የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ ረፍት መንሳቱና መፈናፈኛ ማሳጣቱ ብሎም በደፈጣ ተዳክሞ ሲገኝ በመደበኛ ዉጊያ መደምሰስና መማረኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
ዞብል አምባ ክፍለጦር ካለው ሰራዊት 1ኛ ሻለቃ እና በፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ልዩ ዘመቻ ዛሬ ህዳር 13/2017 ዓ.ም በጋራ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ጥቃቱ ከቆቦ ከተማ በምዕራብ ተኩለሽ መስመር ከ4-5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተፈፀመ ሲሆን በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ዉጊያ ወደ መደበኛ አድጎ ጠላት በርካታ ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ ወደ ቆቦ ከተማ ፈርጥጧል:: የደፈጣ ጥቃቶቹ ከከተሞች በቅርብ ርቀት ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ጠላትም በበርካታ ጥቃቶች ተሰላችቶ ወደ ፋኖ እየኮበለለ ይገኛል::
ራያ ቆቦ ተኩለሽ የገባው ጠላትም መሉ ለሙሉ ከበባ ዉስጥ ገብቶ ረሽንና ተጨማሪ የሰው ሃይል እንዳይደርሰው ሆኖ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ሲል የዞብል አምባ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሃብተማርያም መንበሩ ገልፇል::
በቀጣይም የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የዞብል አምባ ክፍለጦር አመራሮች እና የልዩ ዘመቻ አዛዡ ፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) ገልፀዋል::
ህዳር 13/2017 ዓ.ም
ድል አለማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
ንሥር ብሮድካስት መረጃ
አርብ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም
=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! ትግላችን በጋራ!
ዮቱብ፣https://youtube.com/@nibcnewsethiopia?si=oM5AASTB3fSDK53F