በማኅበረ ቅዱሳን ዲላ ማእከል አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለነዳያን የምግብና የስጦታ መርሐ ግብር ተካሄደ።
በዲላ አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በተቋቋመው የበጎ አድራጎት ማኅበር ኮሚቴ ከተለያዩ ምእመናን የአልባሳትና የምግብ ግብዓቶችን በማሰባሰብ ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖቻችን የማዕድ ማጋራትና የአልባሳት ስጦታ አካሂዷል።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በተከናወነው በዚህ መርሐ ግብር ላይ የዲላ ወለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ደብር አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ሰላም ቀሲስ አምሳሉ "በጎ ኅሊና ይኑርህ " በሚል መሪ ቃል ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን የማኅበረ ቅዱሳን የዲላ ማእከል የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ርእሰ መምህር በሆኑት አቶ ታደለ በጌዴኦ ቋንቋ የመርሐ ግብሩን ዓላማ እና መልእክት አስተላልፈዋል።