#አማኑኤል_ይቅር_ባይነዉ
አማኑኤል ይቅር ባይነዉ ፍቅር
ምህረት ከቦት በሰማያት ሚኖር
እያመመው አባቱን እየጠራ
አይቻለው ለሚገድሉት ሲራራ
#አዝ
አይምረኝም አትበሉ ጨካኝ ንጉስ አይደለም
ደሙ ብቻ ያነፃናል ከሀጢአታችን ዘለዓለም
እንደሞላ ጅረት ፈሶ ምድራችንን አጥለቅልቋል
የእሱ ምህረት ሀይል ሆኖት ስንቱ ከሞት አፈትልኳል
#አዝ
የጨለመው እየነጋ የተሻለ ቀን ይመጣል
በፍቅሩ ጦር ሳይወጋ ማን ከሞት እሮጦ ያመልጣል
ያን ክፉ ቀንበድል አልፈን እንደ ዋርካ የሰፋነው
ነውርን ሁሉ በሚከድን በሞተልን በኢየሱስ ነው
#አዝ
የእሱን ፍቅር የሚያሸንፍ አንዳች ሀጢአት የለምና
ወደጌታ ለመመለስ አንዳች እንኳን እዳትፈራ
ሀገራችን በሰማያት ነው የሚወድቅ የለም የሚረሳ
ሰማያትን እንወርሳለን ከቤቱ ደም የተነሳ
#አዝ
ወዳጅ አለን አንድ ብቻ በሰማያት የምድርም
ስሙ ኢየሱስ የተባለ ሰውን ሁሉ የሚያፈቅር
ከመቃብር በላይ ሆኖ ፍቅሩ አለምን አስገረመ
እሄን ሁሉ ጎስቋላ ሰው በትክሻው ተሸከመ
ዘማሪ ዕዝራ ኃ/ሚካኤል
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊