የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የጥቃት ዓላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እንዲቆሙ ምእመናን ጠየቁ !
መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና መልእክቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ እና መንግስትም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ቲኤምሲ ያነጋገራቸው ምእመናን ገልጸዋል።
ማናቸውም ቤተ እምነቶች መብቶቻቸው እንዲከበር እንደሚፈልጉትና የሃይማኖታቸውን አስተምህሮ በነጻነት ማስተላለፍ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው እንደሆነ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ ምእመናኑ በተመሳሳይም ሁሉም ቤተ እምነቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት እና አስተምህሮ ባከበረ መልኩ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ነጻነታቸውን ተጠቅመው በማናቸውም መልኩ ሃይማኖታቸውን ማራመድ ሕገ መኖግስታዊ መብታቸው ቢሆንም የሌላውን እምነት ማንቋሸሽ፣ ማኮሰስ እና ማጥላላት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና ግጭት ቀስቃሽና ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ መሆኑ ነው የተገለጸው።
ባለፉት ጊዜያት ከአንዳንድ ቤተ እምነት ተከታዮች ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን፣ ስለ ንዋያተ ቅድሳት ብሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በምታስተምቸው ትምህርቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች ሲተላለፉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።
በተለይም መዋቅራዊ ድጋፍ እየተሰጠው በሚመስል መልኩ የጥላቻ ንግግሮች ተባብሰው መቀጠላቸው እና ይኸው ጥላቻም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን በሜንስትሪም እና በመጽሐፍትም ጭምር ሲካሄድ መቆየቱ እና እየተካሄደ መሆኑ በርካታ ምእመናንን ያሳዘነና ያስቆጣ መሆኑ ተመላክቶአል።
መንግስት እነዚህን የጥላቻ አራማጆች እና ጸረ ሃይማኖት ግለሰቦችን በሕግ አግባብ እንዲጠይቅም ምእመናን ጥሪ አቅርበዋል።