Репост из: መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿
ክፍል አንድ
ዓይነ ጥላ እና ዛር ከማኅፀን ሲዋረሰን
/በስውር የተጎዳንበት መንገድ/
ወዳጆቼ ሆይ ስለ ዓይነ ጥላ አጋንንት በመግቢያችን ላይ በሰፊው ገለጥለጥ አድርን ቃኝተናል፡፡ የሚገርመኝ አብዛኞቻችን ስለ መንፈሱ ጠባይ እና ጥቃት በጥልቀት ሳታውቁ ‹‹መፍትሔው ምንድን ነው?›› እያላችሁ ትጠይቁኛላችሁ፡፡ የመንፈሱን ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃት እና የውግያ ስልት ስጣውቁ ነው በመንፈሳዊ ሞራል እና ኃይል ለመዋጋት፣ለመላቀቅ የምትጥሩት፡፡ ስለዚህ መፍትሔውን ላልነግራችሁ ስላልጀመርኩላችሁ ታግሳችሁ ትምህርቱን ተከታተሉ፡፡
ተወዳጆች ሆይ የዓይነ ጥላ አጋንንት ነገ ለሚያደርስብን የሕይወት ኪሳራ ዛሬ ነው የጥፋት መሠረት የሚጥለው፡፡ መንፈሱን አደገኛ የሚያደርገው ለሩቅ የተንኮል መንገዱ ዛሬ ነው መንቀሳቀስ የሚጀምረው፡፡ ከሕይወታችን ስር እና መሠረት በመነሳት ነው ነገአችንን ለማበላሸት የሚጥረው፡፡ ትላንት በሕይወታችን የሰረጸው አጋንንት ዛሬን ያለልፋት ማበላሸት ይቀለዋል፡፡
ዓይነ ጥላ ለሕይወታችን ከባድ የሚሆነው ከእናታችን ማህጸን ስለሚዋረሰን ነው፡፡ ይህ ማለት በጽንስ ወቅት በእናታችን ማህጸን ደም በሆንበት ሰዓት በስውር መጠናወት ይጀምራል፡፡ ይህን ስል አንዳንዶች ‹‹እንዴት በማህጸን በጽንስ ወቅት ሊይዘን ይችላል፣ዓይነ ጥላው በማህጸን እንዴት ይዋረሰናል?›› ሊሉ ይችላሉ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚብሔር ነብዩ ኤርምያስን ‹‹ከማኅፀን ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ›› ብሎታል፡፡ ልብ በሉ እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን በኤርምያስ ላይ በማሳደር በማኅፀን ሳለ ነው የባረከው፡፡ /ኤር 1÷5/ መጥምቁ ዮሐንስ ገና ሳይወለድ ቅዱስ ገብርኤል ለካህኑ ለዘካርያስ ‹‹ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል›› ብሎ አብስሮታል፡፡ /ሉቃ 1÷15/
ወዳጆቼ ርኩስ መንፈስ የቅዱስ መንፈስ ተቃራኒ ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱስ የሆነው መንፈስ ቅዱስ በማኅፀን ለቀድሶት እንደሚያድረው ሁሉ ርኩስ መንፈስም በማኅፀን በተቃራኑው ያድራል፡፡ ከማኅፀን የተመረጡት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ነብዩ ኤርምያስ እና መጥምቁ ዮሐንስ ሰማያዊ የአገልግሎት እና የቅድስና ሕይወት ጥሪው የደረሳቸው በማኅፀን ሳሉ በደምነታቸው ጊዜ ነው፡፡ ከማኅፀን ጀምረው መንፈስ ቅዱስን መሞላታቸው ሠርተው ያለፉት ሥራ ምስክራቸው ነው፡፡ ስለዚህ ዓይነ ጥላ ደግሞ ልክ እንደ ቅዱስ መንፈስ በማኅፀን ያድራል፡፡ በደምነታቸው ግዜ ተዋህዶ ከልጆቹ ጋር ይወለዳል፡፡ በተባረከ ማኅፀን የተጸነሰው ቅዱስ ዮሐንስ ገና በጽንስ ሳለ መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት ሁሉ ባልተባረከ ማኅፀን በሚጸነሰው ጽንስ ዓይነ ጥላ መዋረስ ይጀምራል፡፡
ቅዱስ ዳዊት ‹‹እነሆ በዓመጻ ተጸነስኩ፣እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ›› ብሏል፡፡ እኛም በዓመጻ ተጸንሰን በኃጢአት ከተወለድን ማለትም በዚህ መልክ ከተወለድን ዓይነ ጥላው በሕፃንነታችን ወቅት የማይጠናወተን ምንም ምክንያት የለም፡፡ /መዝ 51÷5/
ወዳጆቼ ዓይነ ጥላ እንኳን በማኅፀን ያለ ጽንስ ላይ ማደር ቀርቶ እንደ ሾተላይ ገና ደም የሆነ ጽንስን በማጨናገፍ ጽንስ እንዲቋረጥ ያደርጋል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ላይ ደግሞ በተደጋጋሚ ጽንሳቸውን በማስወረድ ልጅ አልባ ያደርጋል፡፡ ሌሎቹን ደግሞ ባረገዙ ቁጥር ጽንሱን በደም እየመታ ማኅፀናቸው ልጅ እንዳይዝ ያደርጋል፡፡ በዚህ ተንኮሉ በተደጋጋሚ ማኅፀናቸውን ሲጠረጉ ለሌላ ችግር ይዳጋቸውና እስከመጨረሻው ያለ ልጅ ሊያስቀራቸው ይችላል፡፡ ለዚህ መፍትሔው ጸሎት ማስደረግ፣ለሚወዱት ታቦት መሳል፣ጸበል መጠመቅና መጠጣት፣ቅባዕ ቅዱስ መቀባት፣ማስወገዝ፣ የዓይነ ጥላውን ስውር ደባና ተንኮል ያርቅልናል፡፡
የተወለዱት ልጆች በሚያድጉበት ጊዜ ዓይነ ጥላው በራሱ ባሕርይ እየቀረጻቸው፣እያጣመማቸው አብሮ ማደግ ይጀምራል፡፡ ልጆቹም ቅድስና እንዲርቃቸው፣መልካም ባሕርይ እንዳይኖራቸው ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው የነገ የተስፋ ሕይወታቸውን ለማጨለም ገና በጠዋቱ ተክለ ሰብዕናቸውን እያራቀ፣እራሱን በተንኮል እያራቀቀ በውስጣቸው አድብቶ ይቀመጣል፡፡ ትንሽ ከፍ ሲሉ የመታዘዝ ሳይሆን የእንቢተኝነትን ጠባይ ይዘው እንዲያድጉ ያደርጋል፡፡ የሚነገራቸውን የማይሰሙ፣ተዉ የተባሉትን አድርጉ የተባሉ ይመስል በእልህ መንፈስ አብሮ ያድጋል፡፡
ዓይነ ጥላው ከማኅፀን ጀምሮ ስላደረባቸው ንቃተ ሕሊናቸውን በመስለብ እንዲፈዙ እንዲደነዝዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ደስተኛ እና ሳቂታ ሳይሆን አልቃሻ እና ሆደ በሻ ልጅ ያደርጋቸዋል፡፡ አንድ ነገር ሲነገራቸው ወይም ሲቆጥዋቸው ደንግጦ ከመስማት ይልቅ አፍጦ የሚሟገትና እንቢኝ እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ መልኩ ዓይነ ጥላው በስውር የራሱን የክፋት እና የጥመት ባሕርይ እያዋረሳቸው በሽምቅ በመደበቅ አብሮ መኖር ይጀምራል፡፡
ወዳጆቼ እኛ ስንባረክ ነው የተባረከ ልጅ የምንወልደው፡፡ እኛ በመንፈሳዊ በረከት በእግዚአብሔር ሳንባረክ ኖረን የተባረኩና የተቀደሱ በተለይም ከአጋንት የተንኮል እይታ የተለዩ ልጆች ለመውለድ እንቸገራለን፡፡ የእኛ የመባረክ ጸጋ ነው ለልጆቻችን የሚተርፈው፡፡ ይህ ባልሆነበት መስፈርት ‹‹አይ አጋንንት ከማኅፀን ጀምሮ አይቆራኛቸውም›› ብንልም የዘራነውን በተዘዋዋሪ እያጨድን ነው፡፡
ወዳጆቼ የዛር መንፈስም የሕይወት ውግያው ከዓይነ ጥላ የሚያንስ ሳይሆን የሚብስ የማኅፀን ተዋራሽ አጋንንት ነው፡፡ እናት አባቶቻችን በተለያየ ምክንያት ዛር አንጋሽ ቤት ሄደው ማምለክ፣መንበርከክ ሲጀምሩ አጋንንቱ እነሱን መዋረስ ይጀምራል፡፡ ሳይመጣባቸው የሄዱበት የዛር አጋንንት በጽንስ ወቅት መጠናወት ይጀምራል፡፡ እግዚአብሔርን ትተን፣የዛር አጋንንትን አምልከን መኖር ስንጀምር ሙሉ ሕይወታችን ለአጋንንቱ ተላልፎ ይሰጣል፡፡
የእግዚአብሔር ጸጋ በሌለበት ሕይወትና ማኅፀን ዓይነ ጥላው ዛሩ ቢያድርበት ምን ይደንቃል? እንዴትስ አጋንንት በፅንስ ወቅት በማኅፀን ይጠናወታል ብሎ መከራከር ይቻላል? የሚከራከሩትን ይሁዳ በመልእክቱ ‹‹በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ›› በማለት ይወቅሳቸዋል፡፡ /ይሁ 1÷18/
የሚገርመው የዛር አጋንንት እንኳን በማኅፀን ያለን ፅንስ ቀርቶ በስም እንጂ በአካል የማናውቃቸው ቅድመ አያቶቻች የሚያመልኩት የሚገብሩለት ከሆነ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ዘራችንን በመዋረስ ቤተኛ ሆኖ ይኖራል፡፡ በተለይ ያስለመዱበትን ግብር ሲተዉ ልጆችን በተለያየ ነገር ማሰቃየት ይጀምራል፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ ‹‹በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ለሚወዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፣አታምልካቸውም›› በማለት ቤተሰቦቻችን ባመጡት ስህተት ለእኛ የመከራ ሕይወት እንደሚተርፍ እና ቤተሰቦቻችን እግዚአብሔርን በማምለክና ትዕዛዙን በመፈጸም የሺህ ትውልድ በረከት እና ምሕረት እንደሚያገኙና ለእኛም እንደሚተርፉ ነው የሚያስረዳን፡፡ /ዘዳ 5÷ 9-10/
የዛር አጋንንት ከወለድናቸው ልጆች ‹‹ደመ ግቡ›› የሚለው አለ፡፡ ይህ ማለት አጋንንቱ ለተንኮሉና ለውግያ፣ቤተሰብን ለማሰቃየት የሚጠቀምበት አንድ ልጅ ላይ ይሰፍራል፡፡ ይህ ልጅ በመንፈሳዊ ሕይወቱ አጋንንቱን የሚዋጋ፣ጸሎቱም ለቤተሰቡ የሚተርፍ ስለሚሆን አጋንንቱ መጥፊያውን ገና በጠዋቱ ማጥፋት ይጀምራል፡፡ በቤተሰባቸው ምክንያት በዛር አጋንንት የሚሰቃዩት ልጆች አጋንንቱ ወድዋቸው ሳይሆን ነገን ፈርቷቸው ነው ለመከራ የሚዳርጋቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ል