የማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሦስት አብያተ ክርስቲያናትን አስገንብቶ አስመረቀ።
ማኀበረ ቅዱሳን በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት ጥቅምት 23፣24 እና 25 ቀን 2017 ዓ.ም ሦስት አብያተ ክርስቲያናትን አስገንብቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት አብያተ ክርስቲያናቱን ያስገነባው ባለድርሻ እና ተባባሪ አካላትን በማስተባበር ሲሆን የሦስቱ አብያተ ክርስቲያናት ሙሉ የግንባታ ወጪ 15 ሚልዮን 4 መቶ ሺህ ብር መሆኑ እና ወጪውንም በአሜሪካን ሀገር የሚገኙ የስብከተ ወንጌል ቤተሰቦች መሸፈናቸው ተገልጿል።
አብያተ ክርስቲያናቱ የተገነቡት ቀደም ባሉት ጊዜያት የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ተሰጥቷቸው አምነው ለተጠመቁ አዳዲስ አማንያን እና በቅርበት ቤተ ክርስቲያን ባለመኖሩ ከምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን እና ሥርዓተ አምልኮ ለመካፈል ሲቸገሩ ለነበሩ ምእመናን ነው ።
የተመረቁት ሦስቱ አብያተ ክርስቲያናት የወልባክ ቅዱስ ገብርኤል ፣ የጉዶ አሸከር አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የተንቤል ቅዱስ መርቆርዮስ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
የአብያተ ክርስቲያናቱ ቅዳሴ ቤት ተከብሮ አገልግሎት በጀመረበት ዕለት ቀደም ባሉት ጊዜያት የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ሲሰጣቸው የነበሩ 784 አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል ።
በምርቃት መርሐግብሩ የአሪ እና የደቡብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት ልዑካን ፣ የማኀበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ሌሎች ልዑካን እና የጂንካ ማእከል አባላት እንዲሁም የጽርሐ ጽዮን የሐዋርያት አንድነት የኑሮ ማኀበር ፣ የላፎቶ ደብረ ትጉኃን ሰ/ት/ቤት እና ጥሪ የተደረገላቸው የስብከተ ወንጌል ቤተሰቦች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።