?
መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?
ትዝ አለህ?
በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?
ትዝ አለህ?
የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ?
ብለህ ስትቆዝም …
እንዲያ ነው አይዋ
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።
ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
ኧረ ስከን ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!


የአብዛኛው ፍልስፍና መፅሐፍ ቶቻችን የቃላት ውስንነት ይታይባቸዋል ከደራሲው የሚመነጩ አንዳንዱም ከዘርፉ ባህሪ አንባቢም ግር ላለማሰኘት ፀሐፊዎች በቅንፍ የእንግሊዘኛውን ቢያስቀምጡ መልከም ይመስለኛል
ይሄንን ከዘረያቆብ ገፅ ነው ያገኘሁት ተከተሏቸው አሪፎች ናቸው
የፍልስፍና መዝገበ ቃላት
=============
1. Pragmatic - ገቢራዊ
2. Statuesque - ነቢር
3. Hierarchy - የላዕላይነት ተዋረድ
4. Normative - የልኬት-ሚዛን
5. Theory - ህልዮት
6. Ideal - ተምኔታዊ-ስዕል
7. Moral sense - ግበረ-ገባዊ ህዋስ
8. Collective - ጋርዮሻዊ
9. Soul-Body dichotomy - የነፍስና ስጋ ኩፋሌ
10. Compromiser - አመቻማች
11. Ethos - የአኗኗር-ዘይቤ-መንፈስ
12. Aristocratic - ባላባታዊ/ጌትነታዊ
13. Moderation - ታጋሽነት
14. Courageous - ደፋርነት
15. Indulgence - ልልነትን
16. Passivity - ቀሰስተኛነት
17. Chaotic - ውጥንቅጥ
18. Master Morality - የጌትነት ምግባር
19. Slave Morality - የደካሞች ምግባር
20. Life-negating - ህይወትን የሚያማርር
21. Life-affirming - ህይወትን የሚያፈቅር
22. moral supremacy - ግብረገባዊ ልእልና
23. Contextual background - አውዳዊ ዳራ
24. Intuition - ውስጠተ-ስሜት
25. Oedipus Complex - የወንድ ህቡዕ ፆታዊ ምኞት
26. Electra Complex - የሴት ህቡዕ ፆታዊ ምኞት
27. Classics - ብሉያት
28. Humanists - ሥነ ሰብዓውያን
29. Renaissance - ዘመነ ትንሳኤ
30. Critical Thinking - ነቂሳዊ እሳቤ
31. Artificial Intelligence - ሰው ሰራሽ አስተውሎት
32. Sculpture - ኪነ ቅርፅ
33 Painting - ኪነ ቅብ
34. Premises - መነሻ ሐሳቦች
35. Argument - ነገረ ሐሳብ
36. Critical Social Theory - የማህበራዊ ነቀሳ ህልዮት
37. Thesis, Anti-thesis, Synthesis - አንብሮ፣ ተቃርኖ፣ አስተፃምሮ
38. Virtue - ምግባረ እሴት [ሰናይነት]
39. Altruism - ለሌላው ቅድሚያነት
40. Contemporary - ዘመነኛ
41. Existentialism - የአኗኗር ፍልስፍና
42. Authority - መሪ ሊቅ
43. Absurd - ወለፈንድ
44. Prejudice - ፅልማዊነት
45. The Problem of Evil - ነገረ እኩይ
46. Moral Evil - ክፋት
47. Scholastic - መጽሐፋዊ
48. Fallacy - ተፋልሶ
49. Historical Background - ታሪካዊ ዳራ
50. Being/Existence - ኑባሬ
51. Term - አኃዝ
52. Dialectic - ሕገ-ተቃርኖ


#ሐዲስ ዓለማየሁ እና ፍቅር እስከ መቃብር
(Abrham Tsehaye)

ዘመኑን በልኩ የሚስሉት አሉ። የዘመን ልኮች፤ ፖለቲካው እነሱን የሚመስል፣ ራሳቸው ስነ ጽሑፍን የሚያክሉ፤ የጊዜውን ምጣኔ ሃብት ለማውራት ማጣቀሻ የሚሆኑ አሉ። የዘመን ዋርካዎች!

#ሐዲስ

ሩዶልፍ ኬ ሞልቪየር ጽፈው የሰነዱት የጥበብ ሰዎቻችንን የያዘው ዶሴ 'ጥቋቁር አናብስት' ተብሎ ወደኛ ቋንቋ ተመልሷል። እዚሁ ላይ ስለሐዲስና መጽሐፋቸው የተቀነጨበ ታሪክ አለ። ሁኔታውን ስናወሳ ልክ እንደ ድርሰቱ ደራሲውም ይታወሱ በሚል ሐቅ ነው! መጽሐፉ ወደቴሌቪዥንና አንተርኔት መስኮቶች ብቅ ማለቱን ተከትሎ መሆኑም ይታወቅ።

#ሐዲስ ዓለማየሁ የዛሬ 59 ዓመት በ1958 ዓመተ ምህረት ፍቅር እስከ መቃብርን ወለዱ። ይህ የመጀመሪያ ትልቁ ልብወለዳቸው መፃፍ የተጀመረው ግን በግምት ከ20 ዓመታት በፊት በዋሺንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋና ፀሐፊ እያሉ ( ከ1939–1943 ) ነበር። በ1938 ማለት ነው! ሃያ ዓመታት የተማጠ ያልቸኮለ ጥበብ!

መጽሐፉ በመጀመርያ በእንግሊዝኛ ተሞክሮ ነበር፤ ኒውዮርክ ለሚገኝ አሳታሚ ልከውት ኅትመት ቤቱ ለማሳተም ፈቃደኛ አልሆን አለ እንጂ። መልሰው በአማርኛ መጻፍ ጻፉት።

ፍቅር እስከ መቃብር በየመሐሉ ለረዥም ጊዜ ተቋርጧል። ለምሳሌ ደራሲው በእንግሊዝ አምባሳደር ሳሉ ( 1953–1958) ባለቤታቸው አረፉ፤ በዚህ ሀዘናቸው የተነሳ ለአንድ ዓመት ያህል እርግፍ አድርገው ትተውት ቆይተዋል።

ከስራ ወደስራ በተዛወሩ ቁጥር ሌሎችም ረዣዥም መቆራረጦች ነበሩ። ሲጨርሱትም ጥሩ መጽሐፍ መስሎ እንዳልታያቸው ይነገራል። ያው ልከኛ የጥበብ ሰው አይረካም! ሐዲስ ያለምንም ማቋረጥ ሲጽፉ ፍሰቱ ጥሩ እንደሚሆን የሚያቋርጣቸው ሲኖር ግን እንደገና ካቆሙበት ለመቀጠል ሃሳባቸው ስለሚበታተን ፍሰቱን ለማስኬድ እንደሚቸገሩ ያስረዱ ነበር። በአጠቃላይ መጽሐፉ በአስቸጋሪ ጊዜያት የታጀቡ የብዙ ቅጥልጥል ውጤቶች ነው፡፡

ሞልቪየር ይህ አለመመጣጠን ባለቀው መጽሐፍ ላይ በጉልህ ይታያል ባይ ናቸው። መጽሐፉን ጽፎ ለመጨረስ ብዙ ጥረት ጠይቋል፤ ለማሳተምም ገንዘብ እስከመበደር ተደርሷል። ይህ ታልፎ ታትሞ የወጣው ፍቅር እስከ መቃብር በስተመጨረሻ በጥሩ ሁኔታ በመሸጡ ደራሲው እጅግ ተደስተውም ተገርመውም ነበር። የጻፉት ሲነበብ ራሱ ትልቅ ሽልማት ነው!

#ህትመትና ሽያጭ

በመጀመሪያው ዙር 5,000 ቅጂዎች ብቻ ነበር የታተመው። በሚቀጥለው 7,000 ቅጂዎች ደረሰ። እስከ 1978 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ በጥቅሉ ስድስት ጊዜ ያህል ተደጋግሞ ታትሟል። መጽሐፉ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ሲያገኝ ከታተመ ከጥቂት ዓመታት በኋላም በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ገብቶ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የማስተማሪያ መጽሐፍም ሆነ።

#ደራሲውና ገጸ ባሕሪያቱ!

በዛብህና ጉዱ ካሳ

በፍቅር እስከ መቃብር ውስጥ ብዙ ክፍሎች ከደራሲው ሕይወት የተቀዱ ናቸው ። በጎጃም ደብረወርቅ እና ዲማ ያሉት ታሪኮች ደራሲው በቅኔ ተማሪነታቸው ያሳለፉት ሕይወት ግልባጭ ነው። በዛብህ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣና በከተማው ውስጥ የሚያጋጥሙት ሁነቶች ሐዲስ ራሳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1918 ዓ.ም ከጎጃም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የታዘቡት ገጠመኝ ጥርቅም ነው።

በአጠቃላይ ሐዲስ ልብወለዱ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ገፀ ባህሪያት ውስጥ ራሳቸውን በተወሰነ መልኩ እንደሚያዩ ይናገራሉ። የመጀመሪያው ወደ አዲስ አበባ ከመምጣቱ በፊት የቤተክርስቲያን ትምህርት የቀመሰው እና እንደ ሐዲስ ለቤተሰቡ ብቸኛ ልጅ የሆነው የልብወለዱ ዋና ገፀ ባህሪ በዛብህ ሲሆን ሌላው ደግሞ በማኅበረሰቡ ሳይሆን በራሱ ሀሳብ የሚመራው ይኼም ዘወትር ከራሱ ወገኖች እና ከመደብ ፍላጎቶቹ ጋር ቅራኔ ውስጥ የሚያስገባው ጉዱ ካሳ ነበር ።

#መቼት

የልብወለዱ መቼት ከሐዲስ የልጅነትና ወጣትነት ሕይወት ጋር በተወሰነ ደረጃ ይገጥማል (የተወለዱት በ 1902 ነበር )። በእርግጥ ልብወለዱ ከዚህ ትንሽ ቀደም ብሎ ይጀምራል። የልብወለዱን መቼት በሀያኛው ከፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ ወደ ኃይለሥላሴ የግዛት ዘመን የመጀመሪያ ዓመታት ( ስልጣን የያዙት በ 1923 ዓ.ም ነው ) ይጠጋል። ሞልቪየር ሲያክሉ "ከሐዲስ ጋር ይህንን የጊዜ ሰሌዳ አውጥተን ነበር ፤ ነገር ግን ሐዲስ በልብወለዱ ውስጥ የተጠቀሱ አንዳንድ ልማድና ስርዓቶች የጥንት እንደነበሩ አንዳንዶቹም እስከ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ዘመን ( 1847- 1861 ) ወደኋላ እንደሚለጠጡ ነግረውኛል" ብለዋል።

#በስተመጨረሻ!

ሐዲሳችን በመጨረሻው የሕልፈት ሰዓታቸው ግን እንደተለመደው፣ እንደባሕላችን እሳቸውም እንደሌሎቹ ትጉኃን እጦት ጎብኝቷቸዋል። ደራሲ ዘነበ ወላ በአይፐሲዜ መጽሐፉ ላይ እንዳወጋን እንዴት ነው የፈረንካ ነገር ሲላቸው አሁን አሁን ይቸግረኝ ጀምሯል ብለውታል። ተደጋግሞ የሚታተመው የፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍዎስ አላቸው። "ማን ጠይቆን ይታተማል ብለህ ነው?!" ሲሉ መልሰው ነበር።

ሰዎቻችን አኑረውን የማይኖሩት ነገር የድግግሞሻችን የነውር ቀለም ይመስላል! ነጋዴዎችም ነግደው ያተርፉባቸዋል። እኛም ለምን አለማለት ለምዶብናል!


Репост из: መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine
ምጥን ቅጽ.pdf
14.9Мб
ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት ቤተሰቦች

እንኳን ለ2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ! ለአዲስ ዓመት ገጸ በረከት እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ የጳጉሜን ልዩ ዕትም ይዘንላችሁ ቀርበናል። የጳጉሜ ዕትም በመሆኗ ከወትሮ በተለየ በገጽ ከመመጠኗ በቀር ያጎደለችው ነገር የለም። ስለምታነቡን እናመሰግናለን።

መልካም አዲስ ዓመት!


በዚህ ዓመት ፣ ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ ፥ ትንሸ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ቦታ መሠደጃ ፥ ምናለበት ፤
ለምናልባት ብንተውለት?!

በአንጎላችን መላወሻ ፣ ትንሽ ቦታ እንተውለት
‹‹ምናልባት›› የምንልበት!!
ልክ እንደአምና ለዚህ ዓመት ።

ብንጣላ መታረቂያ ፥ ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሠር ይቅር ማያ ፥ ትንሽ እንተው ! መጠለያ ፡፡
ጥግ ድረስ የለም ስራ ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ ፤
በልባችን ደግ በኩል ፣ የጳጉሜ አይነት ፥ እንፈልግ ባዶ ቦታ ።
----------------------------
ነብይ መኮንን - ጳጉሜ 5 2005 ዓ.ም

Показано 20 последних публикаций.