#መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
«ተንሥዕ ንሣዕ ዓራተከ ወሑር፤ /ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ» /ዮሐ.፭፥፰/5፥8/ የዐቢይ ፆም አራተኛው ሳምንት መጻጉዕ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡
«ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ» ያለው ሠላሳ ስምንት ዓመት በአልጋ ላይ ሰውነቱ ልምሾ ሆኖ ታሞ የነበረውን ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው የህመሙ ዘመን ስለረዘመ ዘመዶቹ ሁሉ እየሰለቹ የማስታመሙን ነገር ችላ ብለው ጥለውት ሄደዋል፡፡ ህመምተኛው ዘመዶቹ በተውት ቦታ በቤተሳይዳ መጠመቂያ ፀበል አጠገብ ተኝቶ ነበር፡፡
ጌታችንም ብዙ ዘመን ተኝቶ እንደኖረ አውቆ «ልትድን ትወዳለህን?» አለው፡፡ እርሱም መጠቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም በማለት መልስ ሰጠ፡፡ ፀበሉን አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ድንገት ሲያናውፀው ቀድሞ ወደ ፀበሉ የገባ ይድን ስለነበር፤ መልሱ የሚያመለክተው ከሁሉ ቀድሞ እኔን ተሸክሞ ወደ ፀበል ሊያስገባኝ የሚችል ዘመድ ስለሌለኝ እንዴት እድናለሁ ነበር፡፡
ነገር ግን ጌታችን የሁሉም መድኃኒት በመሆኑ ወዲያው «ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ» ሲለው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሄደ፡፡ አይሁድ ማን አልጋውን ተሸክሞ እንዲሄድ እንደፈቀደለት ቢጠይቁት ለጊዜው ጌታችንን ባያውቀውም፤ በሌላ ጊዜ ጌታችን ሲያገኘው «እነሆ! ድነሃል ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ዕወቅ» በአለው ጊዜ ይህ ሰው ከሰላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኝነት በኋላ ከተጣበቀበት አልጋ ያላቀቀውን አምላክ ረስቶ ለአይሁድ ሊጠቁመው ሮጦ ሄደ፡፡ እንዳሰበውም ነገራቸው እነሱም ሊያሳድዱት ሊገሉትም ይሹ ነበር፡፡
ምንባባት መልዕክታት
(ገላ. 5÷1-ፍጻሜ ምዕ.) እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትኑሩ፡፡ እነሆ÷እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፤ “ብትገዘሩም በክርስቶስ ዘንድ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡” ......
(ያዕ.5÷14- ፍጻሜ ምዕ.) ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉ ቀሳውስትን ይጥራና ይጸልዩለት፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቅቡት፡፡ .......
ግብረ ሐዋርያት
(የሐዋ.3÷1-11) ጴጥሮስና ዮሐንስም በዘጠኝ ሰዓት ለጸሎት በአንድነት ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፡፡ ከእናቱ ማኅፀንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ ሁል ጊዜ እየተሸከሙ መልካም በሚልዋት በመቅደስ ደጃፍ ያስቀምጡት ነበር፡፡(ተጨማሪ ያንብቡ)
ምስባክ
(መዝ.40÷3) “እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፡፡ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢ ሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ
ትርጉም፦ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል፡፡
ወንጌል
(ዮሐ. 5÷1-24) ከዚህም በኋላ በአይሁድ በዓል እንዲህ ሆነ፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ መጠመቂያ ነበረች፤ ስምዋንም በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል፤ አምስት እርከኖችም ነበሩአት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)
ቅዳሴ፡- ቅዳሴ ዘእግዚእነ
❖እግዚአብሔር አምላካችን መዋዕለ ጾሙን በሰላም እንዳስጀመረን ሱባኤውን በሰላም አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም እንዲያደርሰን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን። አሜን።❖
👉 #ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot