Репост из: Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
ጠያቂው ተጠየቅ እንጂ…!
"…ክርስቶስ ማነው…? በሚል 303 ጥያቄዎች አሉኝ ብሎ እሱ በማያምንበት ለእኔ ግን ጌታዬ አምላኬና መድኃኒቴ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጥያቄ አቅርቧል። በመጽሐፍ መልክም አሳትሟል። መልካም መብቱ ነው። አሕመዲን ጀበል በጌታ ላይ ተሳልቋል፣ በምስጢረ ሥላሴ ላይ አሹፏል፣ ቀልዷል ብለን ሰልፍ አልወጣንም። ይገደልም አላልንም።
"…አሕመዲን ጀበል በኢየሱስ ክርስቶስ ስለማያምን የፈለገውን የመጻፍ መብት አለው ከተባለ እፎይም ሆነ እኔ ስለማላምንበት ስለ መሀመድ ብጽፍ ለምን ትናደዳለህ? አንተ የእኔን በመናቅህ ዝም እንዳልኩህ እኔም የአንተን ስንቅ ዝም ማለት ነው እኮ ያለብህ። አንተ የእኔን ድንበር አልፈህ ለማዋረድ ስትሞክር እኔ በድንበሬ ላይ ቆሜ የአንተን ባዋርድ ለምንድነው ጎረቤት ሁላ እስኪረበሽ የምትንጫጫው። አንተ "ለነቢይህ" ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውዴታ አለኝ ካልክ እኔ ለአምላኬና ለመድኃኒቴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ዓይነት ፍቅር፣ መስዋዕትነት የማልከፍል ይመስልሃል?
"…ንጽጽር ብለህ ያለ አቅምህ መጽሐፍ ቅዱስ ትንተና የጀመርከው አንተው ራስህ ነህ። አንተ የማታውቀውን መጽሐፍ ቅዱስ ገልጠህ ስትዳክር ዝም ብለን ቆይተን፣ መልስም ከዚያው ከመጽሐፍ ቅዱስ ስንሰጥህ ከርመን፣ አይ ቆይ እስኪ ለምን ደግሞ ከቁርዓኑና ከሐዲሱ መልስ አንጠይቃቸውም ብለን ስንነሣ ቆንጨራ ይዞ መፎከር ምን የሚሉት ነው? ወይ አስቀድሞ አለመፎከር፣ አቅምን ዐውቆ መኖርም ጥሩ ነው። ግጠመኝ ካልክ በኋላ አንተ በእኔ መጽሐፍ ቅዱስ ልትሞግተኝ ስትመጣ፣ እኔ ደግሞ በአንተው ቁርዓን ልሞግትህ ስነሣ የምን መነጫነጭ ነው?
"…በመስታወት ቤት የሚኖር ሰው የድንጋይ ውርወራ ጠብ ውስጥ ፈጽሞ አይገባም። ባለጊዜ ነን ተብሎ እንደ ሕጻን በልቅሶ፣ በጩኸት ፍላጎትን ለማሳካት መሯሯጥ ያስገምታል።
• እፎይ…!