#1| በአንድ ወቅት ለህዝብ ተደጋግመው ተነግረው የነበሩ፣ አሁን ላይ ግን ደብዛቸው ከጠፉ 10 ጉዳዮች መሀል
(መሠረት ሚድያ)- 1ኛ: "የአፍሪካ ዋካንዳ በባህር ዳር ሊገነባ ነው"
በአንደኛ ደረጃ የምንመለከተው በባህር ዳር አካባቢ ይገነባል ተብሎ በስፋት ተነግሮለት ስለነበረው የአፍሪካ ዋካንዳ ፕሮጀክት ነው።
የዛሬ ስድስት አመት ገደማ ዋካንዳን በባህር ዳር እገነባለሁ ብሎ የተነሳ ሀብ ሲቲ ላይቭ የተባለ አንድ ድርጅት ነበር። ይህ ድርጅት አለኝ የሚለው ምዝገባም ሆነ የፋይናንስ ምንጭ ከመጀመርያው ጀምሮ አጠራጣሪ ነበር።
ታድያ ይህ ምናባዊውን ዋካንዳ በአማራ ክልል ጭስ አባይ አካባቢ ዕውን ያደርጋል የተባለው ፕሮጀክት የት ደረሰ?
‘ምንጩ’ ወይም The Source በሚል ስያሜ በጭስ አባይ ፏፏቴ አቅራቢያ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መንደር ሊገነባ እንደነበር በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በወቅቱ ሲዘገብ ነበር፡፡
ይገነባል ተብሎ የታሰበው የቴክኖሎጂ መንደር ባለቤት ሀብ ሲቲ ላይቭ የተባለ የአሜሪካ ድርጅት ሲሆን፤ እ.አ.አ በ2018 በሆሊውድ ፊልም መንደር ተሠርቶ ለዕይታ የበቃው የ‹‹ብላክ ፓንተር›› ፊልም ምናባዊ ከተማ ዋካንዳን መሠረት አድርጎ እንደሚገነባ ነበር በወቅቱ የተገለጸው፡፡
ሀብ ሲቲ ላይቭ የተባለው ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሚካል ካሚል ከዋልታ ቲቪ ጋር በወቅቱ በነበራቸው ቆይታ የፕሮጀክቱ ስያሜ ‘ምንጩ’ እንደሚባልና ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር፣ ኢትዮጵያንም በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሻለ ደረጃ እንደሚያሰጣት ነበር የተናገሩት፡፡
ፕሮጀክቱ እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅና ሦስት ቢሊዮን ዶላር በወቅቱ ተመድቦ እንደነበርም መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ቀሪው በጀት በዋናነት ከአሜሪካ ባንኮች እንደሚገኝም ሥራ አስኪያጁ ጠቁመው ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ፕሮጀክቱን እና ተያያዥ ሥራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸውንም በቃለ መጠይቁ አስረድተው ነበር፡፡
ባሕር ዳር የጣና ሐይቅ እና የጭስ የአባይ መገኛ ውብ ከተማ በመሆኗ ተመራጭ አድርጓታል፤ ከታሪክ አንፃርም የዓለም ትልቁ ስልጣኔ መነሻ ከዚህ አካባቢ ነው ተብሎ ስለሚታመን ምናባዊ ዋካንዳ የቴክኖሎጂ ከተማን ለመገንባት አካባቢውን እንደመረጡት ሥራ አስኪያጁ እንደመረጡት መናገራቸውም ይታወሳል።
ጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲስብ አድርጎት የነበረው ደግሞ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ከተማን የመስራት እቅዱን አስመልክቶ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከባለድርሻዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ አብዛኞቹ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የዘገባ ሽፋን መስጠታቸው ነበር፡፡
ሀብ ሲቲ ላይቭ የተባለው ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሚካል ካሚል እውነተኛውን የዋካንዳ ፕሮጀክት በጭስ ዓባይ ፏፏቴ አቅራቢያ ገንብቶ ለመጨረስ ከስምንት እስከ አስር ዓመታት እንደሚወስድ፣ ፕሮጀክቱንም አጠናቅቀው ዕውን እንደሚደርጉት ገልጸው ነበር፡፡
‹‹ሀሳባችን በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ለምንጠይቀው ሁሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን ነው›› ብለውም ነበር፡፡ ይሁንና ከጥቂት ወራት በኃላ ‹ዕውን ይሆናል የተባለው ምናባዊው ዋካንዳ› የት ደረሰ? በማለት የወቅቱ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ሲጠየቁ “የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የፕሮጀክቱ እውን መሆን ለክልሉ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ተገቢውን ድጋፍ እንድናደርግ ደብዳቤ ፅፎልን እንጅ በኛ በኩል ስለ ፕሮጀክቱ የምናውቀው ነገር አልነበረም” ብለዋል፡፡
በተፃፈለት የድጋፍ ደብዳቤ መሠረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በንድፈ ሀሳቡ ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ማድረጉንም አስታውሰው ውይይቱም ፕሮጀክቱ ለሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር በሚኖረው ፋይዳ ዙሪያ እንደነበር እና አሁን በምን ደረጃ ላይ እንዳለ እውቅና እንደሌላቸው ተናግረው ነበር፡፡
ከዛ ወዲህ የሀብ ሲቲ ላይቭ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደማያውቁ የታወቀ ሲሆን ያ ብዙ የተወራለት የዋካንዳ ፕሮጀክትም የውሀ ሽታ ሆኖ ቀርቷል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia