ማኅበረ መድኀኔዓለም መዝሙር ጥናት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✝️ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ግጥሞችን ከነዜማቸው እንለቃለን ✝️
🙏🙏🙏 (መዝሙር ጥናት) 🙏🙏🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


✞ የሚያዚያ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ማክሰኞ ሚያዝያ 7 - ቅዱስ እያቄም - እረፍቱ - በኮተቤ ሐና ማርያም ቤተክርስቲያን

አርብ ሚያዚያ 9 - አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ  እረፍታቸው - በቤተል ሚካኤል ቤተክርስቲያን በቀበና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን - በወይራ ሰፈር ቅድስት አርሴማ ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

ረቡዕ ሚያዝያ 15 - መጥምቁ ዮሐንስ - አንገቱ ለ15 ዓመት ያስተማረችበት መታሰቢያ በዓል - በቤላ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

ሰኞ ሚያዝያ 20 - በለቡ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን (አዳም)

ረቡዕ ሚያዝያ 22 - ቅዱስ ዑራኤል - ቅዳሴ ቤት ጎፋ መብራት ሀይል

ሐሙስ ሚያዝያ 23 - ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍቱ

ሰኞ ሚያዝያ 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም በ 6 ኪሎ ምስካየ ኃዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብቻ

ሐሙስ ሚያዝያ 30 - ቅዱስ ማርቆስ - በዓለ እረፍቱ -በ6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


✝በስመ አብ ወ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

    ✝ መንፈሳዊ ጉዞ 🚌

♦️ ወደ ሚጣቅ አማኑኤል ገዳም

    ✝ መነሻ ቀን
መጋቢት 28

✝️ ደርሶ መልስ

መነሻ ሰዓት : 11:00


ዋጋ 800 ምግብ ውሀ እና ትራንስፖርትን ጨምሮ

➡️ ለመመዝገብ፦

☎️
0970423153

☎️
0929048787

❤️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤️ ወለ ወላዲቱ ድንግል
❤️ወለ መስቀሉ ክቡር

📍መነሻ ቦታ - ትሮፒካል መድኃኔዓለም ቤ/ክ
- አየር ጤና - መገናኛ - ጣፎ

‼️ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዳይለዮ


✝በስመ አብ ወ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

    ✝ መንፈሳዊ ጉዞ 🚌

♦️ ወደ ኩክ የለሽ ማርያም

    ✝ መነሻ ቀን መጋቢት 21

✝️ ደርሶ መልስ

ዋጋ 750 ምግብ ውሀ እና ትራንስፖርትን ጨምሮ


➡️ ለመመዝገብ፦

☎️ 0970423153

☎️ 0929048787

❤️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤️ ወለ ወላዲቱ ድንግል
❤️ወለ መስቀሉ ክቡር

📍መነሻ ቦታ - ትሮፒካል መድኃኔዓለም ቤ/ክ
- አየር ጤና - መገናኛ - ጣፎ

‼️ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዳይለዮ


✝በስመ አብ ወ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

ለ ደብረዘይት

    ✝ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ 🚌

♦️ ወደ ሳማ ሰንበት

    ✝ አዳር

    ✝ መነሻ ቅዳሜ መጋቢት 13

✝️ መመለሻ
እሁድ መጋቢት 14

ዋጋ 800 ምግብ ውሀ እና ትራንስፖርትን ጨምሮ


➡️ ለመመዝገብ፦

☎️ 0963004353

☎️ 0929048787

❤️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤️ ወለ ወላዲቱ ድንግል
❤️ወለ መስቀሉ ክቡር

📍መነሻ ቦታ - ትሮፒካል መድኃኔዓለም ቤ/ክ
- አየር ጤና

‼️ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዳይለዮ


✝በስመ አብ ወ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

 ደብረዘይት

    ✝ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ 🚌
    ✝ ደርሶ መልስ

    ✝ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ121፥1

    ✝ ወደ አጤ ዋሻ ማርያም
    ✝ እሁድ መጋቢት 14

➡️ ለበለጠ መረጃ፦
☎️ Wende 0929048787
☎️ Melat 0970423153

አዘጋጅ : ማኅበረ መድኃኔዓለም


❤️ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤️ ወለ ወላዲቱ ድንግል
❤️ወለ መስቀሉ ክቡር


✝በስመ አብ ወ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

    ❤እንኳን ለዓብይ ጾም አደረሰን❤️

    ✝ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ 🚌
    ✝ አዳር

    ✝ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ121፥1

    ✝ ወደ ምድረ ከብድ አቦ
    ✝መነሻ      መጋቢት 4 ሐሙስ
    ✝መመለሻ መጋቢት 5 ዓርብ

➡️ ለበለጠ መረጃ፦
☎️ Wende 0929048787
☎️ Melat 0970423153

አዘጋጅ : ማኅበረ መድኃኔዓለም


❤️ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤️ ወለ ወላዲቱ ድንግል
❤️ወለ መስቀሉ ክቡር


✝በስመ አብ ወ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

    ❤እንኳን ለዓብይ ጾም አደረሰን❤️

    ✝ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ 🚌
    ✝ አዳር

    ✝ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ121፥1

    ✝ ወደ ምድረ ከብድ አቦ
    ✝መነሻ      መጋቢት 4 ሐሙስ
    ✝መመለሻ መጋቢት 5 ዓርብ

➡️ ለበለጠ መረጃ፦
☎️ Wende 0929048787
☎️ Melat 0970423153

አዘጋጅ : ማኅበረ መድኃኔዓለም


❤️ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤️ ወለ ወላዲቱ ድንግል
❤️ወለ መስቀሉ ክቡር


✞ #የየካቲት_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ቅዳሜ የካቲት 8 - በዓለ ስምዖን አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት መታሰቢያ በዓል - በቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን

ማክሰኞ የካቲት 11 - አቡነ ሐራ ድንግል - በጣፎ

ረቡዕ የካቲት 12 - ቅዱስ ሚካኤል - ቅዳሴ ቤት በ 6 ኪሎ ማርቆስ ቤተክርስቲያን (አካፋው ሚካኤል)

እሁድ የካቲት 16 - ቅድስት ኪዳነምህረት የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት

ሐሙስ የካቲት 20 - ቅዱስ ፊልጶስ - ቅዳሴ ቤት- አጠና ተራ

እሁድ የካቲት 23 - ቅዱስ ጊዮርጊስ በአደዋ ጊዜ  የተራዳበትን ምክንያት በማረግ በገነተ ፅጌ (ፒያሳ)

ቅዳሜ የካቲት 29 - ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ - እረፍቷ - በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ፈረንሳይ ጉራራን አልፎ

እሁድ የካቲት 30 ቅዱስ ዮሀንስ - አንገቱ በሸክላ ዕቃ የተገኘችበት መታሰቢያ በዓል - በቀርሳ ሚካኤል ወ ቅዱስ ዮሀንስ ቤተክርስቲያን ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አለፍ ብሎ አዋሽ ጋር እዛው ቀርሳ ሚካኤል (ዮሐንስ ) የሚሄድ ታክሲ አለ

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

የተረሳ ወይም የቀረ ካለ አሳውቁን🙏🏽
🙏🏽
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።






የጥር ወር የንግስ በዓላት

ሐሙስ ጥር 1 -ቅዱስ እስጢፋኖስ - ልደቱ እና እረፍቱ

ቅዳሜ ጥር 3 -አባ ሊባኖስ - በዓለ እረፍታቸው በጣፎ ገብርኤል

እሁድ ጥር 4 -ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ - የተሰወረበት መታሰቢያ እለት - ትሮፒካል ቤተል መድኃኔዓለም ቤ/ክ እና- ዮሐንስ ማርያም ፒያሳ

ሰኞ ጥር 5 -አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ - በዓለ ልደታቸው ከታህሳስ 29 ወደ ጥር 5 የተዘዋወረ

ማክሰኞ ጥር 6 -ኢየሱስ - ግርዘቱ - በገዳመ ኢየሱስ እና በፈርንሳይ ገነተ ኢየሱስ
- ነብዩ ኤልያስ - በእሳት ሰረገላ ያረገበት
- ቅድስት አርሴማ - በዓለ ልደቷ

ረቡዕ ጥር 7 -ቅድስት ሥላሴ - የባቢሎን ግንብ ያፈረሱበት መታሰቢያ እለት

ቅዳሜ ጥር 10 - ከተራ

እሁድ ጥር 11 - በዓለ ጥምቀት

ሰኞ ጥር 12 - ቅዱስ ሚካኤል - ቃና ዘገሊላ

ማክሰኞ ጥር 13 - ቅዱስ እግዚአብሔር አብ

- ቅዱስ ሩፋኤል

ረቡዕ ጥር 14 - አቡነ አረጋዊ - ልደታቸው

ሐሙስ ጥር 15 - ቅዱስ ቂርቆስ - እረፍቱ

አርብ ጥር 16 - ቅድስት ኢየሉጣ - እረፍቷ

እሁድ ጥር 18 - ቅዱስ ጊዮርጊስ - ስባረ አፅሙ
- ቅድስት ፀበለ ማርያም

ረቡዕ ጥር 21 - እመቤታችን -እረፍቷ በዓለ አስተርእዮ

ሐሙስ ጥር 22 - ቅዱስ ዑራኤል - በዓለ ሲመቱ

ቅዳሜ ጥር 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት -በፀሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት (የተነሳበት) መታሰቢያ እለት

እሁድ ጥር 25 - ቅዱስ መርቆርዮስ - በስዕሉ ላይ አድሮ ታምር የሰራበት - በጎፋ መብራት ሀይል

ሰኞ ጥር 26 - አቡነ ሃብተ ማርያም - ቅዳሴ ቤት- አስኮ ቃሉ ተራራ

ማክሰኞ ጥር 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም - ቅዳሴ ቤት - በቀበና መድኃኔዓለም

ረቡዕ ጥር 28 - ቅዱስ አማኑኤል - 2 አሳ እና 5 እንጀራ አበርክቶ የመገበበት መታሰቢያ እለት

አርብ ጥር 30 - ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ - ቅዳሴ ቤት - በቤላ በጣፎ እና በምንጃር ሸንኮራ ዮሐንስ

ቸር ያገናኘን አሜን !!!


ፍቁረ_እግዚእ

ፍቁረ እግዚእዮሐንስ (፪)
ምስክሩ ነህ የኢየሱስ
ባማረው ቃልህ ልቤን አድስ

ጌታ የሚወደው ትሁት ወንጌላዊ
ምድራዊ አይደለ ክብሩ ሰማያዊ
በወንጌል የተካ የአሣውን መረብ
አደገ በፊቱ ተሞልቶ በጥበብ
#አዝ
ወንጌል ናት ሕይወቱ የተሰወረባት
በርሷ እየነደደ ለአለም ያበራባት
ተነጥፎ ያነባ በአምላኩ ፍቅር
ሳለው በውስጣችን የወንጌልን ክብር
#አዝ
የአይሁድ ጭካኔ ቢወራ ቢነገር
ከእራት ብቻ አይደለም ቀራንዮም ነበር
ፊቱን አላዞረም በዚያች የጭንቅ ቀን
ዮሐንስ አልቻለም በጌታው መጨከን
#አዝ
አምደ ቀራንዮ ከአስራ ሁለቱ አንዱ
አስራ አንዱ ሸሽተው በመንገድ ሲሄዱ
ዮሐንስ ነው ስሙ ጅራፍ ያላሸሸው
የክርስቶስ ፍቅር ውስጡን ያሸነፈው
#አዝ
ከአይሁድ ዛቻ ይልቅ ፍቅሩ ይሰማዋል
ገዳዮቹን ሊያድን ለሚሞተው አዝኗል
እንዲህ ያለ ፍቅር ለማንም የለውም
አለና ጻፈለት ብዕር ባይችለውም

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
።።።🙏🙏🙏።።




#በኤፍራታ_በጎል

በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ተወለደ ጌታ/2/

ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሳያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ/2/

አዝ____

ዓለምን በእፍኙ ጨብጦ አዳኙ
በከብቶቹ ግርግም አቀፈችው ማርያም/2/
መጡ ሰብዐ ሠገል ሊሠግዱ ለልዑል
ዕጣን ለክህነቱ ወርቁን ለመንግስቱ/2/

አዝ____

የመቅደሡ ናፍቆት በክንዱ መዘርጋት
ቤንሆር ተዋረደ መሲህ ተወለደ /2/
የጥሉ መንጦላይት ለይቶን ከገነት
ሕይወትን አገኘን ልደቱ አስታረቀን/2/

አዝ____

ምድር ተፈወሠች አዳኟን ስላየች
ሠውና መላዕክት ተቀኙ በአንድነት ዘመሩ በአንድነት
በሠላም አለቃ ኩነኔው ሊያበቃ
ስቃይ ሊመነገል ወለደችው ድንግል/2/

አዝ____

ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሣያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ/2/


@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


✞ በኤፍራታ ምድር

በኤፍራታ ምድር በቤተልሔም/2/
ጌታ ተወለደ ከድንግል ማርያም/2/
ብርሐናዊው ኮከብ ከሠማይ ዝቅ አለ/2/
ፍጥረትም ዘመረ ሀሌሉያ እያለ/2/
 
መንጋውን በለሊት ሲጠብቁ እረኞች
ከሰማይም ሠሙ ታላቅ የምስራች
በመላዕክት ግርማ ምድር ስታበራ
የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ

አዝ___

ድንገትም በሠማይ ሠራዊት ተገልጠው
በአንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋር ሆነው
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሠላምም በምድር በጎ ፈቃድ ለሠው

አዝ___

ቤተልሔም ሄደው ጌታን ተሣለሙት
ከእናቱ ጋር ሆነው በግርግም አገኙት
የመላዕክትን ዜማ እረኞች አወሩ
በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ

አዝ___

በመዝሙርም ቢሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ  ጌታ
ህፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈለጉት
እርሱ ነው ለሠዎች የድህነት ምልክት

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።




ናና አማኑኤል

ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
አዝ

የምሕረት አባት     አማኑኤል
የቸርነት ጌታ          ''
ፊትህ የተመላ        ''
ሁሌ በይቅርታ        ''
ካለው ፍቅር በላይ  ''
አባት ለአንድ ልጁ   ''
አምላክ ይወደናል      ''
አይጥለንም ከእጁ     ''
አዝ

መድኃኒቴ ልበል        አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ         ''
ቁስሌ ተፈውሷል         ''
በቁስልህ በሞትህ        ''
ስሸጥህ አቀፍከኝ         ''
ስወጋህ አይኔ በራ         ''
በፍቅርህ አወጣኽኝ       ''
ከዚያ ከመከራ               ''
አዝ

አንተ ከኔ ጋር ነህ          አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ                    ''
ድል አርገህልኛል             ''
የጭንቄን ተራራ               ''
በጉባኤ መሀል                ''
አፌ አንተን አወጀ             ''
የከበረ ደምህ                 ''
ነፍሴን ስለዋጀ                ''
አዝ

የድንግሏ ፍሬ                አማኑኤል
የበላቴናዋ                       ''
የቤቴ ምሰሶ                     ''
የነፍሴ ቤዛዋ                    ''
መሠረቴ አንተ ነህ              ''
ያሳደገኝ እጅህ                  ''
አተወኝም አንተ                  ''
ስለሆንኩኝ ልጅህ               ''

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አድርሱ
@mahberemedhaniyalem


✞ #ታህሳስ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ማክሰኞ ታህሳስ 1 - የነብዩ ኤልያስ ልደቱ - በእንጦጦ እና በጎፋ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 3 - ባዕታ ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን
                      -ቅዱስ ፋኑኤል - በዓለም ባንክ
      
                      -ዜና ማርቆስ - በጣፎ

እሁድ ታህሳስ 6 - ቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤቷ - የቅድስት አርሴማ ታቦት ባለበት

ማክሰኞ ታህሳስ 8 - አባ ኪሮስ ልደታቸው - አለምባንክ ጀሞ ተራራ መድኃኔዓለም ቤ/ክ - በጣፎ

ረቡዕ 9 - እስትንፋሰ ክርስቶስ ልደታቸው - በቦሌ ቡልቡላ ዋሻ ተክለሃይማኖት

አርብ 11 - ቅዱስ ያሬድ - ጎተራ አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት

ቅዳሜ ታህሳስ 12 - አባ ሳሙኤል እረፍታቸው - በአቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል ገዳም ፣ በቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል እና በሲኤሚሲ ሚካኤል

እሁድ ታህሳስ 13 - ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ - በሸጎሌ

ረቡዕ ታህሳስ 16 - ፍቅርተ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበለችበት እለት - በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ከፈርንሳይ ጉራራ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ጋር ባጃጅ እና ታክሲ አለ የአንቆርጫ

ቅዳሜ ታህሳስ 19 - ቅዱስ ገብርኤል - ሶስቱን ህፃናት ያዳነበት

ማክሰኞ ታህሳስ 22 - ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እደምትወልድ ያበሰረበት - በብስራተ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት - ልደታቸው

ሰኞ ታህሳስ 28 - ቅዱስ አማኑኤል - የልደቱ መታሰቢያ - በመሳለሚያ

ማክሰኞ ታህሳስ 29 - ባለወልድ - የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በዓል - በ4 ኪሎ ባለወልድ ቤተክርስቲያን - በለቡ መብራት አብርሃም ገዳም

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

         ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


ማክሰኞ ህዳር 24 - ሃያራቱ ካህናተ ሰማይ(ሱራፌል) - በቦሌ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን

                      - አቡነ ተክለሃይማኖት - 25ተኛ ሆነው የሥላሴ መንበር ያጠኑበት መታሰቢያ ዕለት

ረቡዕ ህዳር 25 - ቅዱስ መርቆሬዎስ - በዓለ እረፍቱ - በደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ - በጎፋ መብራት ሀይል ቅዱስ መርቆርዮስ ቤተክርስቲያን

- በካሳንቺስ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን

- በአዲሱ ገበያ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን

ሐሙስ ህዳር 26 - አቡነ ሃብተማርያም - በዓለ እረፍታቸው

እሁድ ህዳር 29 - አቡነ እጨጌ ዮሐንስ - በዓለ ልደታቸው - በወይራ ሰፈር

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞


ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን /2/
ውስተ አፍላገ ባቢሎን
ኅየ ነበርነ ወበከይነ
እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ኲሓቲሃ
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን /2/
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ

ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ለአምላካችሁ ቢያድናችሁ ከመከራ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ

የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ

ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን

መጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን ተስፋዬ
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem

Показано 20 последних публикаций.