የክረምት ድባቴ!
የክረምት ድባቴ በምን ይከሰታል?
ክረምት ከስነልቦና አንፃር ከስሜት መቀያየር ጋር ይያያዛል፡፡ ክረምት ማለት የፀሀይ ብርሀን የሚቀንስበት ዝናብ እና ቅዝቃዜ ያለበት ወቅት ስለሆነ ቀደም ካለው አየር ሁኔታው ሲቀየር ስሜታችንም አብሮ ሊቀያየር ይችላል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ክረምት ከመደበት፣ እንቅስቃሴ ከመቀነስ እና ደስተኛ ካለመሆን ጋር ይያያዛል፡፡ በክረምት የጭለማው መብዛት የድባቴው ስሜት እንዲመጣ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
ይህም የሚፈጠረው ጭንቅላታችን ስሜቶችን የሚያስተናግደው አዕምሯችን ውስጥ በሚፈጠር ኬሚካል ስለሆነ ነው፡፡
ጨለምለም ሲልም ’’ሜላቶኒን’’ የተባለ ሆርሞን በብዛት ይመረትና ድካም ድካም የማለት፣ እንቅልፍ የመፈለግ እና ለመንቀሳቀስ አለመፈለግ ይፈጠራል፡፡
የድባቴ ስሜቱ የሚመጣበት ዋናው ምክንያትም የፀሀይ ብርሀን በመቀነሱ እና ጨለማ በመጨመሩ ምክንያት ሆርሞኑ በአብዛኛው በመመረቱ ነው።
የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
- የምንሰራውን ስራ ለመስራት መቸገር
- መንቀሳቀስ አለመፈለግ
- ምንም ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆንን ሊያስከትል ይችላል፡፡
እንዴት መከላከል እንችላለን?
- አስተሳሰባችንን ማስተካከል
- ስራ ለመስራት መሞከር
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ማድረግ
- ያለንበት አካባቢ በበቂ ሁኔታ ብርሀን እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
በመጨረሻም በክረምት ወቅት የሚከሰት ድባቴን ለማስወገድ ስሜቱን በማሸነፍ ለመንቀሳቀስ መሞከር፡፡
ዶ/ር በላይ ሀጎስ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልቦና አስተማሪ እና ተባባሪ ፕሮፌሰር)
Via: ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@melkam_enaseb