የመንግስት ሚድያዎች የትናንቱን የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ዜና እንዳይሰሩ እንደተነገራቸው ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- አሜሪካ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ለተከሰተው ድርቅ እና የምግብ እጥረት ምግብ እየተላከ መሆኑን አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል በትናንትናው እለት ያሳወቀችበትን መረጃ የመንግስት ሚድያዎች እንዳይዘግቡ እንደተነገራቸው ታውቋል።
በሁለት የተለያዩ የመንግስት ሚድያዎች ውስጥ የሚሰሩ የሚድያ ባለሙያዎች ስማችን አይጠቀስ ብለው ለመሠረት ሚድያ እንደተናገሩት "ከላይ በመጣ ትእዛዝ" የአሜሪካ ድጋፍ ማድረግ እንዳይዘገብ ትእዛዝ ተላልፏል።
"ዜናውን መስራት ጀምረን ነበር፣ በኤዲተራችን በኩል ግን ተዉት ተብለናል" ያለው አንደኛው ምንጫችን ጉዳዩ "የመንግስትን የሰብል ምርት ስኬት ያኮስሳል" ተብሎ እንደተነገረው ገልጿል።
ሌላኛው ጋዜጠኛ ደግሞ "ጉዳዩ ለሀገር ገፅታ አንፃር ይቅር" እንደተባለ ተናግሯል።
የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው በወረዳው ድርቅ እንደተከሰተ ከሰሞኑ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ላይ ክትትል አድርጌያለሁ ብሏል።
"የኢትዮጵያ ህዝብን ለመደገፍ አጋሮቻችን ምግብ እና አልሚ ምግቦችን ወደተጠቁት ስፍራዎች እየላኩ ነው" ያለው ኤምባሲው ሁኔታውን በቀጣይም በመከታተል ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ አስታውቋል።
መሠረት ሚድያን ጨምሮ አንዳንድ ሚድያዎች ከሰሞኑ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ስለተከሰተው ድርቅ ሲዘግቡ ቆይተዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው እና በርሀብ እጅግ የተጎዱ ህፃናት ምስልም በማህበራዊ ሲዘዋወር ነበር።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia