የእግዚአብሔር ባህርይ
የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህርይ በሰው አእምሮ የማይመረመርና የማይወሰን ረቂቅ ነው። በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር መመራመርም ሆነ ለሌላውም ማስረዳት ይቻላል። የመለኮትን ባህርይ ግን ሙሉ በሙሉ ተመራምሮ የሚያውቅም ሆነ የሚያስረዳ ማንም የለም። ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት በገለጹልን መሠረት እንደሚከተለው ለመግለጽ እንሞክራለን።
እግዚአብሔር መንፈስ (ረቂቅ) ነው እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእምነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሐ 4 ፥ 24። በማለት ጌታችን እንደተናገረ እግዚአብሔርን ስናምን በዓይናችን አይተን ፣ በእጃችን ዳስሰን አረጋግጠን ሳይሆን በመለኮታዊ ባህርዩ በሥጋ ዓይን የማይታይ አምላክ መሆኑን አምነን በመቀበል ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው ስንልም። በእኛ አእምሮ የማይታወቅ ፤ መጠን የማይሰጠው ፤ በላብራቶሪ ምርመራ የማይደረስበት ፤ከምርምር ውጭ የሆነ አምላክ ማለታችን ነው። እግዚአብሔር የፈጠረው ነፋስን እንኳን ከረቂቅነቱ የተነሳ በዓይናችን ማየት እንደማንችል ሁሉ። ዮሐ 3 ፥ 8። ረቂቃን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ መለኮታዊ ባህርዩ ሊመረመርና ሊገመት የማይችል ረቂቅ ነው።
እግዚአብሔር በሁሉም ሙሉ ነው
ሰው በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መገኘት የማይችል በተወሰነ ቦታ ብቻ የሚወሰን ነው። ኤር 23 ፥ 23። እግዚአብሔር ግን ፍጡር የማይወስነው ፣ በሁሉም ቦታ የሚገኝ ፣ (ምሉዕ በኩለሄ የሆነ) አምላክ ነው። እግዚአብሔር በዓለም ሙሉ ነው ሲባል በዓለም ውስጥ ብቻ ተወስኖ ይኖራል ማለት ሳይሆን ዓለምን በውስጡ ይወስናል ማለት ነው። በኢሳ 8 ፥ 1። “ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት።” የሚለው ቃል እግዚአብሔር በዚህ አካባቢ ብቻ አለ ተብሎ ቦታ የማይወሰንበት ፡ ሰማይም ምድርም ዓለማት በሙሉ ግዛቱ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው።
እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው ሰዎች በዚህ ዓለም መኖር የሚችሉት በሕይወት እስካሉ ድረስ ብቻ ነው። ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊ ኑሯቸው በሞት ይለወጣል። ዘፍ 3 ፥ 19። እግዚአብሔር ግን ዓለማት ሳይፈጠሩ የነበረ ፣ አሁንም እየገዛ ያለ ፣ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ፣ በባህርዩ ሞት ፣በመንግሥቱ ሽረት የሌለበት ዘለዓለማዊ አምላክ ነው። እኛ ሰዎች የተወለድንበት ቀን መጀመሪያችን ፤ የምንሞትበት ቀን መጨረሻችን ነው ፤ አምላክ ግን ሰው በመሆኑ ዘመን ቢቆ ጠርለትም ፤ ሥጋ ፡ የመለኮትን ባህርይ በተዋሕዶ ገንዘቡ ስላደረገ “ስለተዋሃደ” ፤ ዘመናት የማይቀድሙት ቀዳማዊ ዘመናትን አሳልፎ የሚኖር ደኃራዊ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ አምላክ ነው ። ራዕ 1 ፥ ፲፰ ለነበረበት መጀመሪያ ፤ የማይኖርበት መጨረሻ የለውም ፤ ለሁሉም ነገር መጀመሪያውም ሆነ መጨረሻው ራሱ ነው። ዘፍ 18 ፥ 14 ዘፀ 3 ፥ 14:
እግዚአብሔር ጥበበኛ (አዋቂ) ነው የሰው ልጅ ይዞት የተወለደው ልቅሶ ብቻ ነው። ሌላውን ሁሉ ፡ በማየት፣ በመስማት ፣ በመማር ፤ ከሰዎች ያገኘው ነው። ያውም ቢሆን ያለፈውን ታሪክ ከማውራትና አሁን የሚደረገውን ከማየት በቀር ወደ ፊት የሚሆነውን ለማወቅ የሚያስችል ዕው ቀትና ጥበብ የለውም። ዕውቀቱም ቢሆን የአንዱ ዕውቀት ከሌላው ይበልጣል ፤ በዚህ ዓለም ፍፁም የሆነ ዕውቀት የለም የተከፈለውም ቢሆን በጊዜው ያልፋል። 1ቆሮ 13 ፥ 8። እግዚአብሔር ጥበቡ የባህርዩ የሆነ ፣ ያለፈውን የማይረሳ ፣የሚያውቅ ፣ ለሰዎች ዕውቀትንና ጥበብን የሚገልጽ አምላክ ነው። ሰው ሊያውቅና ሊመራመር የሚችለው ውጫዊውንና ግዙፉን ነገር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ግን ልብና ኩላሊትን (በሰው ህሊና የታሰበውን) አስቀድሞ የሚያውቅ አምላክ ነው። መዝ 7 ፥ 9።
እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ቅድስና የእግዚአብሔር የባህርዩ ሲሆን “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ዘሌዋ 19 ፥ 2። 1 ጴጥ 1 ፥ 15። ባለው ቃል መሠረት ቅዱሳን መላእክትና በሥራቸው ለቅድስና የበቁ ሰዎችም ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ። የመላእክትና የሰዎች ቅድስና ግን ፡ በሥራ የሚገኝ ፣ በሃይማኖት የተፈተነ ፣ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የፀጋ ቅድስና ነው። የፍጡራን ቅድስና ደረጃ አለው ከአንዱ የሌላው ይበልጣል። 1 ቆሮ 15 ፥ 41። የእግዚአብሔር ቅድስና በመጠን አይወሰንም ፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለምና ። ኢሳ 6 ፥ 3። ዕንባ 1 ፥ 13።
እግዚአብሔር ቸር ነው የሰው ልጅ ቸርነቱ (ልግስናው) በኪሱ ያለው ሳንቲም እስኪያልቅ ፤ እሱንም ቢሆን የሚሰጠው ተለምኖ ነው። እግዚአብ ሔር ሁሉ ያለው ፣ ያለ ንፍገትና ያለ መሰሰት ለጋስ ፣ ስጦታው የማያልቅበት ፣ ኃጥዕ ጻድቅ ሳይል በቸርነቱ ለሁሉ ያለ አድልዎ የሚያድል ማቴ 5 ፥ 41። ሳንለምነው የሚያስፈልገንን አውቆ የሚሰጠን ፣ቸር አምላክ ነው። ማቴ 6 32። ሰው የሚሰጠው ከሌላው ያገኘውን ነው ፤ወደዚህ ዓለም የመጣው ራቁቱን ነው ፤ወደ ምድር ሲመለስም የሚያስከትለው ነገር የለውም። ኢዮ 1 ፥ 21። 1ጢሞ 6 ፥ 7። እኛ ለሌሌሎች የምንሰጠው ከተረፈን ብቻ ነው አምላካችን ግን ለእኛ የሰጠን ራሱን ነው። ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሐ 15 ፥ 13። ሰው የሚሰጠው ለወዳጁ ፣ ለወገኑ ፣ ለሚመስለው… ነው እግዚአብሔር ግን ጠላቶቹ ሳለን ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ከራሱ ጋር አስታረቀን ፤ ከዘለዓለም ሞትም አዳነን። ሮሜ 5 ፥ 10።
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ሰው ወዳጁን ይወዳል ለማይወደው ግን ቦታ አይሰጥም ፤ እንዲያውም ከተመቸው ከመበቀል ወደኋላ አይልም። እግዚአብ ሔር ግን እየበደልነው ለንስሐ እስክንዘጋጅ በብዙ ታግሶ ይወደናል። ሮሜ 2 ፥4። የሰው ፍቅሩ ተለዋዋጭ ፣ ወረት ያለበት ፣ ጊዜያዊ ነው። ሰው ለጥቅም ብሎ ወዳጁን ይገድላል። አምላካችን ፍቅሩ የማይለካ ፣ ለእኛ ለጠላቶቹ የሞተ ፤ ኢሳ 53 ፥ 1 ፥12። የሠራነውን ሁሉ በቸርነቱ ይቅር ብሎ ከበደል የሚያነጻን አምላክ ነው። ኢሳ 1 ፥ 18። እግዚአብሔር ፈቅደን እንድንገዛለት ይፈልጋል እንጅ ፤ ማንኛችንንም አስጨንቆ አይገዛንም። 1 ዮሐ 18
እግዚአብሔር በእውነት የሚፈርድ እውነተኛ ዳኛ (ፈራጅ) ነው እግዚአብሔር ለሰዎች የዳኝነት ሥልጣን የሰጣቸው ትክክለኛ ፍርድ እንዲፈረዱ ነው። ማንም ቢሆን እውነት መፍረድ እንዳለበት ህሊናው ይነግረዋል። በሐሰት ስንፈርድ በመጀመሪያ የሚወቅሰን ህሊናችን ነው። የህሊና ወቀሳን የማይፈራ ማንንም ሊፈራ አይችልም። ዳኞች ፡ በዘመድ ፣ በጥቅማ ጥቅም ፣ በዓላማ መመሳሰል ፡ እና በሌላም ፍርድ ሊያዛቡ ይችላሉ። እግዚአብሔር ግን ከማንም ምንም የማይፈልግ ፣ ከእውነት ጋር ደስ የሚለው ፣ ፍርዱ ትክክለኛ የሆነ አምላክ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል። ራዕ 22 ፥ 12። መዝ 36 ፥ 28
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ሀልወተ እግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️