#የፍቅሩ_ምክንያት
እግዚአብሔር ሰውን ያፈቅራል ስንባል ሰምተናል። ልክ ነው በተግባርም አይተነዋል። ይሁን እንጂ በምን ምክንያት ነው ያፈቀረን? ምን ምክንያት ሆኖ ነው የወደደን? እስኪ ወንድሜ ለተወሰነ ሰከንድ ይህን ጥያቄ እራስህን ጠይቅ አንቺም እህቴ እራስሽን ጠይቂ። ...... ለምን ወደድከኝ...በምን ምክንያት ነው ያፈቀርከኝ
እናንተ በእግዚአብሔር ስለመወደዳችሁ ምክንያት ሊሆን የሚችል ከእናንተ ምን በጎ ነገር አገኛችሁ። እግዚአብሔርማ ከዚህ ነገሬ የተነሳ ሊወደኝ ይገባል የምትሉት አንዳች ምክንያት አገኛችሁን? አዎ አገኝቻለሁ ካላችሁ ዋሳችሁ።
እግዚአብሔር እኛን የወደደን በእኛ ዘንድ ለእርሱ ባህሪ ተስማሚ የሆነ ነገር ተገኝቶብን ሳይሆን እንዲሁ ነው። የወደደን እንዲሁ ነው። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን #እንዲሁ ወዶአልና።”(ዮሐንስ 3፥16)
እግዚአብሔር እኔን በመውደዱ ውስጥ እኔ ያዋጣሁት ነገር የለም ማለት እጅግ አስተዋይነት ነው። ለእርሱ ፍቅር እኛ የምናዋጣው ነገር ቢኖር ኖሮ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ መዋጮ ልክ ከፍ እና ዝቅ ይል ነበር። እናም እግዚአብሔር ከራሱ በሆነ መውደድ የሚወደን አምላካችን ነው።
አንዳንዴ ስራዎቻችን መጥፎ ሲሆኑ እግዚአብሔር የጠላን ይመስለናል። ወይም ድርጊታችን ልክ ሳይሆን ሲቀር የእግዚአብሔር ፍቅሩ የሚቀዘቅዝ ይመስለናል። አልያም በጎ ስንሰራ፣ ሰው ስንረዳ፣ ሰው ስናገዝ፣ እግዚአብሔር የሚወደውን ነገር ስናደርግ፣ መንፈሳዊ ህይወታችን ያመረ ሲሆን የእግዚአብሔርን የፍቅሩ ግለት የሚጨመርን ይመስለናል።
የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ምክንያት ስላልመጣ በእኛ ምከንያት አይጸናም የሚጸናው እርሱ እግዚአብሔር እራሱ ጽኑ ስለሆነ ነው። አትሳሳቱ እግዚአብሔር የሚወደኝ እንዲህ ሳደርግ ነው አትበሉ። እግዚአብሔር እኛ ጠላቶቹ ሆነን ሳለ የፍቅሩን ሃያልነት ገለጠልን እንጂ ወዳጁ ስለነበርን አይደለም። “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”( ሮሜ 5፥8)
የእግዚአብሔር ፍቅር እንደ ሰዎች ፍቅር መልክ እና ሁኔታ እያየ አይጎርፍም ይልቁንም ጠላት የሆነውን ያቀርባል እንጂ። እግዚአብሔር በደለኞቹን እኛን ማዳኑ የመውደዱ ማብራሪያ ነው ይህም ከእኛ በሆነ በጎ ምግባር ላይ የተመሰረተ አይደለም። “ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥” (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥9)
ፍቅር ምክነያት ይፈልጋል የምንለው ፍቅሩ ሰዋዊ ሲሆን ነው ምከንያቱም የሰው ልጅ ስለቀረብነው የሚያፈቅር ስለራቅነው ደግሞ የሚረሳ ወረተኛ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔራዊ ፍቅር ግን ከእራሱ ከእግዚአብሔር የሚመነጭ የፍቅር ውሃ ነውና ሁሉን ያረሰርሳል። የእግዚአብሔር ፍቅር ምክንያት አልባነት ከተሰወረበት ሰው ይልቅ አላዋቂ ሰው አይኖርም።
ስናለማም ስናጠፋም
ፍቅሩ ግን ከቶ አይጠፋም
ስናበጅም ሳናበጅም
ፍቅሩ ጭራሽ አያረጀም
ስናደርግም ሳናደርግም
ፍቅሩ ግን አይዋዥቅም
ሰንቀርብም ስንርቅም
ፍቅሩ ግን ፈቅ አይልም
ስንጨልምም ስንበራ
የእርሱ ፍቅር ያው ጠንካራ
ስንሰጥም ሳንሰጥም
የእርሱ ፍቅር ሰው አይመርጥም
ስንሄድም ስንመጣም
ፍቅሩ ላይ ለውጥ አይመጣም
ስንስቅም ስንከፋም
ድርጊታችን የሱን ፍቅር አያፋፋም
በሁኔታችን ከፍ አይልም
ወይም ደግሞ ዝቅ አይልም
ሁሌም ጽኑ የእርሱ ፍቅር
ለዘላለም ለዘወትር
ያለ ምክንያት ስለሚፈሰው ፍቅርህ አማኑኤል ሆይ ተመስገን።
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ሚያዝያ 21 2015 ዓ.ም ተጻፈ
@orthodox_new_mezmur