መውደዴን ሳታውቂው እኔ የምወድሽ የምወድሽ ማፍቀሬን ሳታውቂው እኔ የማፈቅርሽ የማፈቅርሽ አንድ ቀን አገኝሻለው ብዬ አለው ተስፋ ጥዬ እሄዳለው እንጂ አንቺን ተከትዬ ባደርሽበት ላድር በዋልሽበት ውዬ በአካል በመንፈሴ መች እለይሻለው አንቺ ግን አታውቂም ሁሌ አብሬሽ አለው አንድ ቀን መቼም ቢሆን አንድ ቀን ሳለው በህይወቴ አንድ ቀን ተሳክቶልኝ አንድ ቀን ምኞት ፍላጎቴ የኔ ሆነሽ የኔ የፍቅር እመቤቴ በሰመረ ስለቴ ስለቴ ስለቴ ያውና እዛ ቁጭ ብለሽ ደምቀሽ ትታያለሽ ደሞ እንዴት ታምሪያለሽ አንቺማ ምን አለብሽ የኔን ልብ እንጠልጥለሽ ይዘሽ ትዞሪያለሽ እኔ ግን አንቺን ብያለው ተከትዬሽ መጥቻለው ደሞ ነገም በሄድሽበት እሄዳለው
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏